Author Archives: Central

በአላማጣ የአንድ አካባቢ ነዋሪዎች ቀኑን ሙሉ በልዩ ሀይሎች ታግተው ዋሉ

ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ጋርቬ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩ የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ጧት ወደ ስራ ለመሄድ ሲነሱ አካባቢያቸው በሙሉ በፌደራል    ልዩ ሀይል ፖሊሶች ተከቦ አግኝተውታል። ማንም ከቤት እንዳይወጣ በማገድ የመንግስት ባለስልጣናት በስም ጽፈው የያዙዋቸውን ከ300 በላይ ቤቶች ሲያስፈርሱ ውለዋል። በእያንዳንዱ ቤት በር ላይ ሁለት ሁለት ልዩ ፖሊሶች ቆመው የእያንዳንዱን ሰው ቤት እንቅስቃሴ በሚከታተሉበት ሁኔታ ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችን እያበረረ በኢህአዴግ አባላት እየሞላ ነው

ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአየር መንገዱ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት በኢህአዴግ አባሉ ስራ አስኪያጅ በአቶ ተወልደ ገብረማርያም ፣ በተጠባባቂው ስራ አስኪያጅ በአቶ ኢሳያስ ወልደማርያም እና በኦዲተሩ በአቶ ዋሱ ዘለለው አነሳሽነት ነባር ሰራተኞች ከስራ እየተቀነሱ  በኢህአዴግ የወጣት ፎረም አባላት እየተተኩ ነው። በቅርቡ 36 የትኬት ሽያጭ ሰራተኞች እና 14 ኤጀንቶች ከስራ ተባረው በፎረሙ አባላት ...

Read More »

“በአስመራ ሁሉም ነገር የረጋጋ ነው” ሲሉ የፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ተናገሩ

ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- አቶ የማነ ገብረቀመስቀል ለኤኤፍ ፒ  አስመራ እንደትናንቱ ሁሉ ዛሬም የተረጋጋች ናት በማለት ተናግረዋል። በደቡብ አፍሪካ የኤርትራ አምባሳደር የሆኑት ሳሊህ ኦማር በበኩላቸው ምንም የመፈንቅለ መንግስት ሙከራም ሆነ ምንም አይነት የአመጽ እንቅስቃሴ  አልታየም ብለዋል። ቢቢሲ ባሰራጨው ዘገባ ደግሞ የማስታወቂ ሚኒሰቴር መስሪያ ቤትን የተቆጣጠሩት አማጺዎች፣ መስሪያ ቤቱን ለቀው ወጥተዋል። ተቋርጦ የነበረው የአገሪቱ ቴሌቪዥን ስርጭቱን ...

Read More »

የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ ኢትዮጵያ መንግስትን አስጠነቀቀ

ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በኢትዮጵያና በዛምቢያ መካከል  ትናንት ምሽት የተደረገውን እግር ኳስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን  ከማሰራጫ ቻናል  በድብቅ በመውሰድ ማስላለፉን ደርሸበታለሁ ሲል የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን(ካፍ)  መግለጹን ኒው ቢዝነስ ኢትዮጵያ ዘገበ እንደ ዘገባው  የ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን  ሌሎች የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚያሰራጩትን ጨዋታ በመስረቅ ጫዋታውን እንዳስተላለፈ የተደረሰበት በእረፍት ሰዓት የጨዋታው ስፖንሰር እንደሆኑ አድርጎ የበርካታ ድርጅቶችን ማስታወቂያ ሢሰራ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አስደናቂ ውጤት አገኘ

ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:– ብሄራዊ ቡድኑ ዛሬ ከአምናው ሻምፒዮን ዛምቢያ ጋር ተጫውቶ አቻ ተለያይቷል። ዋልያዎች ጀግንነታቸውን አስመሰከሩ በ29ኛው አፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ ቀትር ላይ ከዓምናው ሻምፒዮን ከዛምቢያ ቡድን ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ 10 ሰው ተጫውቶ 1ለ1 ተለያዬ። በሺዎች በሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው የእልታ ዜማ ታጅበውና ከላይ እስከ ታች በቢጫ አሸብርቀው ወደሜዳ የገቡት ዋልያዎች ...

Read More »

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በደቡብ አፍሪካ ተቃውሞአቸውን አሰሙ

ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:– በኢትዮጵያ እና በዛምቢያ መካከል የተካሄደውን የአፍሪካ ዋንጫ ተከትሎ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ መንግስት በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚወስደውን እርምጃ ተቃውመዋል። ሙስሊሞቹ መሪዎቻችን ይፈቱ፣ በእምነታችን አንደራደርም፣ የሀይማኖት ነጻነት ይከበር፣ የሚሉ መፈክሮችን በእንግሊዝኛ በመጻፍ ለአለም የቴሌቪዥን ተመልካቾች አሳይተዋል። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ብሄራዊ ቡድኑን በከፍተኛ ስሜት ከመደገፍ አልፈው በእረፍት ሰአቶቻቸው ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ ተስተውሎአል።

Read More »

ልዩ ሀይል በአላጣማ መግባቱን ተከትሎ በከተማው ያለው ውጥረት አይሏል

ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:– የኢሳት የአላማጣ ምንጮች እንደተናገሩት በዛሬው እለት በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 12 ሰአት አካባቢ ከመቀሌ የተነሱ በ3 መኪኖች የተጫኑ ልዩ የፌደራል ፖሊስ አባላት አላማጣ በመግባት ህዝቡን እያሸበሩት ነው። በከተማዋ ጋርቬ እየተባለ በሚጠራው  አካባቢ የሚገኙ 200 የሚጠጉ የቤት ባለንብረቶች ንብረቶቻቸውን ነገ ማክሰኞ የማያወጡ ከሆነ ፣ ቤቶቻቸው በዶዘሮች እንደሚፈርሱ ንብረቶቻቸውም እንደሚወረሱ እንደተነገራቸው ታውቋል። ...

Read More »

መንግሥት የበጀት ጉድለቱን ለመሸፈን ከአገር ውስጥ ባንኮች ሊበደር ነው

ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም   ኢሳት ዜና:– የአገሪቱን  ኢኮኖሚና የዜጎችን ኑሮ እየተፈታተነ የሚገኘውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር  ከ እንግዲህ ከአገር ውስጥ አንበደርም ሲል የነበረው የ ኢትዮጵያ መንግስት ዘንድሮ ያጋጠመውን የበጀት ጉድለት መሸፈን ባለመቻሉ  ከ አገር ውስጥ ባንኮች ሊበደር እንደሆነ ሪፖርተር ዘገበ። ለኑሮ ውድነቱ ጣራ መንካት አንዱና ዋነኛው ምክንያት መንግስት ከ አገር ውስጥ መበደሩና ይህንንም ብድር ለማሟላት ብር እንዲታተም ...

Read More »

የጥምቀት በአል ተከበረ

ጥር ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ በየአመቱ የሚከበረው የጥምቀት በአል ዘንድሮም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በድምቀት ተከብሯል። በአዲስ አበባ በ ጃንሜዳ ማረፊያቸውን አድርገው የነበሩ ታቦታት አብዛኞቹ ወደ መጡበት በሰላም ተመልሰዋል።

Read More »

የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን 70 በመቶው የአመራር ቦታ በህወሀት አባለት የተያዘ ነው ተባለ

ጥር ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግንቦት7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለኢሳት በላከው ሁለተኛ ጥናቱ ላይ እንዳመለከተው በ11 መምሪያዎች የተዋቀረው በስሩ አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱስትሪዎቸን የሚያስተዳደርው የኢትዮጵያ ብረታ ብረት እንጂኔሪንግ ኮርፓሬሺን አስራ አንድ ትላልቅ መምሪያዎችና አስራ ሦስት ግዙፍ እንዱሰትሪዎች በዋና ሀላፊነት፤ በዳይሬክተርነትና በምክትል ዳይረክትርነት የሚመሩ በ29 የከፍተኛ አመራር አባላት ነው። ከእነዚህ 29 ከፍተኛ አመራር አባላት ዉስጥ 69 በመቶዉ ...

Read More »