የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግብፅ የውኃና መስኖ ሚኒስትር መሐመድ አብዱል ሙታሊብ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ለማድረግ በጠየቁት መሠረት ባለፈው ሰኞ አዲስ አበባ ቢገቡም፣ የዓባይ ግድብ ግንባታ እንዲቆም በመጠየቃቸው ውይይቱ በሰዓታት ውስጥ ተቋረጠ፡፡ ሪፖርተር እንደዘገበው የግብፅ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ አቻቸው አቶ አለማየሁ ተገኑና ከባልደረቦቻቸው፣ እንዲሁም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተወከሉ ባለሙያዎች ጋር ባለፈው ሰኞ ተገናኝተዋል። ይዘዋቸው የመጡት አጀንዳዎችም ...
Read More »Author Archives: Central
የአራጣ ብድር በአስከተለው ቀውስ ከ250 በላይ ነጋዴዎች ተሰደዋል
የካቲት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ቋሪትና ጃቢጠህናን ወረዳዎች ይካሄድ የነበረው መረን የለቀቀ ህገወጥ የአራጣ ብድር ስርዓት በአስከተለው ቀውስ ከ250 በላይ ጠንካራ ነጋዴዎች ተሰደዋል ተባለ፡፡ ከፍተኛ ማታለል የነበረበት ይህ ህገወጥ የአራጣ ብድር ስርዓት ነጋዴዎችን ባዶ ያስቀረና ያሰደደ ከመሆኑ ባለፈ ብዙዎችን ለእብደትና ለቤት መፍረስ ዳርጓል ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉና ከ121 ሺህ ብር በላይ ተወሰደብኝ ያሉ አንድ የገነት ...
Read More »መንግስት በአገሪቱ እየታየ ላለው ረሀብ በቂ ዝግጅት እያደረገ አለመሆኑን መረጃዎች አመለከቱ
የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍተኛ የግብርና ምርት እንደተገኘ በመንግስት የመገናኛ ብዙሀን በሚገለጽበት በአሁኑ ወቅት ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ካላገኙ ህይወታቸው አደጋ ላይ እንደሚወድቅ መረጃዎች አመልከተዋል። የዓለም ባንክ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በመግብ ለስራ የታቀፉ ዜጎችን ሳይጨምር ከ3 ሚሎዮን ያላነሱ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። በምስራቅ አማራ፣ በደቡብ ምስራቅ ትግራይ፣ በአፋር እና ኦሮምያ የተከሰተውን ረሀብ ለማስታገስ ...
Read More »በ500 ብር ደሞዝ የሚተዳደረው የህወሃት ታጋይ ከ10 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ሃብት ማካበቱ ተገለጠ
የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደህንነት ሃላፊ ከነበሩት ከአቶ ወልደስላሴ ወልደ ሚካኤል ጋር በግብረ-አበርነት የተከሰሱት የህወሃት ታጋዮች ከደሞዛቸው ጋር ፈጽሞ የማይመጣጠን ሃብት አግበሰው መገኘታቸው ታውቋል። በተለያዩ አለመግባባቶች የተነሳ እየተመሰረቱ ያሉ ክሶች የህወሃት ተጋዮች በህገወጥ መንገድ የሰበሰቡትን የሃብት መጠን ለማወቅ እየረዳ መሆኑን የገለጸው ዘጋቢያችን ከአቶ ወልደስላሴ ጋር በግብረ አበርነት የተከሰሱት የህወሃት ታጋዩ የአቶ ወልደስላሴ ወንድም አቶ ዘርአይ ወልደስላሴ ...
Read More »አንድ የአየር ሃይል ባልደረባ የአርበኞች ግንባርን ተቀላቀለ
የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የደብረዘይት አየር ኃይል አባል የነበረው ምክትል መቶ አለቃ ዳንኤል የሽዋስ የኢህአዴግን ስርአት በመቃወም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትን መቀላለቀሉን ግንባሩ ለኢሳት በላከው መግለጫ አስታውቋል። ም/መ/አለቃ ዳንኤል የሽዋስ የ L-39 ስኳድሮን ተዋጊ ጀት አብራሪ እንደነበር መረጃው ያመለክታል። ም/መ/አ ዳንኤል የሽዋስ “ተቃዋሚዎችን ትደግፋለህ ከእነሱም ጋር የጠበቀ ግኑኝነት አለህ በሚል ምክንያት ተጠርጥሮ ያለምንም ወንጀል ለአምስት ...
Read More »ተጠልፈው የተወሰዱት ሁለቱ የኦጋዴን ነጻ አውጭ ባለስልጣናት በአንድ ወታደራዊ ሆስፒታል ውስጥ ሲታከሙ መታየታቸውን ግንባሩ ገለጸ
የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግንባሩ ለኢሳት በላከው መረጃ ፣ ከኢህአዴግ መንግስት ጋር ድርድር ለማድረግ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ተገኝተው በኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ታፍነው የተወሰዱት የኦብነግ አመራሮች፣ የደረሰባቸውን ከፍተኛ ድብደባ ተከትሎ በአንድ ወታደራዊ ሆስፒታል ውስጥ ሲታከሙ ታይተዋል። የመንግስት የደህንነት ሰራተኞች ” ባለስልጣኖቹ በገዛ ፈቃዳቸው እጃቸውን እንደሰጡ ለማሳመን ያደረጉት ከፍተኛ ጥረት ባለመሳካቱ አሰቃቂ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው” ግንባሩ አክሎ ገልጿል። ...
Read More »የዩጋንዳ ጦር ደቡብ ሱዳንን ለቆ እንዲወጣ አቶ ሃይለማርያም አስጠነቀቁ
የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚ/ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የዩጋንዳ ጦር በሂደት ለቆ ካልወጣ አካባቢው የጦርነት ቀጠና ሊሆን ይችላል ብለዋል። ሁሉም ሃይሎች የራሳቸው የሆነ ፍላጎት አላቸው ያሉት አቶ ሃይለማርያም፣ በደቡብ ሱዳን ሰላም ይመጣ ዘንድ የዩጋንዳ ጦር ጁባን ለቆ መውጣት አለበት ሲሉ አሳስበዋል ። አቶ ሃይለማርያም የገለጹት አቋም የደቡብ ሱዳንን መንግስት የሚያስከፋ ቢሆንም፣ በሌላ በኩል ግን ለተቀዋሚዎች ...
Read More »በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግሩ እንደተባባሰ ነው
የካቲት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከተማው ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ተሽከርካሪዎች ፣ የግል ባለንብረቶችና ባለታክሲዎች በመላ አገሪቱ የጠፋውን ነዳጅ ተከትሎ ነዳጅ ለማግኘት ላይ ታች እየተንከራተቱ ሲሆን፣ የነዳጅ መጥፋቱን ተከትሎ የትራንስፖርት ታሪፊም ጨምሯል። ዘጋቢያችን እንዳለው ዛሬ ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀስ 0.25 ሳንቲም ተጨማሪ ገንዘብ ለመክፈል ተገዷል፡ ነዳጅ ማደያዎችን ተዘዋውሮ የተመለከተው ዘጋቢያችን፣ በከተማው የሚገኙ ነዳጅ ማደያዎች ናፍጣም ሆነ ቤንዚን በማጠራቀሚያቸው ውስጥ ...
Read More »በአዲስ አበባ በሌሊት የሚጻፉ የተቃውሞ ጽሁፎች ቁጥር እየጨመረ ነው
የካቲት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከታህሳስ ወር 2006 ዓም ጀምሮ በመዲናዋ ሌሊት የሚጻፉ የተቃውሞ ጽሁፎችን ማየት የተለመደ እየሆነ መምጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ትናንት ሌሊት በአስኮ መስመር ጀኔራል ዊንጌት ከሚገኘው አደባባይ ጀምሮ አወሊያ፣ካኦጄጄ፣ አስኮ የሚወስደውን ዋና መንገዱን በመሃል በሚከፍለው እስከ 2.5 ሜትር ቁመት ባለው ግድግዳ ላይ የሙስሊሙን የመብት ጥያቄና የትግል ቀጣይነት የሚያንፀባርቁ ጽሁፎች በተለያዩ ቀለማት ተጽፈው ዛሬ ህዝብ ሲያነባቸው ...
Read More »የሃይማኖት ተቋማትን በሚመለከተው አዋጅ ላይ የሚመክር ስብሰባ በአዋሳ ተጠራ
ጥር ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የተዘጋጀው የእምነት አኩልነትና ተቻችሎ የመኖር የሃይማኖት እሴትን ሊያጎለብት ይችላል የተባለ ረቂቅ አዋጅ ላይ የሚመለከታቸውን ወገኖች ሃሳብ ለማሰባሰብ ከነገ ጥር 30 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ቀናት በአዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ ምንጮቻችን ጠቆሙ። በዚሁ ስብሰባ ላይ በዋንኛነት የሚሳተፉት በአገሪቱ አሉ የሚባሉት 945 ያህል የእምነት ተቋማት መሆናቸውም ታውቆአል፡፡ መንግስት የሙስሊም ማህበረሰብ የመብት ጥያቄ ...
Read More »