(Aug. 27) የመንገስት መገናኛ ብዙሀን ስለ አቶ መለስ ጀግንነትና እንከን የለሽነት የሚያቀርቡት የግለሰብን ተክለ-ሰውነት ወይንም ፕረሰናሊቲ ከልት የመገንባት፤ እንዲሁም፤ በአቶ መለስና በፓርቲያቸው የተሰሩ ስህተቶችንና ደካማ ጎኖችን እንድንረሳ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት ነው ሲሉ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ተናገሩ። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ጽሁፍ አቶ መለስ ሰው እንደመሆናቸው፤ ድክመቶችና ስህተቶችም እያሉባቸው፤ እንደእንከን የለሽ ሰው የማቅረቡ ሂደት መጪው ትውልድ ከአቶ መለስ ህስተት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ህዝቡ ለአቶ መለስ ሀዘኑን እንዲገልጽ ጫናዎች እየተደረጉበት ነው
(Aug. 27) የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝቡ ሀዘኑን እንዲገልጽ የተለያዩ ጫናዎች እየተደረጉበት እንደሆነ ከኢትዮጵያ የሚመጡት መረጃዎች አስረዱ። ለጎንደር ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ የተጻፈ ደብዳቤ እንደሚያሳየው የጎንደር ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ በመስቀል አደባባይ ተገኝቶ ሀዘኑን እንዲገልጽ ታዞ እንደነበር ታውቋል። በዚህም መሰረት፤ ባለፈው አርብ በጎንደር መስቀል አደባባይ በተዘጋጀው የሀዘን መድረክ ላይ፤ የመንግስት ሰራተኞች በሙሉ ከስራ መግቢያ ሰዓት ቀደም ብለው ከጠዋቱ 1 ሰዓት ከ40 ...
Read More »የተመስገ ደሳለኝን እስራት አምነስቲ አወገዘ
(Aug. 27) የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ እስራት፤ መንግስት የተለየ ሀሳብ ያላቸውን ሰዎች የጥቃት ኢላማ ማድረጉን እንደሚቀጥልበት ጠቋሚ ነው፤ ሲል አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ስጋቱን ገለጠ። አቶ ተመስገን ደሳለኝ ባለፈው ሀሙስ መታሰሩ የሚያሳየው ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላም ኢትዮጵያ ውስጥ ነገሮች እንዳልተቀየሩ ነው ሲሉ ክሌር ቤስተን የአምነስቲ አለማቀፍ የኢትዮጵያ ተመራማሪ ተናግረዋል። ተመስገን የታሰረው ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብቱን ሲጠቀምና ...
Read More »የአቶ ሀይለማርያም ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ኢህአዴግን እያወዛገበ ነው
ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአራት ቀናት በፊት የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት ይፋ ባደረገበት ወቅት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ፤አቶ መለስን ተክተው በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንደሚሰሩ መወሰኑን ይፋ ቢያደርግም፤ በተለይ በህወሀት በኩል በተቀሰቀሰ ከፍተኛ ተቃውሞ እስካሁን የ አቶ ሀይለማርያም ሹመት ሊጸድቅላቸው እንዳልቻለ የኢሳት የውስጥ ምንጮች ጠቁመዋል። አቶ ...
Read More »የመለስን እረፍት ተከትሎ ኢትዮጵያ የነጻነት አየር ትተነፍሳለች ብየ አምናለሁ ሲሉ ክብርት አና ጎሜዝ ተናገሩ
ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአውሮፓ ፓርላማ አባልና በ1997 ዓም በኢትዮጵያ የተካሄደውን ምርጫ የታዘቡት ክብርት አና ጎሜዝ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ፣ በማንም ሰው ሞት መደሰት ተገቢ ባይሆንም፣ የመለስን ሞት ተከትሎ ኢትዮጵያ የነጻነት አየር ትተነፍሳለች ብየ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል። መለስ ዜናዊ አምባገነን፣ የገዛ ህዝቡን ጨፍልቆ የገዛ ነው ያሉት ክብርት አና ጎሜዝ፣ አለማቀፉ ማህበረሰብ የመለስን ስራዎች እያየ ...
Read More »የኩማ አስተዳደር በይፋ ድንኳን ተክሎ ለቅሶ ተቀመጠ
ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኩማ አስተዳደር በተለምዶ ማዘጋጃ ቤት ተብሎ በሚጠራው ቅጥር ግቢ ውስጥ የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት አስመልክቶ ሁለት ትልልቅ ድንኩዋኖችን በግቢው ውስጥ ተክሎአል። አስተዳደሩ ከፌዴራል መንግስት በተለየ የከተማዋ ነዋሪዎች ሐዘናቸውን የሚገልጹበት ቦታ ያስፈልጋል በሚል ሁለት ትልልቅ ድንኩዋን ትላንት የተከለ ሲሆን አንዳንድ ሰዎች ሐዘናቸውን በለቅሶ በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በይፋ ባይገለጽም የአቶ ...
Read More »ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንዳይጎበኝ በበላይ አካል ተከልክሏል” ይላሉ የማረሚያ ቤት ምክትል ኃላፊ
ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከትላንት በስተያ ዕለት በፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 16 ወንጀል ችሎት የዋስትና መብቱ ተገፎ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሆኖ ክሱን እንዲከላከል የተፈረደበት የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፌዴራል ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የታሰረበት ዞን /ቀጠና/ እና ክፍል አልታወቀም፤ ሊጎበኙት የመጡ ሰዎች ሁሉ እንዳያገኙት ተከልክለዋል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገንን ለመጠየቅ መጥተው አለ የተባለበት ...
Read More »የሼክ ሙሀመድ አላሙዲን ከህዝብ እይታ መጥፋት አነጋጋሪ እንደሆነ ነው
ነሀሴ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ ደጋፊ የሆኑት ባለሀብቱ ሼክ ሙሀመድ ሁሴን አልአሙዲን በብጹወ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነስርአት እንዲሁም፣ በአቶ መለስ ዜናዊ አስከሬን አቀባባል ዝግጅት ላይ አልተገኙም። አንዳንድ ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ባለሀብቱ በሳውዲ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው። ይህንን መረጃ ግን ከነጻ ወገን ማረጋጋጥ አልተቻለም። የባለሀብቱ ኩባንያ የሆነው ሚድሮክ ሰራተኞች በአቶ መለስ ዜና እረፍት ሀዘናቸውን ...
Read More »አቶ በረከት ስምኦን ባለስልጣኖች አቶ መለስ ዜናዊን አርዓያ በማድረግ ተከትለው እንዲሄዱ ተማጸኑ
ነሀሴ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ በረከት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “በሀይወት ዘመናቸው አቶ መለስ የያዙት ዓላማ የጥቂቶች ዓላማ ከሆነ ሞት ነበር ” ብለዋል ። የመንግስትና የኢህአዴግ አመራርም የህዝቡን መልዕክት ተቀብለን ጠቅላይ ሚኒስትሩን አርዓያ አደርገን ለመከተል ወስነናል የሚሉት አቶ በረከት፤ ሌሎች ባለስልጣኖችና የኢህአዴግ አመራር አካላት፣ ህዝቡ እና የአለማቀፉ ማህበረሰብ ከጎናቸው እንዲቆም ተማጽነዋል። ኢሳት በትንናት ዘገባው አንድ የብአዴን ...
Read More »የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነ ስርዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፀመ
ነሀሴ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የፕትርክና ታሪክ አወዛጋቢ የሆኑት ብጹወ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የመንግስት ባለስልጣናት እና ሌሎች ዲፐሎማቶች በተገኙበት ዛሬ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን የቀብራቸው ስነስርአት ተፈጽሟል። ከሃምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ 20ኛ አመት በአለ ሲመታቸውን ሲያከብሩ የነበሩት አቡነ ጳውሎስ፣ በድንገት ማረፋቸው የብዙዎች መነጋገሪያ አጀንዳ እንደሆነ ነው። በተለይም የእርሳቸውን ሞት ተከትሎ የአቶ መለስ ዜናዊ ዜና እረፍት ...
Read More »