.የኢሳት አማርኛ ዜና

የረሀብ አድማው አፈና እስር ትኩረት እንዲያገኝ ይረዳል ተባለ

ከነገ እኩለ ሌሊት እስከ ኦገስት 19 ወይም ነሐሴ 13 በዋይት ሀውስ ፊት ለፊት የሚደረገው የረሀብ አድማ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን የመብት ረገጣ አጉልቶ ለማሳየት እንደሚረዳ የረሀብ አድማው አዘጋጅ  ቃል አቀባይ ለኢሳት ገለጹ:: ቃል አቀባይዋ ወይዘሪት ትርሲት ጌታቸው፤ ነጻ ሚዲያ ለኢትዮጵያ የሚባለው ቡድን የረሀብ አድማ እንዲደረግ የወሰነው በሀገራችን እየተባባሰ ያለውን የመብት ገፈፋ በተለይ ደግም  በጋዜጠኞች ላይ የተጣለውን አፈና እስርና እንግልት በመቃወም መሆኑን ...

Read More »

የግራዚያኒ ሀውልትና የመታሰቢያ ፓርክ ውስጥ ተቃውሞ ቀሰቀሰ

የጣልያን መንግስት ለፊልድ ማርሻል ግራዚያኒ ያቆመው ሀውልትና የመታሰቢያ ፓርክ በኢጣሊያ ውስጥ ተቃውሞ እንደቀሰቀሰ ቢቢሲ ዘገበ። የቤኔቶ ሙሶሎኒ የጦር መሪ በመሆን፤ በሊቢያና በኢትዮጵያ በፈጸመው ከፍተኛ ፍጅትና ግድያ የተፈረደበት ግራዚያኒ፤ የ160 ሺህ ዶላር መታሰቢያው የቆመለት፤ ከሮም ወጣ ብላ በምትገኝ መንደር ውስጥ ነው። የኢጣሊያ ዋንኛው ግራ-ዘመም ፓርቲ፤ ግራዚያኒ በ1930ዎቹ ውስጥ በኢትዮጵያ የፈጸመውን የዘር ማጥፋት በማስታወስ፤ በዚህ ዘመን ለግራዚያኒ ይህ መታሰቢያ መቆሙን አጥብቆ አውግዟል። ...

Read More »

ሙስሊም ጋዜጠኞች አገር ጥለው ተሰደዱ

(Aug. 16) የመንግስት ጥቃት በመፍራት ከሀገር መሰደዳቸውን ሁለት የሙስሊሞች ጉዳይ ጉዳይ ጋዜጠኞች ይፋ አደረጉ። መንግስት ሁለቱን ጋዜጤኞች በቁም እስር ላይ አስቀምጧቸው እንደነበር ይታወሳል። ጋዜጠኛ ይስሐቅ እሸቱ እና አክመል ነጋሽ የተባሉት፤ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ወቅታዊ ጥያቄ አጉልቶ በማሳየት የሚታወቀው የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሄት አዘጋጆች፤ መንግስት በሙስሊሙና በጋዜጠኞች ላይ የሚያደርሰውን ግፍ በመፍራት ከሐገር መሰደዳቸውን የጋዜጠኞቹን የቅርብ ሰዎች በመጥቀስ ፍኖተ ነጻነት ዘግቧል። ጋዜጠኞቹ የሙስሊሞን እንቅስቃሴና ...

Read More »

የዳላስ ግድያ በኢትዮጵያኖች ላይ ሀዘንና ድንጋጤ ፈጥሯል

(Aug. 16) በዳላስ፤ ቴክሳስ የደስታ ሬስቶራንት ባለቤት በነበሩት አቶ ያየህ ይራድ ለማና ወ/ሮ የኔነሽ ደስታ ላይ በትላንትው እለት የተፈጸመው የግድያ ወንጀል በዳላስ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ላይ ክፍተኛ ሀዘንና ድንጋጤ ፈጥሯል:: በዳላስ መልካም ስም ካላቸው የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶች በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው የደስታ ሬስቶራንት ባለቤት የሆኑት ኢትዮጵያውያን ስራቸውን እኩለ ሌሊት ላይ አጠናቀው ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲመለሱ መግቢያ በር ላይ የተገደሉት በጥይት ተመተው መሆኑ ...

Read More »

የአቡነ ጳውሎስ ዜና እረፍት የተደበላለቀ ስሜት ፈጥረ

ነሀሴ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጻውሎስ ፓትሪያሪክ ርዕሰ ሊቀጻጻስት ዘኢትዮጵያ ሊቀጻጻሳት ዘአክሱም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣የዓለም አብያተክርስቲያናት ፕሬዚዳንት በ76 ዓመታቸው አርፈዋል። 20ኛ ዓመት የሲመት በዓላቸውን ሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም በሸራተን ሆቴል ያከበሩት አቡነ ጻውሎስ በባልቻ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ትላንት ለሊት አርፈዋል። ኢትዮጵያውያን በተለይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በጳጳሱ ዜና እረፍት የተደበላለቀ ስሜት ተስምቷቸዋል። የአዲስ ...

Read More »

የአቡነ ጳውሎስ የስልጣን ዘመን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ቸግር አምጥቶ ማለፉን የተለያዩ የሀይማኖት አባቶች ገለጡ

ነሀሴ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአቡነ ጳውሎስ የስልጣን ዘመን በጎንደር አደባባይ እየሱስ ህዝቡን በመቀስቀስ ግጭት አስነስተዋል ተብለው ለ12 አመታት በእስር የማቀቁት፣ አባ አመሀ እየሱስ አቡነ ጰውሎስ ከማረፋቸው ከ10 ቀናት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢሳት በሰጡት ቃለምልልስ አቡኑን ከፉኛ ተችተዋል። አባ አምሀእየሱስ ከደርግ ጊዜ ጀምሮ ዋልድባ ገዳምን ሊደፍሩ በተነሱት ላይ ሁሉ የእግዚአብሄር ተአምራት ታይቷል። አባ አምሀ እየሱስ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ...

Read More »

አቶ መለስ ዜናዊን ለመተካት አዲስ ህግ ተረቀቀ

ነሀሴ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ለኢሳት እንደገለጡት ፍትህ ሚኒስቴር እጅግ ጥብቅ በሆነ ሚስጢር አዲስ ህግ አርቅቆ ለፓርላው የህግ ክፍል ልኳል። በከፍተኛ ሚስጢር በተያዘው በዚህ ህግ የማርቀቅ ስራ ላይ የተሻለ የህግ እውቀት አላቸው የተባሉ ሰዎች  ተሳትፈዋል። አቶ መለስን የመተካቱ ነገር ያለቀለት ጉዳይ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጠዋል። ፓርላመው ምናልባትም የፊታችን ማክሰኞ ካልሆነም በሚቀጥለው ሳምንት ...

Read More »

በደቡብ ክልል ከፖሊስ መጋዘን የጦር መሳሪያ ተዘረፈ

ነሀሴ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል ከሚገኘው ደራሼ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት መጋዘን ውስጥ  የጦር መሳሪያ መዘረፉ ተገለፀ፡፡ የጦር መሳሪያው በጊዜያዊነት በመጋዘን ተሰብስቦ የነበረው በአሁን ወቅት በ“አሌ” ወረዳ የሚገኘው ህዝብ፤ በደራሼ ልዩ ወረዳ ስር በነበረበት ወቅት ነው። በ1997 ዓ.ም የወረዳ ህዝብ ላቀረበው ራስን ችሎ የመዋቀር ጥያቄ አመራሩ ተግባራዊ ምላሽ እንደሚሰጥ  ቃል ቢገባም፤ በወቅቱ በነበረው አገር አቀፍ ምርጫ ...

Read More »

የቦረና ዞን ዋና አስተዳደር ታሰሩ

በቦረና  ዞን በጋሬና ቦረና ጎሳዎች መካከል የተሳው ግጭት የረገበ ቢሆንም፤ ችግሩ ግን አሁንም መቀጠሉን ከስፍራው የመጣው ዜና ያስረዳል። ይህንንም ተከትሎ የቦረና ዞን ዋና አስተዳደር መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሏል። ግጭቱን ተከትሎ በቦረና ዞን ግምገማ እየተካሄደ ሲሆን፤ ለግምገማው መነሻው ግጭቱን ተከትሎ በቦረና ዞን “ኢሕአዲግ አይገዛንም” የሚል ተቃውሞ በመሰማቱ ነው ተብሏል። በቦረና ዞን ነዋሪዎች የተነሳውን ይህንን ተቃውሞ መቆጣጠር ባለመቻል ወይንም ቀጥተኛና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ...

Read More »

አቡነ ጳውሎስ በ76 ዓመታቸው አረፉ

(Aug. 16) የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ፤ በ76 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ጤናቸው እያቆለቆለ መምጣቱ የተገለፀው አቡነ ጳውሎስ፤ ነሐሴ 10/2004 ዓ.ም፤ ንጋት ላይ በባልቻ ሆስፒታል ሕይወታቸው ማለፉንም ቤተክርስቲያኒቱ አረጋግጣለች። የአቡነ ጳውሎስን ሕልፈት ተከትሎ የቀብር ሥርዓቱን የሚያስፈጽም ኮሚቴ በመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ፅ/ቤት መቋቋሙን  ደጀ ሰላም ዘግቧል። መኖሪያ ቤታቸውና ቤተ መፃሐፍቱ፤ ጳጳሣት በተገኙበት መታሸጉም ተመልክቷል። አቡነ ...

Read More »