.የኢሳት አማርኛ ዜና

ሰባት አባላት ያሉት ቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ተዋቀረ እስከቀብሩ ድረስ የሚቆይ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ

ሰባት አባላት ያሉት ቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ተዋቀረ እስከቀብሩ ድረስ የሚቆይ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት በይፋ ከተነገረ በኃላ የመጀመሪያ በሆነው የመንግስት መግለጫ የቀብር አስፈጻሚ ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋሙን፣ከዛሬ ጀምሮ እስከቀብር ቀን የሚዘልቅ ብሔራዊ የሐዘን ቀን መታወጁን፣የአገሪቱ ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አቶ በረከት ስምኦን አስታወቁ፡፡ ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት በሒልተን ሆቴል በሰጡት መግለጫ ብሔራዊ ኮሚቴው የቀብሩን ቀንና ሥነሥርዓት በተመለከተ በቀጣይ ...

Read More »

ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ማረፋቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያው ጠ/ሚ፤ አቶ መለስ ዜናዊ በተወለዱ በ57 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ይፋ አደረገ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት ሁለት ወራት ከተሰወሩ በኋላ ነው ዛሬ፤ ማክሰኞ፤ ነሀሴ 15 ቀን መሞታቸው የተዘገበው። ኢሳት ሀምሌ 23 ቀን፤ የአለምአቀፉን የቀውስ አጥኚ ቡድን (አይ.ሲ.ጂ) ውስጣዊ ምንጮችን ጠቅሶ የአቶ መለስን ሞት መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የአቶ መለስን ሞት ሲያስተባብሉ ቆይተዋል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ...

Read More »

ወቅታዊ ዜና:- ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከፖሊስ አባላት ጋር ተጋጩ በርካታ ሰዎች ተጎድተዋል

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከፖሊስ አባላት ጋር ተጋጩ በርካታ ሰዎች ተጎድተዋል በዛሬው የኢድ አል ፈጥር በአል ላይ በጊዮን ሆቴል በኩል የተቃውሞ መፈክሮችን እያሰሙ ሲሄዱ የነበሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፣ ከብረት ለበስ የፌደራል ፖሊስ አባላት  ጋር ተጋጭተዋል። በርካታ ሙስሊሞች ተረጋግጠዋል፣ በቆመጥና በዱላ ተደብድበዋል፤ የተፈነከቱ፣  እጅና እግራቸው የተሰባበሩ ሰዎች ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተወስደዋል። አንዲት እርጉዝ ሴት መረገጧንም ዘጋቢያችን ገልጧል። ብዙዎችም በፖሊስ ካሚዮን ተጭነው ወደ ...

Read More »

ወቅታዊ ዜና:-በኢድ አል ፈጥር በአል ላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰማ

በኢድ አል ፈጥር በአል ላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰማ የተወሰኑ ሰዎች ታሰሩ በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢድ አል ፈጥርን በአል ለማክበር የተሰባሰቡ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተዋል። የክብር እንግዳው የነበሩት የአዲስ አበባ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ እና የእስልምና ምክር ቤት ሃላፊዎች ንግግር እንዳይደመጥ እና እንዲቋረጥ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተቃውሞው እንደተጀመረ የቀጥታ ስርጭቱን አቋርጧል። በተመሳሳይም በደሴ ፣ አዳማ ( ናዝሬት) , ጅማ ...

Read More »

የደህንነት ሹሙ አቶ አቶ ጌታቸው አሰፋ “የጠቅላይ ሚኒስትሩን ህመም ተከትሎ ጎንበስ ቀና ማለቱ ያስተዛዝባል” አሉ

ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የብሄራዊ የመረጃ እና የደህንነት ምንጭ እንደገለጠው የደህንነት ዋና ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋ ሰሞኑን ዋና ዋና የሚባሉ የኢሚግሬሽንና የውጭ መረጃ ሰራተኞችን እና በተለያዩ ተቋማት የተመደቡ የደህንነት አባላትን ሰብስበው በአቶ መለስ ዜናዊ የደህንነት ሁኔታ ላይ ገለጻ ሰጥተዋል። ከስብሰባው በፊት በከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ ለሚገኙት የደህንነት አባላትና የመንግስት ባለስልጣናት ” የጠቅላይ ሚኒስትሩን ህመም ተከትሎ ...

Read More »

ብአዴን እየታመሰ ነው

ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የብአዴን አባል የሆኑ ታማኝ የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ሰሞኑን የብአዴን የኮር አባላት ለሁለተኛ ጊዜ በአቶ በረከት መሪነት በባህርዳር ከተማ ስብሰባ አድርገዋል። የአማራ ክልል የወጣቶች ፕሬዚዳንት የሆነው ወጣት ዘመነ ካሴ ከአገር መውጣቱና ለኢሳት  ቃለምልልስ መስጠቱ፣  በክልሉ የተነሳው የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ከአቶ መለስ ዜናዊ የጤንነት ሁኔታ ጋር ተደማምሮ በብአዴን የኮር አባላት ላይ ከፍተኛ ፍርሀት እና አለመረጋጋት ...

Read More »

ልዑል ሙሉጌታ አስራተ ካሳ ተባረሩ

ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከውጭ ጉዳይ ሰራተኞች በደረሰው መረጃ ልኡሉ በትናንትናው እለት በ2 የደህንነት ሰዎች ታጅበው ምርር ብለው እያለቀሱ ከለንደን ኢምባሴ ወጥተዋል። የኢህአዴግ ካድሬ በመሆናቸው ለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የአማካሪነት ቦታ አግኝተው የነበሩት አስራቴ ካሳ ፣ ከስራ የተባረሩት ያለ ኢምባሲው ፈቃድ ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ዝግጅት ጳጳሱን በተመለከተ ቃለምልልስ ሰጥተዋል ተብሎ ነው። እርሳቸው ግን ቃለምልልሱን ...

Read More »

በነገው የኢድ በአል ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል

ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ እና አካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ በቅርቡ በፌደራል ፖሊስ እና በደህንነት ሀይሎች በማእከላዊ እስር ቤት በቁጥጥር ስር የዋሉ የኢትዮጵያ ሙስሊም ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ለማስፈታት የነገውን የኢድ አል ፈጥር በአል የአዲስ አበባ ስታዲዮምን ስግደት ሊጠቀሙበት መዘጋጀታቸውን ምንጮቻችን ገልጠዋል። የታሰሩ ወገኖቻችንን ሳናስፈታ ወደ ቤታችን አንገባም የሚል መሪ ቃል መዘጋጀቱም ታውቋል። በትናንትናው የጁመአ ...

Read More »

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንትን ለመምረጥ ፍትጊያው ቀጥሎአል

ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከምግብ መመረዝ ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሕመም ምክንያት ከኃላፊነታቸው ለመነሳት ከአንድ ዓመት በፊት የስራ መልቀቂያ ጥያቄ ያቀረቡት የኦህዴድ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት እንዲሁም የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አለማየሁ አቶምሳ እስካሁን ጥያቄያቸው ምላሸ ባለማግኘቱ ፣ እርሳቸውን ማን ይተካ የሚለው ጥያቄ በኦህዴድ ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ መፍጠሩ ታውቋል። በጳጉሜ ወር 2002 ዓ.ም በአዳማ ...

Read More »