ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአንዋር መስጊድ ለጁማ ሶላት የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን ጥያቄያቸውን በጽናት እና በቁጭት አቅርበዋል። ድምጻችን ይሰማ፣ መጅሊስ አይወከለንም፣ ምርጫው በመስጊዳችን ይሁን፣ ህገ መንግስቱ ይከበርና የመሳሰሉትን መፈክሮች አሰምተዋል። መንግስት መጪው የመጂሊስ ምርጫ በቀበሌ እና በመስተዳድር ቦታዎች እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል። ሙስሊሙ ማህበረሰብ ምርጫው በቀበሌ መሆኑ፣ የኢህአዴግ ደጋፊዎችና ተማኞችን መልሶ ወደ መጅሊስ አመራር የሚመጣ ነው በማለት ይቃወማሉ። በዛሬው ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ስቴት ዲፓርትመንት እስረኞቹ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበ
ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የተላለፈውን የጥፋተኝነት ውሳኔ ተከትሎ የ አቶ መለስ መንግስት ከመላው ዓለም ጠንካራ ተቃውሞዎች እየተነሱበት ነው። የኢትዮጵያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በነ አንዷለም አራጌ መዝገብ በሽብርተኝነት በተከሰሱ 24 ሰዎች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ በ አቶ መለስ መንግስት ላይ ከ ዓለም ዙሪያ ጠንካራ ተቃውሞዎች እየተሰነዘሩ ነው። በፍርድ ቤቱ ብይን ላይ ተቃውሞ ...
Read More »ግንቦት7 የይስሙላውን ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳፋሪ ሲል አጣጣለው
ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የግንቦት7 ንቅናቄ ባወጣው መግለጫ ” የመለስ ዜናዊ የይስሙላ ፍርድ ቤት በ24 ንጹሀን ዜጎች ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ የሚገርም ” አይደለም ብሎአል። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲህ አይነቱን የይስሙላና አንድን ወገን ለመጥቀም ተብሎ የተደረገውን የድፍረት አሳፋሪ ውሳኔ የለመደው ነው የሚለው ንቅናቄው፣ በጋዜጠኞች ላይ የተላለፈው ውሳኔም ሀሳብን የመግለጽን መብት ሙሉ በሙሉ የሚደመስስ ነው በማለት አለማቀፍ የመብት ተንከባካቢ ...
Read More »የኦሎምፒክ ችቦ ቅብብል አባል እንዲሆን የተመረጠው ታዳጊ ወጣት ጠፋ
ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቢቢሲ ዛሬ ባወጠው ዘገባ እንደገለጠው ኢትዮጵያዊው የ15 ዓመት ታዳጊ ወጣት ፣ ናትናኤል የማነ፣ የኦሎምፒክ ችቦ ከሚያዞሩ ወጣቶች መካከል በመሆን ወደ እንግሊዟ ኖቲንግሀም ከተማ ባለፈው ሀሙስ አቅንቷል። ይሁን እንጅ ታዳጊው ወጣት ዛሬ ረፋዱ ላይ ከሆቴሉ እንደወጣ አልተመለሰም። የታዳጊው እንግሊዝኛ ችሎታ ውስን መሆንና መንገዶችን የማያውቅ በመሆኑ ፣ ታዳጊው ችግር ሊፈጠርበት ይችላል በማለት ፖሊሶቹ ስጋታቸውን ...
Read More »በሱዳን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የተቃዋሚ ደጋፊዎች የአልበሽር መንግስት እንዲወገድ ጠየቁ
ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሱዳን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የተቃዋሚ ደጋፊዎች አልበሽር መንግስት እንዲወገድ ጠየቁበካርቱም እና በኦምዱርማን ዛሬ ከፍተኛ የመንግስት ተቃውሞ ሰልፎች ተደርገዋል። ተቃዋሚዎቹ የአልበሸር መንግስት እንዲወገድ ጥያቄ አቅርበዋል። ፖሊሶች ተቃውሞውን ለማፈን የሀይል እርምጃ መውሰዳቸውም ታውቋል። ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________ ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other ...
Read More »የጭኮ እና የይርጋለም ህንጻዎች መፈክሮች ተውበው ታዩ፣ መፈክሮችን ለማጥፋት ህንጻዎች እንዲፈርሱ ተደርጓል
ሰኔ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጭኮና በይርጋለም ከተሞች ዛሬ ጠዋት የታየው ነገር በከተማዋ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው ይላል ዘጋቢያችን። ሰላም የራቀውና በሀዘን ድባብ ላይ የሚገኘው የከተማው ህዝብ ከቤቱ በጧት ሲወጣ የጠበቀው እንደ ሰሞኑ ፍርሀትና ጭንቀት ሳይሆን ደስታና ተስፋ ነበር። በከተማዋ የሚገኙ ህንጻዎች ሁሉም በሚባል ደረጃ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ሌሊቱን በሙሉ በደማቅ ቀለማት ሲሸለሙ አድረዋል። ህዝቡም በግድግዳዎቹ ላይ ...
Read More »ኢህአዴግ ነባር ታጋዮቹን ልዩ ተጠቃሚ የሚያደርግ ህግ አወጣ
ሰኔ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በነፍጥ ትግል የመንግሥት ሥልጣን የተቆጣጠረውና በአሁኑ ሰዓት ግን ኢህአዴግ በታገለበት መስመር በመሄድ በትጥቅ እና በሁለገብ ትግል ለውጥ ለማካሄድ የተደራጁ የተቃውሞ ኃይሎችን በአሸባሪነት የሚፈርጀው ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ለቀድሞ ታጋዮቹ ላሳለፉት የትግል ዘመን ልዩ የጡረታ ተጠቃሚ የሚያደርግ ደንብ አወጣ፡፡ በዚሁ ደንብ መሰረት አቶ መለስ ዜናዊን ጨምሮ ሌሎች ታጋይ የነበሩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ...
Read More »ከሳሾቼ እንድጠጣው የሚፈልጉትን የግፍ ጽዋ በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ሲል አቶ አንዱአለም አራጌ ተናገረ
ሰኔ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድነት ፓርቲ ም/ል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው አቶ አንዱአለም አራጌ ይህን የተናገረው ፣ የጥፋተኝነት ውሳኔ ለማስተላለፍ ዛሬ በዋለው ችሎት ላይ ነው። የዛሬውን የፍርድ ቤት ውሎ የተከታተለው ዘጋቢያችን እንደገለጠው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሶስተኛ ወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል የተከሰሱትን ሁሉንም ተከሳሾች ጥፋተኞች ብሎአቸዋል። ከ9 ነኛ እስከ 24ኛ ባሉት ላይ የጥፋተኝነቱ ውሳኔ የተላለፈው በሌሉበት እና ...
Read More »በአዋሳ ከተማ በተደረገው ስብሰባ ህዝቡ ስብሰባውን ረግጦ ወጣ
ሰኔ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትናንትናው እለት የክልሉ መስተዳደር ሀላፊ የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የአዋሳ ከተማ ነዋሪዎችን በአዋሳ ባህል አዳራሽ ውስጥ በሰበሰቡት ወቅት ነው ውዝግቡ የተፈጠረው። አቶ ሽፈራው ” ሲዳማ ክልል እንዲሆን የጠየቃችሁት መቼውንም አይሳካም ቁርጡን እወቁት ” በማለት ሲናገሩ ተሰብሳቢው ተቃውሞውን ገልጧል። በአዋሳ ተወልደው የኖሩ የሲዳማ ብሄረሰብ ተወላጅ ያልሆኑ የከተማው ነዋሪዎች ” እኛን የሲዳማ ህዝብ አላጠቃንም፣ ሲዳማ ...
Read More »ከታንዛኒያ ወደ ማላዊ ሲጓዙ የነበሩ 42 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሞተው ተገኙ
ሰኔ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የታንዛኒያ ያገር ውስጥ ምክትል ሚኒስትርን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው፤ በከባድ መኪና እንደ ዕቃ ከሁዋላ ታሽገው ወደ ማላዊ ሲጓዙ ከነበሩት 120 ሰዎች መካከል 42 ቱ ሞተዋል። ሚኒስትሩ ፔሬሪያ ሲሊማ እንዳሉት ስደተኞቹ የመጡት ከኢትዮጵያ ሲሆን፤የሞቱትም ከትራኩ የሁዋላ ክፍል ተጨናንቀው በመታሸጋቸው ሳቢያ አየር አጥሯቸው ነው። ታንዛኒያ እና ማላዊ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራቸው የሚፈጠርን ግጭት እና ድርቅን በመሸሽ ...
Read More »