ሰኔ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እንደ ሪፖርተር ዘገባ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኛ የነበረው አቶ ሀሚድ ወዳጆ ህይወቱ ያለፈው ሰኔ 2 ቀን 2004 ዓ.ም ምሽት ላይ ቄራ አካባቢ በፖሊሶች በደረሰበት ከባድ ደብደባ ነው። አቶ ሀሚድ በፖሊሶች ተደብድቦ ሕይወቱ ሊያልፍ የቻለው ከጓዳኞቹ ጋር ሲዝናኑ አምሽተው በዕለቱ የ2012 የአውሮፓ ዋንጫ ተፋላሚ የነበሩትን የጀርመንን እና የፖርቹጋልን ጨዋታን በሚመለከት የተወሰኑት ‹‹ወደ ቤት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሲ.ፒ.ጄ በኢትዮጵያ በእስር ላይ ያሉትን ጋዜጠኞች ለመጎብኘት ያቀረበው ጥያቄ ሳይሳካ ቀረ
ሰኔ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እንደ ሲፒጄ መግለጫ፤ እስረኞቹን የመጎብኘቱ ጥረት ያልተሳካው፤ የሲፒጄ ልኡካን የታሰሩ ጋዜጠኞችን መጎብኘት እንደሚችሉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ቃል ከገቡ በሁዋላ ነው ። የዓለማቀፉ የጋዜጠኞች ተቋም ልዑካን -ከአፍሪካ ሚዲያ ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን ባለፈው ሳምንት በ ኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት፤ ከኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ ከአቶ በረከት ስምዖን ጋር ሁለት ሰ ዓታት የፈጀ ውይይት ማድረጋቸውን መግለጫው ያመለክታል። በውይይቱ ወቅት ...
Read More »ንግድ ባንክ የወጭ ገንዘብ አገልግሎት መስጠት ማቋረጡን ተከትሎ ከደንበኞቹ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገባ
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዘጋቢያችን እንደገለጠው ዛሬ ከጠዋቱ 3 ሰአት ጀምሮ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ አበባ በሚገኙ ሁሉም ቅርንጫፎች የወጭ ገንዘብ አገልግሎት መስጠቱን አቋርጧል። በመሀል መርካቶ አባኮራን ቅርንጫፍ በባንክ ሰራተኞችና በደንበኞች መካከል ግጭት መፈጠሩን ተከትሎ አንድ የባንኩ ሀላፊ ችግሩ የሰራተኞች አለመሆኑንና የቴሌ ሰርቨር የፈጠረው መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያን ንግድ ባንክ ከግንቦት 1 ጀምሮ በቴሌ ኔት ወርክ መጠቀም በመጀመሩ ...
Read More »አንድ ፖሊስ በልመና የሚተዳደርን ሰው ደብድቦ ገደለ
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወደ ተክለሀይማኖትና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በሚወሰድው መንገድ ላይ በርካታ ህጻናት ጎዳና ላይ ውለው ያድራሉ። ትናንት ከጧቱ 4 ሰአት ከ 30 ደቂቃ ላይ ነው። አንድ አዲስ አበባ ፖሊስ አባል አንድ በልመና የሚተዳደርን የጎዳና ተዳዳሪ ይደበድበዋል። የጎዳና ተዳዳሪውም በድብደባው ህይወቱ ያልፋል። ድብደባውን የፈጸመው ፖሊስና ጓደኞቹ በፍጥነት ከአካባቢው ይሰወራሉ። ትንሽ ቆይቶም ሌሎች ፖሊሶች በብዛት መጥተው አካባቢውን ...
Read More »በአዲስ አበባ ስታዲየም ለድብድብ የተገባበዙትን ባለሥልጣናት ፤ የዕለቱ የክብር እንግዳ ተነስተው ገላገሉ
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ነገሩ የሆነው፤በብራዚል ለሚደረገው የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያና -የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ባለፈው እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲዮም ግጥሚያ ሲያደርጉ ነው። ጠቡ የተፈጠረውም፤ ጨዋታውን ለመመልከት በክቡር ትሪቡን በታደሙ ሁለት ባለሥልጣናት መካከል ነው-በደደቢት ስፖርት ክለብ መስራች እና ፕሬዚዳንት በኮሎኔል አወል ኢብራሂም እና በስፖርት ኮሚሽነሩ በ አቶ አብዲሳ ያደታ መካከል። የሁለቱም ባለስልጣናት ጠባቂዎች ጠቡን ለማብረድ ያደረጉት ሙከራ በባለስልጣናቱ ...
Read More »በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አቶ ሽፈራው ሽጉጤን በመቃወም ሰልፍ አካሄዱ
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሳስካቺዋን፣ ማኒቶባ እና ከአልበርታ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን በሳስካቺዋን ዩኒቨርስቲ ፊት ለፊት በመገኘት ፣ ዩኒቨርስቲው በሙስና እና ዜጎችን በህገወጥ መንገድ በማፈናቀል የሚወነጀሉትን የደቡብ ፕሬዚዳንት የሆኑትን አቶ ሽፈራው ሽጉጤን መጋበዙን ተቃውመዋል። ሰልፈኞቹ ዩኒቨርስቲው አቶ ሽፈራውን ወደ መጡበት እንዲመለሱ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። ዩኒቨርስቲው የውጭ ጉዳይ ልዩ አማካሪ የሆኑት ቶም ዊሻርት፣ በአቶ ሽፈራው ላይ የቀረበውን አቤቱታ እንዳልሰሙ ነገር ግን ...
Read More »በኢህአዴግ እና በመምህራን መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እየተካረረ ነው
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ተቃዋሚ ናቸው” የተባሉ መምህራንን ከሥራቸው ለማባረር ለየትምህርት ቤቶች የወረደን መመሪያ ለማስፈፀም ፈቃደኛ ያልሆኑ ርዕሳነ-መምህራን በፈቃዳቸው ከሃላፊነታቸው ለመነሳት መልቀቂያ እያስገቡ ነው። ኢህአዴግ፤ የመንግስት ተቀጣሪ መምህራንን ለማባረር አዲስ ስልት መቀየሱን ውስጥ አዋቂ ምንጮች አጋለጡ፡፡ ቀደም ሲል መምህራን ፦“የሙያችን ክብር ተነክቷል፣ ዳቦ ለመብላት የሚያስችልና ከሁሉም ሙያዎች ጋር ትይዩ የሆነ የደሞዝ ማስተካከያ ስኬልና ጭማሪ ይደረግልን” የሚሉ ...
Read More »“ናሽናል ፕሬስ ክለብ” ፤ጋዜጠኛ አበበ ገላውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበውን ክስ ውድቅ እንዳደረገው አስታወቀ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የተባለው የገዥው ፓርቲ የፕሮፓጋንዳ አውታር አምባሳደር ብርሀነ ገብረክርስቶስን በማነጋገር ትናንት ባሰራጨው ቪዲዮ፤ ጋዜጠኛ አበበ ገላው በቡድን 8 አገሮች ስብሰባ ላይ በፈፀመው ተግባር፤ ከእንግዲህ የአሜሪካ መንግስት በሚያዘጋጃቸው ማናቸውም ስብሰባዎች ላይ እንዳይሳተፍ እገዳ እንደተጣለበትና የፕሬስ ፈቃዱን እንደተነጠቀ አውጇል። ከአሜሪካ የጋዜጠኞች ማህበር የተገኙት መረጃዎች ግን፤ ይህ የአምባሳደር ብርሀነ ገብረክርስቶስ ቃለ-ምልልስ ስህተት መሆኑን የሚያመለክቱ ...
Read More »የብርሃንና ሠላም በጋዜጣ አሳታሚዎች ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ አጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ “ፊልም የለኝም” በሚል አሳታሚዎች ተጨማሪ ወጪ አውጥተው ሌላ ማተሚያ ቤት እንዲያሰሩ የሰጠውን ትዕዛዝ አላነሳም፡፡ድርጅቱ በተጨማሪም እሁድ ዕለት የሚታተሙትን ሪፖርተር፣ፎርቹን፣ካፒታል የተባሉ ጋዜጦች የቀለም ሕትመት ማሸን ተበላሸቶብኛል በሚል ሳያትም የቀረ ሲሆን ፎርቹንና ካፒታል በዛሬው ዕለት በሁለት ቀለም ብቻ ለገበያ ሲወጡ የእሁዱ ሪፖርተር በነገው ዕለት ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡የእረቡ ሪፖርተር በዚህ ምክንያት ...
Read More »መኢአድ ሰኔ 1/1997 ዓ.ም በግፍ የተጨፈጨፉ ሰማእታትን ሰባተኛ ዓመት ዘከረ
ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በ1997 ዓ.ም በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ሰኔ 1/1997 ዓ.ም. ‹‹ድምፃችን ይከበር›› ብለው አደባባይ የወጡ ሰላማዊ ዜጎች በግፍ የተጨፈጨፉበትን ዕለት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሰኔ 3/2004 ዓ.ም. በጽ/ቤቱ ሻማ በማብራትና የተፈፀሙትን ዘግናኝ ድርጊቶች የሚያስታውሱና የሚያወግዙ ጽሁፎችን በማቅረብ አስቦ ውሏል፡፡ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ተቃውሞቸውን ለማሰማት ወደ አደባባይ በወጡ ዜጎች ...
Read More »