የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዩክሬን የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ አዲስ መንግስት መመስረቱ ያስቆጣት ሩስያ ክሪሚያ የምትባለውን የዩክሬን ግዛት አውሮፕላን ማረፊያን በማቆጣጠር ተጽእኖ ለመፍጠር እየሞከች ነው። በክሪሚያ ግዛት 60 በመቶ የሚሆኑት ሩስያውያን ሲሆን፣ ሩሲያ ዜጎቿ ከጥቃት ለመከላከል በማሰብ የወሰደችው እርምጃ መሆኑን ትናገራለች። የምእራባዊያን አገራትና ጊዜያዊው የዩክሬን መንግስት የሩሲያን እርምጃ ግልጽ ወረራ በማለት አውግዘውታል። የሩሲያው መሪ ቭላድሜር ፑቲን ...
Read More »Author Archives: Central
አቶ አለማየሁ አቶምሳ ከክልሉ ፕሬዚዳንትነትና ከኦሀዴድ ሊቀመንበርነት ለመልቀቅ ደብዳቤ እንዳሰገቡ ተደርጎ በክልሉ መንግስት የተሰጠው መግለጫ ሃሰት ነው ተባለ
የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር በክልሉ ፕሬዚዳንት በአቶ አለማየሁ አቶምሳ ቢሮ ውስጥ የተፈጠረውን ጉዳይ በዝርዝር ለኢሳት አስረድተዋል። አቶ አለማየሁ ከኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ጋር የካቲት 10 ቀን፣ 2006 ዓም በክልሉ ውስጥ ስለሚታየው የመልካም አስተዳደር መበላሸትና የህዝብ ሮሮ፣ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በመጣው ሙስና እንዲሁም በድርጅቱ ጎጠኛ አሰራር ዙሪያ እርሳቸውን ከሚቃወሙዋቸው ሌሎች ...
Read More »ኢህአዴግ የሚያካሂደው የቤት ልማት ለኪራይ ሰብሳቢነት መጋለጡን አመነ
የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት 10 ዓመታት ሲካሄደው የቆየውና የቤት ልማት ፕሮግራሙ ለኪራይ ሰብሳቢነትና ብልሹ አሰራሮች የተጋለጠ እንደነበር ኢህአዴግ “አዲስ ራዕይ” በተሰኘ ልሳኑ አምኗል፡፡አዲስ ራዕይ በህዳር – ታህሳስ 2006 ዕትም “የመኖሪያ ቤት ፖሊሲያችንና ለዜጎች የሀብት ክፍፍል ፋይዳው” በሚል ርእስ ባሰፈረው ሐተታ “እስከአሁን በነበረው የቤት ልማታችን ሂደት የተፈጠሩ ክፍተቶች አሉ” ብሏል፡፡ ክፍተቶቹን ሲዘረዝርም “በክልል ከተሞቻችን ቀደም ሲል ...
Read More »አንድነት ፓርቲ ተቃውሞውን በሁሉም የአገሪቱ ክፍል እንደሚያቀጣጥል ገለጸ
የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፣ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) በባህርዳር ለታየው ህዝባዊ ተቃውሞ መልስ ለመስጠት ዝግጁ ባለመሆኑ ተቃውሞውን በሌሎች የአገሪቱ ክልሎች ለመቀጠል ፍላጎት ያለው መሆኑን አመልክቷል። አቶ አለምነው መኮንንን በፍርድ አደባባይ ለማቆም በአጭር ጊዜ ውስጥ ክስ መስርቶ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል። አቶ አለምነው በአማራው ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ጸያፍ ስድብ ተከትሎ በባህርዳር ልዩ የተባለ ...
Read More »በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የውጭ ምንዛሬ እጥረት እልባት አላገኘም
የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአስመጭና ላኪ እንዲሁም በግንባታ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች እንደሚገልጹት፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ የአገሪቱ የንግድ እንቅስቃሴ በእጅጉ እየተጎዳ ነው። ምንም እንኳ መንግስት የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዳላጋጠመ በተደጋጋሚ ቢገልጽም፣ በርካታ ነጋዴዎች ወደ ባንኮች ሲሄዱ፣ የሚፈልጉትን መጠን የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት አይችሉም። ከባንኮቹ የሚሰጣቸው መልስ ምንዛሬ የለም የሚል መሆኑን አንዳንድ ነጋዴዎች እንደሚናገሩ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ...
Read More »በሞቃዲሹ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት ደረሰ
የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አልሸባብ እንዳደረሰው በሚገመተው የአጥፍቶ መጥፋት እርምጃ 12 የጸጥታ ሃኢሎች መገደላቸው ታውቋል። ጥቃቱ የጸጥታ ሃይሎችን ኢላማ ያደረገ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል። ባለፈው ሳምንት በፕሬዚዳንቱ ግቢ ውስጥ በደረሰ ጥቃት የሶማሊያ መንግስት ነባር የአመራር አባላት መገደላቸው ይታወሳል። አልሸባብ ከአፍሪካ አገራት በደረሰበት ጥቃት ሞቃዲሹን ለቆ ቢወጣም፣ በተደጋጋሚ እየወሰደ ባለው የፈንጅ ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ ነው።
Read More »ብአዴን ባህርዳር ላይ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ እንዳይሳካ ለማድረግ የቀየሰው ስትራቴጂ ሳይሳካ መቅረቱን የውስጥ ምንጮች ገልጹ
የካቲት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አለምነው መኮንን የአማራን ህዝብ መዝለፋቸውን ተከትሎ አንድነት ፓርቲና መኢአድ የጠሩተን ሰልፍ ለማደናቀፍና ህዝብ በሰልፉ ላይ እንዳይገኝ የተቀየሰው ስትራቴጂ ሳይሳካ መቅረቱን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ለኢሳት ገልጸዋል። በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የሚገኘው ብአዴን ሰላማዊ ሰልፉን ለማጨናገፍ ከተጠቀመባቸው ዘዴዎች አንዱ በአንጻራዊነት የተሻለ ተሰሚነት ያላቸውን ወደ አዲስ አበባ ከመጡት የክልሉን ተወላጅ የብአዴን ከፍተኛ አመራሮችን መካከል ...
Read More »በኦሮምያ የክልል ፐሬዚዳንት ለመሾም የሚደረገው ሽኩቻ ቀጥሎአል
የካቲት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ ምክር ቤት ሳያቀውቀው በስራ አስፈጻሚው እውቅና ከስልጣን የተነሱትን አቶ አለማየሁ አቶምሳን ማን ይተካቸው የሚለው አጀንዳ የአቶ አባ ዱላ ገመዳንና የአቶ አለማየሁ አቶምሳን ቡድኖች እያወዛገበ ነው። አቶ አለማየሁ አቶምሳ ወደ ስልጣን እንደመጡ የአቶ አባዱላን ቡድኖች በመምታት ከስልጣን ውጭ ያደረጉዋቸው ሲሆን፣ አባ ዱላ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ተመልሰው የእርሳቸውን ሰዎች ለማሾም እየሰሩ ነው። ...
Read More »የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ( ኢንሳ) ለተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችን የኢንፎርሜሽን መረቦችን የመሰረተልማት እንደሚዘረጋ ታወቀ
የካቲት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎችን የኢሜል መልእከቶች እና ሌሎችንም የመገናኛ ዘዴዎች በመሰለል ክስ እየቀረበበት የሚገኘው የኢትዮጵያ የመረጃ ደህንነት ኤጀንሲ ( ኢንሳ) ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችን ጋር ውል በመዋዋል የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እያካሄ ነው። ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ ጋር የ70 ሚሊዮን ብር የኢንፎርሜሽን የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ውል ተዋውሎ ስራ በመስራት ላይ ሲሆን፣ በአዋሳና ሌሎችም ...
Read More »የአዲስአበባ የ24 ሰዓታት የቴሌቭዥን ስርጭት እቅድ ተግባራዊ መሆን አልቻለም
የካቲት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የመገናና ብዙሃን ኤጀንሲ የመረጃ ውጤቶችን ለሕዝብ ተደራሽ ያደርግልኛል በሚል ከፍተኛ በጀት በመመደብ ባለፉት ዓመታት በአዲስአበባ ማዘጋጃ ቤት ሕንጻ ውስጥ ዘመናዊ ስቱዲዮና መሳሪዎች ግንባታና ግዥ ቢያከናውንም የ24 ሰዓታት ቴሌቪዥን አገልግሎት ዕቅዱን በአቅም ማነስ ምክንያት ማሳካት ሳይችል ቀርቷል፡፡ የኦሮሚያ፣ የአማራ እንዲሁም የሶማሌ ክልሎች በዓረብ ሳተላይት ላይ ጭምር የክልሎቻቸውን ዜናዎችና መረጃዎች ...
Read More »