ሐምሌ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከአርሲ ዞን ሦስት ወረዳዎች ብቻ ከ 10፣000 በላይ ገበሬዎች “ቦታችሁ ለልማት ይፈለጋል” ተብለው ከይዞታቸው በግዳጅ ሊፈናቀሉ መሆናቸው ተሰማ። በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከምዕራብ አርሲ ዞን ሶስት ወረዳዎች የተወከልን ነን የሚሉ ገበሬዎች ፦”ከሥራችንና ከመኖሪያችን እንድንነሳ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠን ስለሆነ፤ ፍትህ ይሰጠን” ሲሉ አቤት በማለት ላይ መሆናቸውን ፍኖተ ነፃነት ዘግቧል። ‹‹ከአያት ቅድመ አያቶቻችን ጀምሮ ተይዞ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአዲስአበባ አስተዳደር በቤት ልማት ስም የምርጫ ዘመቻ ጀመረ፡፡
ሐምሌ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የከተማ ልማትና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረገው የ40 በ60 የቤት ልማት ፕሮጀክት በቀጣይ ዓመት ከሚካሄደው የአዲስአበባ አስተዳደርና የአካባቢ ምርጫዎች ጋር የተገናኘ መሆኑን ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡ ባለፈው በሒልተን ሆቴል የከተማ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ፣የአዲስአበባ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ በጋራ ያፋ ያደረጉት ፕሮግራም በአምስት ዓመታት ተከታታይ ጊዜያት ውስጥ የሚገነባውን ቤት ግምት ...
Read More »ለፕሬስ ነፃነት ማንኛውንም መስዋትነት እንከፍላለን! ሲሉ የፍትህ ጋዜጠኞች ተናገሩ፡፡
ሐምሌ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የፍትህ ዋና አዘጋጅ የሆነው ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ባወጣው ጽሁፍ ” ነገም ፍትህ እንደወትሮዋ በመላ ኢትዮጵያ ጎዳናዎች አትነግስም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ነው፡፡ በማለት ችግሩን እንደሚከተለው ዘርዝሯል። “ነገሩ እንዲህ ነው፡- ዛሬ ረፋዱ ላይ የፍትህ ጋዜጣ ሽያጭ ክፍል ሰራተኞች ማታ ወደማተሚያ ቤት ለምትገባው ጋዜጣችን ክፍያ ሊፈፅሙ ሄዱ፡፡ የማተሚያ ቤቱ ሃላፊ ደግሞ ...
Read More »የኮሪያ ዘማቾች፤ በኮሪያ መንግስት የጡረታ ክፍያ ሊታሰብላቸው ነው
ሐምሌ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከ60 ዓመት በፊት ወደ ደቡብ ኮሪያ የዘመቱ ኢትዮጵያዊያን አርበኞች ከኮሪያ መንግሰት ጡረታ ሊቆረጥላቸው እንደሆነ ተገለጸ። በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ጃንግ ጊዮን ኪም እንዳሉት ፥ የጡረታውን አበል የደቡብ ኮሪያ መንግስት ለመቁረጥ የፈለገው ለሀገሪቱ ነጻነት ኢትዮጵያውያን አርበኞች ያደረጉትን ትልቅ ተጋድሎ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው። በዚሀም መሰረት አርበኞቹ በየወሩ ሰባት መቶ ብር እንደሚከፈላቸው አምባሳደሩ ጠቁመዋል። ...
Read More »በእስር ላይ በሚገኙ ሙስሊሞች ላይ አሰቃቂ ድበደባ እየተፈጸመባቸው መሆኑ ታወቀ
ሐምሌ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢሳት የፖሊስ ምንጮች እንደተናገሩት ባለፈው ሳምንት በሙስሊሙና በመንግስት መካካል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በተለያዩ እስርቤቶች በሚገኙ አማንያንና አመራሮች ላይ የሚፈጸመው ዘግናኝ ድርጊት እየጨመረ መምጣቱ ፣ አንዳንድ እስረኞች ስቃዩን መቋቋም ተስኖአቸው መንግስት የሚፈልገውን ሁሉ እንዳሉና ከስቃይ ለመገላገል ችለዋል። ሰውነታቸው ተገልብጦ የውስጥ እግራቸው የተገረፈ፣ ብልታቸው የተቀጠቀጠ፣ ጭናቸው መሀል ላይ መቆንጠጫ ብረት የገባላቸው፣ እጃቸው የፊጥኝ ...
Read More »የፍትህ ጋዜጣ እግድ ጸደቀ
ሐምሌ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፍትህ ጋዜጣን እግድ እንዲያፀድቅ በዐቃቤ ህግ ጥያቄ የቀረበለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት፤ ዛሬ ከሰዓት በሁዋላ ጉዳዩን በዝግ ችሎት በማየት የእግዱን ውሳኔ ተቀብሎ ማፅደቁን አሳውቋል። ይሁንና ችሎቱ መቼ እንደተካሄደ እና ልደታ ስንተኛው ችሎት ውስጥ እንደተካሄደ ሌላው ቀርቶ የጋዜጣው አዘጋጆች እንኳ እንደማያውቁ፤ ወኪላችን ከአዲስ አበባ ያጠናቀረው መረጃ ያመለክታል። ፍትህ፤ጠንካራ ትችቶችን በምክንያታዊ ትንታኔ ...
Read More »ጋና አዲስ ፕሬዚዳንት ሾመች
ሐምሌ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት የ68 አመቱ ጆን አታሚልስ ትናንት ካረፉ በሁዋላ፣ ጆን ማሀማ ፕሬዚዳንት በመሆን ዛሬ ቃለመሀላ ፈጽመዋል። ተቃዋሚዎች ሰላማዊውን የስልጣን ሽግግር ያደነቁ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንቱም ሁሉንም ጋናውያንን በእኩል እንደሚያገለግሉ እና ሁሉም ነገር ሰላም መሆኑን ተናግረዋል። የአለም መሪዎች ለሟቹ ፕሬዚዳንት ያላቸውን አድናቆት እየገለጡ ነው። የላይቤሪያዋ መሪ፣ ፕሬዚዳንቱ የተለየ ስእብና ባለቤት መሆናቸውን ሲናገሩ፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ...
Read More »በመልጋ ወረዳ በተነሳ ግጭት ከ19 በላይ ፖሊሶች በጽኑ ቆሰሉ
ሐምሌ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትናንትናው እለት ከአዋሳ ከተማ በ26 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዋ ማልጋ ወረዳ በተፈጠረው ግጭት 3 የፌደራል ፖሊስ አባላት በጽኑ መቁሰላቸውን የዘገብን ቢሆንም፣ ዛሬ ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ ያጠናከረው መረጃ እንደሚያመለክተው ከ19 በላይ ፖሊሶች እና ከ20 በላይ ነዋሪዎች በጽኑ ቆስለዋል። አናታቸው የተፈነከተ ፣ እግራቸው የተሰበረ፣ እንዲሁም በጥይት የቆሰሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት መንገድ ላይ ወድቀው ይታዩ ነበር። ...
Read More »ሲፒጄ በፍትህ ጋዜጣ ላይ የተጣለውን እገዳ ኮነነ
ሐምሌ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ተቀማጭነቱ ኒውዮርክ የሆነው አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት ( ሲፒጄ) በፍትህ ጋዜጣ ላይ የተጣለው እገዳ በኢትዮጵያው ውስጥ የሚታየው አፈና የደረሰበትን ደረጃ ያሳያል ብሎአል። የሲፒጄ የምስራቅ አፍሪካ ዋና አማካሪ የሆኑት ቶም ሮድስ እንደተናገሩት ” የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የጠቅላይ ሚኒሰትሩን ህመም በተመለከተ ምን ነገር እንዲነገርባቸው አይፈልጉም፣ ይህም በአገሪቱ ውስጥ የተንሰራፋውን የአፈና መጠን በገሀድ የሚያሳይ ...
Read More »የአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕርትርክና 20ኛ ዓመት በዓለ ሢመት በሼራተን አዲስ ተከበረ
ሐምሌ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ደጀ-ሰላም እንደዘገበው፤የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት እና ራእይ ለትውልድ ፤ በእንግሊዝኛው አጠራር ፦/Vision for Generation/ የተባለው አካል የጥቅም ትስስር የፈጠሩበት የሼራተኑ በዓለ ሢመት ዝግጅት የተከናወነው፤ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ይኹን አለያም በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት፤ እስካሁን አልታወቀም። በዚሁ የአቡነ ጳውሎስ 20ኛ ዓመት በዓለ-ሢመት ላይ፤ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የአብያተ እምነት መሪዎችን፣ አምባሳደሮችንና ታዋቂ ግለሰቦችን ጨምሮ በሺህ ...
Read More »