Author Archives: Central

የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ የአውሮፕላን ጠለፋ የአለም መነጋገሪያ በመሆን ቀጥሎአል

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር 702 የሆነውን አውሮፕላን በመጥለፍ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ ያሳረፈው ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ እስካሁን ድረስ የጠለፋውን መንስኤና ምክንያት በግልጽ የመናገር እድል ባለማግኘቱ የአለም የመገናኛ ብዙሃን የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው። አንዳንዶች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አስከፊ ጭቆናና ፓይለቱ አውሮፕላኑን እንዲጠልፍ እንዳነሳሳው ሲገልጹ ሌሎች ወገኖች ደግሞ ጥገኝት ለመጠየቅ ተብሎ ከተደረገ ስህተት ...

Read More »

የጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ዘጋቢ አደጋ እንደደረሰበት ተዘገበ

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ ዮሃንስ ገ/እግዚያብሄር ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች በመኪና እንደገጩትና “ገና እንገድልሃለን” የሚል ዛቻ እንደሰነዘሩበት ለፍኖተ ነፃነት መናገሩን ጋዜጣው ዘግቧል። “ጋዜጠኛው ከአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ አያሌው ጋር በፓርቲው ጽ/ቤት ቃለምልልስ አድርጎ ወደ መገናኛ አካባቢ ሲደርስ ኮድ 1 የታርጋ ቁጥር18345 የሆነ ሚኒባስ ታክሲ ሆነ ብሎ አደጋ አድርሶበታል፡፡” ሲል ጋዜጣው ዘግቧል። “ገጭታቸሁኝ ...

Read More »

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ስልጣን ለቀቁ

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦህዴድ ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ፣ ምከር ቤቱ እንዳሰናበታቸው የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። አቶ አለማየሁ መታመማቸው ከተዘገበ የቆየ ቢሆንም እስካሁን ከስልጣን ሳይወርዱ ቆይተው አሁን ለምን ለማንሳት እንደተፈለገ ግልጽ አይደለም። በአፋር በቅርቡ በሚካሄደው የምክር ቤት ስበሰባ ላይ ፕ/ት አሊ ሴሮ ከስልጣን ሊነሱ እንደሚችል ለኢሳት የደረሱ ...

Read More »

የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አውቶቡሶች በቴክኒክ ችግር በየመንገዱ መቆማቸው ቀጥሎአል

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ ይረዳሉ በሚል በብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ተገጣጥመው ወደስራ ከተሰማሩ አውቶቡሶች የቴክኒክ አቁዋማቸው ብቃት መጉዋደልና የመለዋወጫ እጦት ጋር በተያያዘ በየቦታው በብልሽት በመቆማቸው ምክንያት የአዲስአበባ ከተማ የትራንስፖርት እጥረት እንዲባባስ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ተሰምቷል። ከአዲስአበባ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተገኘ መረጃ እንዳመለከተው በአሁኑ ወቅት በኮርፖሬሽኑ ከተገጣጠሙ 500 ገደማ የከተማ አውቶቡሶች ከ110 በላይ ...

Read More »

በቫንኩቨርና ሙኒክ የእርዳታ ገንዘብ ተሰበሰበ

የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፌብሩዋሪ 18//2014 በኤድመንድ ኮሚዩኒቲ ማእከል አዳራሽ በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የቫንኮቨር ነዋሪዎች በመገኘት የገንዘብና የቁሳቁስ እርዳታ አበርክተዋል። የእርዳታ አሰባሳቢው ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት አቶ ደበበ ጉሉ ያቀናበሩት፤ በአረብ አገሮች የተከሰተውን የኢትዮጵያውያን ሰቆቃ የሚያሳዩ የቪዲዮ ቅጂዎች በዝግጅቱ ላይ ለእይታ በመቅረባቸው የወገኖቻቸውን ስቃይ በፊልሙ የተመለከቱ ታዳሚዎች ልባቸው በሀዘን ተነክቶ አንዳንዶች ማምሻውን ...

Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጠለፈበትን ምክንያት ለማወቅ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንደቀጠሉ ነው

የካቲት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ጣሊያን በማምራት ላይ በነበረበት ጊዜ  ረዳት አብራሪው የጉዞውን አቅጣጫ በመቀየር ጄኔቭ አውሮፓላን ማረፊያ በማሳረፍ እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል። የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን የሆኑት ሬድዋን ሁሴን አየር መንገዱ የተጠለፈው ሱዳን በቆመበት ጊዜ በተሳፈሩ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ነው በማለት መጀመሪያ ላይ ለረዩተርስ መግለጫ ቢሰጡም፣ የስዊዘርላንድ ፖሊስ ግን ፈጥኖ ጠላፊው ...

Read More »

በሀገረማርያም ጳጳሱ ለአንድ ሰአት ታግተው ተለቀቁ

የካቲት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአርሴማ ቤተክርስቲያን የውስጥ ችግር ጋር በተያያዘ ከመንግስት ጋር በመሆን የድርጅት ስራ ሰርተዋል ተብለው የተወቀሱት አቡነ ገብርኤል፣ ትናንት ለአንድ ሰአት ያክል ታግተው ተለቀዋል። ህዝብ በመወከል ሲንቀሳቀሱ የነበሩት የአገር ሽማግሌዎች ታስረው በህዝብ ግፊት እንዲፈቱ ከተደረገ በሁዋላ፣ ለችግሩ መፍትሄ ያስገኛል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም፣ ችግሩ እልባት ሳያገኝ ቀርቷል። ጳጳሱ በህዝቡ ከታገቱ በሁዋላ በአገር ሽማግሌዎች ማግባባት ...

Read More »

የቡና ኤክስፖርት ለሙስናና ብልሹ አሰራር ተጋልጧል

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቡናን ኤክስፖርት ከማድረግ ጋር በተያያዘ በክትትልና ቁጥጥር፣ በመረጃ አያያዝ፣ ያለብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ቡናን ወደውጭ ኤክስፖርት ከማድረግ እና በሁሉም አካባቢ የቡና ድርጅቶችን መጋዘኖች ክምችት ቆጠራ በወቅቱ ባለማድረግ ላይ ክፍተቶች እንደሚስተዋሉ የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያጠናው አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ ጥናቱ  ኤክስፖርት በማያደርጉ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ያለመውሰድ፣ በንግድ ፈቃድ ላይ የተጠናከረ ቁጥጥር ያለማድረግ እና ...

Read More »

የጎንደር ከተማ የታክሲ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ መቱ

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታክሲ ሹፌሮች አድማውን የመቱት አዲሱን የትራፊክ የቅጣት ደንብ በመቃወም ነው። በከተማው መሃል ላይ አሽከርካሪዎቹ ተሰብስበው የመኪና ጥሩምባ ማጮሃቸውን የገለጸው የኢሳት ወኪል፣ ከሰአዓታት በሁዋላ ታክሲዎቹ ከአደባባይ ላይ በመሰወራቸው ነዋሪዎች ታክሲዎችን ለማግኘት ሲቸገሩ ታይቷል። የገዢው ፓርቲ ሰዎችና ትራፊኮች፣ በመንገድ ላይ ያገኙትን ታክሲ በማስገደድ ሰዎችን እንዲጭን ለማድረግ ሞክረዋል። ፈቀደኛ ያለሆኑ ሾፌሮች ጥያቄዎች ይቀርቡላቸው ነበር። አዳመው ...

Read More »

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከወረዳ ጀምሮ እስከ ክ/ከተማ ለሚገኙ ሁሉም የጽ/ቤት ኃላፊዎች የጉርሻ ክፍያ እንዲሰጣቸው ፈቀደ፡፡

የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጉርሻ ክፍያው ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ እንዲሰጣቸው ተብሎ የጸደቀበትና የክፍያ ማዘዣው ከከተማ  አስተዳድሩ ለሁሉም ወረዳዎችና ክ/ከተሞች በያዝነው ሳምንት እንደተላለፈላቸው ለማዎቅ ተችሎአል። የጉርሻ ገንዘቡ ከ1 ሺ 700  እስከ 4 ሺ 000 ብር የሚደርስ ሲሆን አገልግሎቱም ለስልክ፣ ለቤት ኪራይ እና ለትራንስፖርት መደጎሚያ ታስቦ የሚሰጥ ነው። ክፍያው በፋይናንስ መክፍያ  ሰነድ ወይም ፔሮል ላይ ሳይቀመጥ ከማንኛውም ...

Read More »