ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ አራት አመት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ 8 ሺ 2 መቶ 46 የመኪና አደጋ የተከሰተ ሲሆን ፣ 5 ሺ 101 ዜጎች እጃቸውን እና እግራቸውን አጥተው ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በኢትዩጵያ በየደቂቃው ከሞት ጋር የሚጋፈጡ የመኪና አደጋ ችግር የሰው ልጅ ራስ ምታት ሁኗል፡፡ የመኪና አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመቀነስ ይልቅ ሲጨምር እንደሚታይ የገለፁት ኑዋሪዎች የመንግስት ...
Read More »Author Archives: Central
መንግስት ሕዝበ ሙስሊሙን ለማውገዝ የሠላም ኮንፈረንስ ጠራ
ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላትን በማንቀሳቀስ አገር አቀፍ የሠላም ኮንፈረሰንስ ለማካሄድ መዘጋጀቱን ይፋ አደረገ፡፡ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ እንደማይገባ ሕገመንግስቱ ቢደነግግም የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር በሕገመንግስት አስተምህሮ ስም የሃይማኖት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጭምር በማቋቋም የመብት ጥያቄ በማቅረባቸው ምክንያት የታሰሩና የሽብርተኝነት ክስ የቀረበባቸውን የሕዝበ ሙስሊም ማህበረሰብ አባላትና ደጋፊዎቻቸውን እንቅስቃሴ ለማፈን አሁንም በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል ሲሉ አንድ ...
Read More »የፕሮቴስታንት ሀይማኖት ተከታዮች እየተሳደድን ነው አሉ
ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ወሎ ዞን ከወልድያ ከተማ በ140 ኪሜ ርቅት ላይ በትምገኘዋ መቀት ወረዳ የሚገኙ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ከፍተኛ እንግልት እደረሰባቸውና አካባቢውንም ለቀው እንዲወጡ ግፊት እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጸዋል። እስካሁን በደረሰን መረጃ 10 የሚሆኑ የሀይማኖቱ ተከታዮች አካባቢውን ለቀው የወጡ ሲሆን፣ አንድ ተመስገን የተባለ ወጣት ለተባባሪ ዘጋቢያችን እንደገለጸው አማኞቹ ድንጋይ ይወረወርባቸዋል፣ ቤታቸውም በድንጋይ ይደበደባል። ተመስገን ሀምሌ 1 ...
Read More »በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ከተሰጠው ብድር ውስጥ 1 ቢሊዮን ብር አልተመለሰም
ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ ልሳን የሆነው ፋና እንደዘገበው ከ2003 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ለተሰማሩ ማህበራት 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ብድር ቢሰጥም ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የሚሆነው አልተመለሰም ። ብድርን በማስመለስ በኩል የቅንጅት እጦት ፣ አስቀድሞ የመስሪያ ቤቶችን ያለማዘጋጀትና የገበያ ትስስሮሽን በበቂ ሁኔታ አለመፍጠር መሰረታዊ ጅግሮች መሆናቸው ተጠቅሷል። ገንዘብ ተበድረው ከሃገር የሚጠፉ ፣ በቂ ...
Read More »በደቡብ ወሎ ዞን በሚገኘው ኩታበር ወረዳ አንድነት ፓርቲ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. በደሴ ያካሄደውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በመቃወም ህዝቡ ሰላማዊ እንዲወጣ ኢህአዴግ እያስገደደ መሆኑን ፍኖተ ነፃነት ዘገበ ፡፡
ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰልፉ ረቡዕ ሐምሌ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. ጠዋት ላይ እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡ በወረዳው ቀበሌ 05፣06 እና 07 ሰፊ የማስፈራሪያና የቅስቀሳ ስራ እየተካሄደ መሆኑንም ጋዜጣው ዘግቧል፡፡ ጋዜጣው የኢህአዴግ ካድሬዎች ገበሬውን በግድ ከአቅሙ በላይ የዘር ማዳበሪያ ውሰድ እያሉ ከፍተኛ ገንዘብ ከማስከፈላቸው በተጨማሪ ለአማራ ልማት ማኀበር፣ለአባይ፣ ለመሬት ግብር እየተባለ የሚጠየቀው መዋጮ በመብዛቱ ነዋሪዎቹ ከአቅማቸው በላይ መሆኑን ሲናገሩ ...
Read More »በስዊዘርላንድ የተካሄደው በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የስፖርት በአል በተሰካ ሁኔታ ተጠናቀቀ
ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኒዮን የስዊዘርላንድ ከተማ የተካሄደው 11ኛው የአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ቅዳሜ ጁላይ 20 በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል። ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት፣ ከሰሜን አሜሪካ፣ ከኢትዮጵያ እንዲሁም ከተለያዩ አህጉራት የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለበዓሉ ድምቀት አስተዋጽዖ አድርገዋል። ይህ በአውሮፓ የኢትዮጵያውያን ፌስቲቫል ላለፉት 11 ዓመታት በተከታታይ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፣ በአህጉሪቱ የሚገኙና ከሌሎች አህጉራትም ጭምር በመሰባሰብ በርካታ ኢትዮጵያውያን ...
Read More »በቂሊንጦ የሚገኙ እስረኞች በሞት አፋፍ ላይ እንገኛለን አሉ
ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ አቶ ተሻለ በካሻ መዝገብ ተከሰው ከሁለት አመታት በላይ በእስር ቤት የቆዩት እስረኞች ሰሞኑን ከፍተኛ ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ ለተከታታይ ቀናት ምግብ ባለመመገባቸው ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመግለጽ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላቸው አቤት ብለዋል። እስረኞቹ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ከውጭ የመጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በፌሮ ክፉኛ እንደደበደቡዋቸውና ህክምና በማጣታቸው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል። ፍርድ ቤት ...
Read More »ኢህአዴግ አንድነት ፓርቲ የጠራው ሰልፍ እንዳይሳካ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው
ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አንድነት የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በማለት የጠራው ህዝባዊ ንቅናቄ ገዢውን ፓርቲ በማስደንገጡን አዲስ ከጀመራቸው ግምገማዎችና የህብዕ እንቅስቃሴዎች ለመረዳት ተችሎአል። በደሴ እና በጎንደር የተካሄደውን ስላማዊ ሰልፍ ተከትሎ የፖሊስ እና የቀበሌ የፖለቲካ አመራሮች በጠንካራ ግምገማ ተይዘው መሰንበታቸውን ከኢህአዴግ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ስማችን እና ድምጻችን አይተላለፍ ያሉት ምንጮች እንደገለጹት በ1ለ5 አደራጃጀት መሰረት ህዝቡ በሰልፉ ላይ እንዳይገኝ ...
Read More »ኢህአዴግ በልሳናቱና በልማታዊ ባለሃብቶቹ ድጋፍ አትራፊ መሆኑን ገለጸ
ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የግንባሩ 9ኛ ጉባዔ ሪፖርት እንደሚያሳየው በ2003 እና በ2004 ዓ.ም ግንባሩ 88 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን ቀድሞ በባንክ አካውንት ውስጥ ከነበረው ሒሳብ ጋር ሲደመር ገቢው 171 ነጥብ 2 ሚሊየን መድረሱንም ይፋ አድርጓል፡፡ 46 በመቶ የሚሆነው ገቢ የተገኘው ከ“አዲስ ራዕይ” እና “ህዳሴ” ከተሰኙ ሕትመቶች ሽያጭ ነው ፡፡ ቀሪው 54 በመቶ የተገኘው ደግሞ ...
Read More »በባህርዳር ከተማ በሙስሊሞች እና በፖሊስ መካከል ግጭት ተፈጠረ
ሐምሌ ፲፭(አስራ አንድ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህር ዳር ከተማ በህዝበ ሙስሊሙ መካነ መቃብር አጠገብ የሚገኘውን ትንሽ ቦታ መንግስት ሞይንኮ ለተሰኘ የመኪና ጋራጅ ድርጅት አሳልፎ መስጠቱን ተከትሎ የአካባቢው ሙስሊም ባነሳው ተቃውሞ ምክንያት ድርጅቱ ቦታውን እንደማይወስድ እና እንደማይረከብ አስታውቆ ነበር። ትናንት ህዝበ ሙስሊሙ ቦታውን ለማጠር እና አታክልት ለመትከል ሲሰባሰብ የፌደራል ፖሊስ በፍጥነት በመምጣት ያስቆማቸው ሲሆን እርምጃውን ተከትሎ በሙስሊሙ ማህበረሰብ እና በፌደራሎቹ ...
Read More »