ሐምሌ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት በጥንቃቄ የመረጣቸው የሲዳማ ተወላጆች በዛሬው እለት በሲዳማ ባህል አዳራሽ ተሰብስበው የክልሉ መንግስት ያቀረባቸውን ጥያቄዎች ህዝቡ እንዲጠይቅ አደርገዋል። 12 ጥያቄዎች ለባለስልጣናት የቀረቡ ሲሆን፣ አቶ ሽፈራው ” የሲዳማን ጥያቄ አሁን ለማቅረብ እንደማይቻል፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሽሎአቸው ወደ ስራ ሲመለሱ እንደሚያቀርቡት ተናግረዋል። በከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ፣ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሀብታሞችና የኢህአዴግ አባላት ጭንቀት ውስጥ ናቸው::
ሐምሌ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ ተሻሽሎ ከዛሬ ነገ ወደ አገር ይመለሳሉ በማለት ተስፋ አድርገው የነበሩት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የአገር ውስጥ እና የውጭ ባለሀብቶች እንዲሁም የኢህአዴግ አባላትና በመካከለኛ ደረጃ የሚገኙ ባለስልጣናት በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንደሚገኙ ነው የኢሳት የመንግስት የውስጥ ምንጮች የሚናገሩት። ባለሀብቶች በየጊዜው ከባለስልጣናት መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት እንደሚያደርጉ የገለጡት ምንጫችን ፣ ...
Read More »ከ20 ሺ በላይ ሰዎች የሞያሌን ግጭት በመሸሽ ኬንያ ገቡ::
ሐምሌ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ቢቢሲ ቀይ መስቀልን ጠቅሶ እንደዘገበው በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል በተነሳው ግጭት 18 ሰዎች ተገድለው 12 ደግሞ ቆስለዋል። ኢሳት ትናንት ከአካካቢው ሰዎች እና ከተለያዩ ድርጅቶች ባሰባሰበው መረጃ 20 ሰዎች መገደላቸውን፣ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የፌደራል ፖሊስ አባል መሆኑን፣ 7 የክልል ፖሊሶች መቁሰላቸውን ዘግቦ ነበር። ዛሬ በደረሰን ዘገባ ደግሞ የሟቾች ቁጥር 30 ደርሷል። ከ20 ...
Read More »በመላ አገሪቱ የሚታየው የኑሮ ውድነት መክፋቱ ተነገረ::
ሐምሌ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ መስሪያ ቤት እና የገንዘብ ሚኒሰትሩ አቶ ሶፍያን አህመድ የዋጋ ንረቱ እየወረደ ነው በማለት በተናገሩ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዋጋዎች እንደገና ወደ ላይ እየወጡ ነው። የእህል ዋጋ በከፍተና ፍጥነት እየጨመረ ሲሆን አንዳንድ የፍጆታ እቃዎችም ከገበያ እየጠፉ ነው። ዘይት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በዋና ከተማዋም ሆነ በክልል ከተሞች ጠፍቷል። ምግብ ...
Read More »መንግስት በሙስሊሞች ላይ የሚሰራውን ድራማ በሲዳማ ለመፈጸም እየተዘጋጀ ነው ተባለ::
ሐምሌ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የድምጻችን ይሰማ ተቃውሞውን ለማኮላሸት መንግስት በክፍለሀገራት የሚገኙ ሙስሊም የሆኑና ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን ከየቦታው በማሰባሰብ እንቅስቃሴውን እንዲያወግዙ በማድረግና በቴሌቪዥን ቀርጾ በማቅረብ ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ስራ እየሰራ ሲሆን፣ ይህንኑ ስትራቴጂ በሲዳማ ላይ ለመድገም ዝግጅት ጀምሯል። በሲዳማ የተነሳው ተቃውሞ በተለያዩ ጊዜዎች እያገረሸ በንጹህን ዜጎች እና በፌደራል ፖሊስ አባላት ህይወት ላይ ጉዳት ...
Read More »በአንዋር መስኪድ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ ትግላችን አይቀዘቅም አለ::
ሐምሌ ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን በስፍራው ተገኝቶ እንደተመለከተው ዛሬ ለተቃውሞ የወጣው ሙስሊም ኢትዮጵያዊ እስከዛሬ ከተሳተፈው ሁሉ በቁጥር በእጅጉ የሚልቅ ነው። ዋና ዋና መሪዎቹ በማእከላዊ እስር ቤት በአሰቃቂ ድብደባ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን የኢሳት እንዲሁም የአምነስቲ ኢንተርናሽናል መረጃዎች ይፋ ባደረጉ ማግስት፣ አንዳንዶች አንድ ሚሊዮን ሌሎች ከ700 ሺ እስከ 800 ሺ የሚገምቱት ህዝብ ተቃውሞውን በዝምታ፣ በጭብጨባና እጆቹን ...
Read More »ሞያሌ ኣካባቢ በተነሳው ግጭት ከ20 በላይ ሰዎች ተገደሉ::
ሐምሌ ፳ (ሀያ)ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ኢሳት የሞያሌ ነዋሪዎችን በስልክ አነጋግሮ ባጠናከረው መረጃ ከሶስት ቀናት በፊት በተነሳው ተቃውሞ ከ20 በላይ ሲቪሎችና 1 የፌደራል ፖሊስ ተገድለዋል። 7 ፖሊሶች ደግሞ በጽኑ ቆስለዋል። ግጭቱ የሶማሊ ብሄረሰብ ተወላጅ በሆኑ ገሪዎችና የኦሮሞ ተወላጅ በሆኑ ቦረናዎች መካከል የተፈጠረ ቢሆንም፣ የሁለቱም ክልል ፖሊሶች ጎራ ለይተው መታኮሳቸውን ነው ነዋሪዎች የሚገልጡት። ሞያሌ ከተማ በሁለት የክልል መንግስታት የምትተዳደር ከተማ ...
Read More »የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም፤ በአቡነ ጳውሎስ ተሾሙ።
ሐምሌ ፳ (ሀያ)ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአቡነ ጳውሎስ 20ኛ ዓመት በዓለ-ሲመት ሐምሌ 16 ቀን 2004 ዓ.ም ምሽት በሼራተን አዲስ ለሁለተኛ ጊዜ በተከበረበት ጊዜ ይፋ የሆነውንና በፓትርያርኩ ስም በ 200 ሚሊዮን ብር ወጪ ሊገነባ የታሰበውን ሆስፒታል በበላይነት እየተቆጣጠሩ እንዲያስፈፅሙ ነው ሚኒስትር ቴዎድሮስ የተሾሙት። በዚሁ በሸራተን በተካሄደው የፓትርያርኩ በዓለ-ሲመት ዝግጅት ላይ፤ የክብር እንግዳ የነበሩትን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን እና ...
Read More »በመልጋ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በወንዶገነትም ተመሳሳይ ተቃውሞ ተነስቷል።
ሐምሌ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ከሶስት ቀናት በፊት በሲዳማ ዞን በመልጋ ወረዳ የተነሳው ተቃውሞ ወደ ወንዶገነትም ተዛምቶ፣ የባሻ ወረዳ ሊቀመንበር መገደሉንና የወረዳው መስተዳደር መኪና መቃጠሉን ዘጋቢያችን ገልጧል። በግጭቱም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ፣ ነገር ግን በርካታ ቁጥር ያላቸው ፖሊሶች መቁሰላቸው ታውቋል። ሁለቱ ወረዳዎች ኩታገጠም ሲሆኑ፣ በመልጋ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የወረዳው ባለስልጣናት ህዝቡን ለማሳመን ወደ ታች ወርደው በሚነጋገሩበት ጊዜ ...
Read More »አምነስቲ በሙስሊሞች ላይ አሰቃቂ ግፍ ተፈጽሟል አለ፡፡
ሐምሌ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይህን ያስታወቀው “በሙስሊም ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥሰት ሳይፈጸም አልቀረም” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ላይ ነው። ድርጅቱ እንዳለው በእስር ላይ የሚገኙት ሙስሊም ተቃዋሚዎች፣ አሰቃቂ ድብደባ ( ቶርቸር) እንደተፈጸመባቸው የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ ብሎአል። አንዳንድ እስረኞች ከቤተሰቦቻቸው እንዳይገኙ ተደርጎ ለብቻቸው መታሰራቸውን፣ በአንዳንዶች ላይም ጭካኔ የተሞላበት ድብደባ መፈጸሙን ገልጧል። ፖሊስ ተቃውሞውን ...
Read More »