Author Archives: Central

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሙስሊሙ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ አንድ ሥራ-አስኪያጁን ማባረሩ ታወቀ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአየር መንገድ የውስጥ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሼባ ማይልስ እየተባለ የሚጠራውን ክፍል በስራ አስኪያጅነት ሲመሩ የነበሩትን አቶ አብዱል ጀባር ሀሚድን ከስራ ያባረረው የአየር መንገዱ ሙስሊም ሰራተኞች ከሌሎች ወገኖች ጎን ተቀላቅለው ተቃውአቸውን እንዲገልጹ አደራጅቷል በሚል ምክንያት መሆኑ ታውቋል። ስራ አስኪያጁ በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። በተያየዘ ዜናም በሱፐርቫይዘርነት ደረጃ ...

Read More »

ፓሊሶች በአራት ኪሎ የሚገኙ ቤቶችን በእሳት አቃጠሉ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለረጅም አመታት በአራት ኪሎ አካባቢ የኖሩ  ሰዎች ቦታው ለሼራተን ሆቴል ማስፋፊያ ይፈለጋል በሚል ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ሲነገራቸው እንደቆየ የተናገሩት አይን እማኞች፣ ነዋሪዎቹ በበኩላቸው መንግስት ተተኪ ቤት እስካልሰጣቸው ድረስ አካባቢውን ለቀው እንደማይሄዱ ሲከራከሩ ቆይተዋል። ዛሬ ጧት ወደ አካባቢው ያቀኑት ፖሊሶች ነዋሪዎቹ እቃዎቻቸውን ሳያወጡ በቤታቸው ላይ እሳት በመልቀቅ ቤታቸውን አቃጥለውባቸዋል። ነዋሪዎቹ በጩሀት ወደ ፓርላማ ...

Read More »

በጥምቀት በዓል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሲሸጡ የነበሩ ሰዎች ታሰሩ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብዙውን ጊዜ በጥምቀት በዓል ጊዜ የሚጠቀሰውንና ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በላከው መልእክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር 5 ላይ ያሰፈረውን ፦“አንድ ጌታ፣ አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ጥምቀት” የሚል  የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የተፃፈበት ቆብ  የጥምቀት ዕለት ለሰንበት ት/ቤታቸው ገቢ ማስገኛነት በመሸጥ ላይ የነበሩ ወጣቶች በፖሊስ ታፍሰው ታሰሩ። እንደ ደጀ ሰላም ዘገባ፤ ጥር 11/2005 ዓ.ም ታቦተ ሕጉን ...

Read More »

የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት አደጋ ላይ ናቸው

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በ12ኛው ክፍለ ዘመን ከአለት ተፈልፍለው የተሠሩት ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በከፍተኛ የመሰንጠቅ አደጋ ላይ መሆናቸውንና አስቸኳይ መፍትሔ ካላገኙም ሊፈርሱ እንደሚችሉ ቅርሶችን የተመለከተው የፓርላማ ቡድን ማመልከቱን ሪፖርተር ዘገበ የቤተ ጊዮርጊስ፣ ቤተ ጐለጐታ፣ ቤተ መርቆርዮስና ቤተ ደናግል አብያተ ክርስቲያናት በከፍተኛ ደረጃ መጎዳታቸው ተገልጿል። ታሪካዊዎቹ ህንጻዎች እየተሰነጠቁ መሆናቸውም በዘገባው ተጠቅሷል። የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዳይሬክተር ...

Read More »

ወ/ሮ አዜብ የመለስ ፋውንዴሽንን በፕሬዚዳንትነት ይመራሉ ተብሎ ይጠበቃል

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ፓርላማ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ዕለት ያጸደቀውና በቢሊየን ብር የሚቆጠር ዓመታዊ በጀት ይኖረዋል ተብሎ የሚገመተው የመለስ ፋውንዴሽንን ወ/ሮ አዜብ መስፍን  በፕሬዚዳትነት ይመሩታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አመለከቱ፡፡ ባለቤታቸውን በድንገት በነሐሴ ወር 2004 አጋማሽ በሞት ካጡ በኋላ  ከአራት ወራት በላይ በተመረጡበት የፓርላማ ወንበር ላይ ተቀምጠው ያልታዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ይኸን ሃላፊነት ...

Read More »

በአለም ላይ እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ የተሰቃየ የለም ያሉት አቶ ስብሀት ነጋ ዛሬ ያ ሁኔታ መቀየሩን ገለጡ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- አንዱ ጠግቦ ሲያድር ያልጠገበው ደግሞ በሰላም ተኝቶ ያድራል ብለዋል:: አዲስ አበባ ለሚታተመው ኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ከቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ በፊት የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህውሀት) መሪ የነበሩትና ዛሬ በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ ተጽዕኖቸው እየበረታ መሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ስብሀት ነጋ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህመም ወዲህ ሚዲያ ላይ በብዛት እየቀረቡ መገኘታቸውን በዚህም ...

Read More »

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ክፍያ ሳይፈጽም ጫወታ ማሰራጨቱ የሚዲያ ስነምግባርን የጣሰ ውንብድና ነው ተባለ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለ ኤል ሲ ቱ የተባለ የቴሌቪዥን ጣቢያ ክፍያ ሳይፈጽም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከዛንቢያ ቡድን ጋር ያደረገውን ጫወታ ማሰራጨቱ የሚዲያ ስነምግባርን የጣሰ ውንብድና ነው ተባለ:: ምንጮቻችን ባደረሱን መረጃ መሰረት የአፍሪካ ዋንጫ የቴሌቪዥን ስርጭት ባለመብት ለሆነው ለ ኤል ሲ 2 ክፍያ ሳይፈጽም ስርጭቱን ማስተላለፉ ተመልክቶል:: በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተፈጸመውና ውንብድና የተሰኘው ለስርጭቱ ባለመብት ...

Read More »

የአፍሪካ ስፖርት ፌዴሬሽን ካፍ ኢትዮጵያን 10 000 የአሜሪካ ዶላር መቅጣቱን አስታወቀ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአፍሪካ ስፖርት ፌዴሬሽን ካፍ ኢትዮጵያን 10 000 የአሜሪካ ዶላር መቅጣቱን አስታወቀ:: ሳላሀዲን ሰኢድ ከዛምቢያ ጋር በተደረገው የመጀመሪያ ግጥሚያ ምርጥ ተጫዋች ተባለ:: በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ባደረገው ግጥሚያ ደጋፊው ህዝብ የተለያዩ ነገሮችን ወደ ሜዳው በመወርወር በዛምቢያ ቡድን ላይ ላሳየው ተቀባይነት የሌለው ተቃውሞ ቅጣቱ መጣሉን ቢቢሲ አመልክቶል:: በደቡብ አፍሪካ ...

Read More »

ሞተዋል ተብለውት የተገነዙትና የተለቀሰላቸው አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት የቀብራቸው እለት ህይወት መዝራታቸው ተገለጠ

ጥር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሞተዋል ተብለውት የተገነዙትና የተለቀሰላቸው አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት የቀብራቸው እለት ህይወት መዝራታቸው ተገለጠ:: አዲስ አድማስ ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው ድርጊቱ የተፈጸመው በትግራይ መቀሌ ሲሆን ከመቃብር ተርፈው ህይወት የዘሩት እናት ወ/ሮ ወይኒ ጸጋዬ እንደሚባሉ ተዘግቦል:: በመቀሌ ከተማ 03 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ወይኒ ጸጋዬ ጥቅምት 5 ቀን 2005 ማለዳ ላይ ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿ አስከሬናቸው ...

Read More »

የባህርዳር ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ግቢአቸውን ለቀው ወጡ

ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ስር በሚገኙት በፔዳ ፣ ፖሊ፣ ይባብና  ዘንዘልማ  ካምፓሶች ይማሩ የነበሩ ከ95 በመቶ ሙስሊም ተማሪዎች ግቢአቸውን ለቀው መውጣታቸውን የተወሰኑትም ወደ መጡበት አካባቢ መመለሳቸውን  ተማሪዎች ገለጹ። ተማሪዎቹ ግቢአቸውን በመልቀቅ ትምህርታቸውን ለማቋረጥ የወሰኑት ከሶስት ሳምንት በፊት የግቢው አስተዳዳሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚደረግ ጸሎት እንዲቆም፣ ሴቶች ጂሃብም ኒቃምብ እንዳይለብሱ መከልከላቸውን ተከትሎ ነው። አንዳንድ ተማሪዎች ...

Read More »