Author Archives: Central

አራት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የ 2012 ትን ዓለማቀፍ የሄልማን ሽልማት አሸኛፊ ሆኑ

ታህሳስ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሄልማንን የክብር ሽልማት ያሸነፉት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች፦ በእስር ላይ የሚገኙት እስክንድር ነጋ፣የአውራምባ ታይምሱ ውብሸት ታዬ፣የፍትህ አምደኛዋ ርዕዮት ዓለሙ እና በስደት የሚገኘው የአዲስ ነገሩ መስፍን ነጋሽ ናቸው። በሂዩማን ራይትስ ዎች አማካይነት የሚሰጠውን ይህን የክብር ሽልማት ያገኙት አራቱም ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ መንግስት የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸዋል። አጠቃላይ ለዘንድሮው የሄልማን ሽልማት የበቁት ከ19 አገራት የተውጣጡ 41 ጋዜጠኞች ሲሆኑ፤ለሽልማት ...

Read More »

መስፍን ኢንጂነሪንግ ኩባንያ የ2.6 ቢሊዮን ብር ኮንትራት ተሰጠው

ታህሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለቤትነቱ የሕወሀት የሆነው መስፍን ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ከሶስት የስኳር ፋብሪካዎች የ2.6 ቢሊዮን ብር ኮንትራት እንደወሰደ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘገበ። ከተቋቋመ 19 አመት የሞላውና የትግራይ መልሶ ማቋቋም ኢንዳውመንት ፈንድ የተሰኘው ግዙፍ ድርጅት አካል የሆነው መስፍን ኢንጂነሪንግ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገነቡ 3 ስኳር ፋብሪካዎች የሚሆኑ የማፍሊያ ቤቶችን (ቦይሊንግ ሀውሶች) ለመገንባት ነው የ2.6 ቢሊዮን ብሩን ኮንትራት የወሰደው። የመስፍን ኢንጂነሪንግ ምክትል ...

Read More »

ጠቅላይ ፍርድቤት የእነ አቶ አንዱዓለምን ይግባኝ አዳመጠ

ታህሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ጠቅላይ ፍርደ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝግብ በሥር ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል ጥፋተኝነት የተፈረደባቸውን የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላትና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ይግባኝ ክርክር አድምጧል፡፡ ከቃሊቲ እና ቂሊንጦ እስር ቤቶች የቀረቡት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አንዷለም አራጌ፣ የፓርቲው አመራር አባልና የወጣቶች አደራጅ ኃላፊ ናትናኤል ...

Read More »

ሙስና እና ብልሹ አሰራርን በአደባባይ ያጋለጡት ሚኒስትር ዴኤታ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተዘገበ

ታህሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሳምንታዊው ሰንደቅ እንደዘገበው ፤በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያለውን ብልሹ አሰራር እና ሙስና ከሳምንታት በፊት በይፋ ያጋለጡት  ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ዳውድ መሐመድ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርገዋል። ሚኒስትር ዴኤታው  አቶ ዳውድ መሐመድ ከኃላፊነታቸው የተነሱት በቅርብ የበላይ አለቃቸው ማለትም በባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሩ  በአቶ አሚን አብዱልቃድር እና በሌላዋ ሚኒስትር ዴኤታ በወ/ሮ ታደለች ዳለቾ መካከል  የተፈጠረውን አለመግባባት አስመልክቶ   ለሰንደቅ ጋዜጣ በይፋ ...

Read More »

ዶ/ር ኃይሉ አርአያ በፈቃዳቸው ከኃላፊነት ተነሱ

ታህሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለረጅም አመታት በተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ውስጥ በከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ ሲሰሩ የቆዩት ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ከአንድነት ፓርቲ ኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ተነሱ። የፓርቲው ብሔራዊ ም/ቤት ባለፈው እሁድ ባካሄደው ስብሰባ ላይ የዶ/ር ኃይሉ ጥያቄን በመቀበል በእሳቸው ምትክ ወጣት ዳንኤል ተፈራን ተክቷል። ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ከኃላፊነታቸው መነሳት የፈለጉት ከጤና ችግር እና ኃላፊነትን ለወጣቶች ለማስረከብ ካላቸው ፍላጎት በመነሳት መሆኑን  ተናግረዋል። ...

Read More »

ኢሳት በናይል ሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያሰራጨው ስርጭቱ ቢቋረጥም፣ ስርጭቱን በአሞስ ሳተላይት እያስተላለፈ ነው

ታህሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ላለፉት ሶስት ወራት ስርጭቱን በ ናይልሳት ሲያሰራጭ ከቆየ በሁዋላ የኢትዮጵያ መንግስት ስርጭቱን ከማፈን አልፎ ባደረገው ከፍተኛ የሎቢንግ ዘመቻ የኢሳት ስርጭት እንዲቋረጥ አድርጓል። በመላው አገሪቱ ኢሳት ቁጥር አንድ ተመራጭ የቴሌቪዥን ጣቢያ በመሆን የሰፊውን ህዝብ የመረጃ ጥማት ለማርካት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ለገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ራስ ምታት ሆኖበት እንደነበር ኢሳት የኢትዮጵያ  ወኪል ገልጿል። ምንም እንኳ ...

Read More »

ራሳቸውን ተበዳይ ኮሚዩኒተሮች በማለት የሚጠሩ የመንግስት የህዝብ ግንኙነት ሰራተኞች የተቀነባበሩ መረጃውን ለአለም ይፋ እንደሚያደርጉ አስጠነቀቁ

  ታህሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአቶ በረከት ስምኦን በሚመራው የኮምኒኬሽን መስሪያ ቤት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ፣ መስሪያ ቤቱ የሚፈጽመውን አድሎአዊ አሰራር በመንቀፍ ለአቶ በረከት ስምኦን የጻፉትን ደብዳቤ ግልባጭ ለኢሳት ልከዋል። በደብዳቤው  አቶ በረከት በሚመሩት መስሪያ ቤቱ ወስጥ በህዝብ ግንኙነት ስራ ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ኮሚኒተሮች ላይ የሚፈጸመው አድሎ የማይቆም ከሆነ እንዲሁም ድብዳቤው የቀረበላቸው አቶ በረከት በተለመደ ንቀታቸውና ዝምታቸው የሚቀጥሉ ...

Read More »

33 የፖለቲካ ድርጅቶች በምርጫ ስም ገንዘብ ማባከን እንዲቆም ጠየቁ

ታህሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቶቹ ባወጡት መግለጫ በጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በአዳማ ኤክስኪዩቲቭ ሄቴል በዚህ አመት በሚደረገው የአካባቢ እንዲሁም የአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ ምርጫ የግዜ ሰሌዳን አስመልክቶ  የውይይት መድረክ መጥራቱን ጠቅሰዋል። ድርጅቶቹ በመግለጫቸው ” ምርጫ ለማካሄድ ነባራዊ ሁኔታው የማይፈቅድ ስለሆነ በፖለቲካ ምህዳሩና በህዝብ ወሳኝነት ሁሪያ መወያየት አለብን ብለን ፒቲሺን ተፈራርመን ለቦርዱ ያስገባን 33 ፓርቲዎች ...

Read More »

ባለፉት 6 አመታት ሩብ ሚሊዮን ኢትዮጵያን ወደ አረብ አገራት ተሰደዋል

ታህሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የሚዲያ ዊዝ ኮንሳይስ ዋና አዘጋጅ ግርሀም ፔብልስ ባወጣው  ጽሁፍ እንዳመለከተው ባለፉት 6 ዓመታት 250 ሺ ኢትዮጵያውያን ወደ አረብ አገራት ተሰደዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞችን ኮሚሽን በመጥቀስ ባሰራጨው ዘገባ ደግሞ በዚህ አመት 85 ሺ አትዮጵያውያን በመንገድ ላይ የሚያጋጥማቸውን አስቸጋሪ ሁኔታ ተቋቁመው የመን ገብተዋል። በየመን ከሚደርሱት ስደተኞች መካከል 50 በመቶ የሚሆኑት ስደተኞች የኦነግና የኦብነግ አባላት ...

Read More »

የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲፈታ ጥያቄ አቀረቡ

ታህሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-16 የ አውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በፃፉት ግልጽ ደብዳቤ የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እንዲፈታ ጥያቄ አቀረቡ። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ አረብ አለም አብዮት በ ኢትዮጵያ ሊከሰት የሚችልበት ዕድል ሰፊ ስለመሆኑ በድረ ገጾች በመጻፉ ሳቢያ የስብርተኝነት ክስ ተመስርቶበት የ 18 ዓመት እስራት እንደተወሰነበት የጠቀሱት  የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላቱ፤ ይህም አልበቃ ...

Read More »