Author Archives: Central

የኢህአዴግ አባላት በድርጅታቸው ላይ  ጥያቄዎችን ማንሳት ቀጥለዋል

ነሃሴ ፳፱(ሃያዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለከተሞች በመካሄድ ላይ ባለው የኢህአዴግ አባላት ስብሰባ ፣ አባላቱ ዛሬም በርካታ ጥያቄዎችን ሲጠይቁ መዋላቸውን ከውስጥ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአባላቱ ከተነሱት ጥያቄዎች  መካከል፡- ” የኢትዮጵና የኤርትራ ህዝቦች የማይነጣጠሉ የአንድ ሃገር ዜጎች ሆነው ሳለ በመሪዎች አለመግባባትና ሽኩቻ በመለያየታቸው እስከዛሬ ድረስ እየተላቀሱ ይገኛሉ፤ ይህም የሆነው በኢህአዴግም አስተዋፆ ጭምር ነው፤ አሁንም ...

Read More »

አብርሃ ደስታ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀበት

ነሃሴ ፳፱(ሃያዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው  ነሃሴ 29/2006 ዓ.ምበአራዳችሎትየቀረበው የአረና ፓርቲ የአመራር አባልና ታዋቂ ጸሃፊ መምህር አብርሃደስታ ፣ ፖሊስ ‹‹ተጨማሪሰነድለማሰባሰብናምስክሮችለማቅረብ” የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው በመጠየቁ ፣ ፍርድ ቤቱ ለመስከረም 22 ቀጠሮ ሰጥቷል። የኢምባሲናሌሎችተወካዮችንጨምሮበርከትያለህዝብየተገኘሲሆንአብርሃደስታከማዕከላዊወደችሎቱበሚመጣበት ጊዜህዝቡደመቅባለ ጭበጭባእንደተቀበለው ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡ህዝቡለአብርሃያደረገውንጭብጨባተከትሎምፖሊስህዝቡከግቢውእንዲወጣቢያስገድድምህዝቡ ሳይወጣ መቅረቱንም አክሎ ዘግባል። የአብርሃደስታጠበቃ  የሆኑት አቶ ተማምአባቡልጉከደንበኛቸውጋርበ28 ቀናትውስጥአንድቀንብቻ እንዳገኙት የነገረ ኢትዮጵያ ዘገባ ያመለክታል። ሀብታሙ አያሌው፣ የሽዋስ አሰፋና ዳንኤል ሽበሺም ተጨማሪ ...

Read More »

የኢህአዴግ አባላት የድርጅታቸውን መሪዎች በጥያቄዎች ሲያፋጥጡ መዋላቸውን ምንጮች ገለጹ

ነሃሴ ፳፰(ሃያስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ በአዲስ አበባ የሚገኙ መላ አባላቱን ለስልጠና ምቹ የሆኑ አዳራሾች ባሉዋቸው ትምህርት ቤቶች እና የመንግስት ተቋማት ከትናንት ጀምሮ በፕላዝማ የታጀበ ስልጠና እየሰጠ ነው። ስልጠናው በመላው አገሪቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያነሱዋቸው አፍራሽ የተባሉ ጥያቄዎች እና አመለካከቶች ወደ ህዝቡ ወርደው አደጋ ከመፍጠራቸው በፊት የኢህአዴግ አባላት እንዴት እንደሚከላከሉዋቸው ስልጠና ለመስጠት ያለመ ቢሆንም፣ የድርጅቱ አባላት ግን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያነሱዋቸውን ...

Read More »

የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት አርባምንጭ መግባታቸውን ተከትሎ ወጣቶች እየታፈሱ ነው

ነሃሴ ፳፰(ሃያስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፊታችን ቅዳሜ የሚከበረውን የአርባምንጭ የ50ኛ አመት የምስረታ በአልን የማጠቃለያ ዝግጅት ለመካፈል ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት የተገኙ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ በከተማዋ ረብሻ ሊያስነሱ ይችላሉ የተባሉ ወጣቶች እየታደኑ ነው። ዘጋቢያችን እንደገለጸው፣ ከ3 ቀናት በፊት እናቶች በየቀበሌው እየተጠሩ ልጆቻቸውን እንዲሰበስቡ ተነግሮአቸው ነበር። ማንኛውም ወጣት በምሽት ከተማ ውስጥ መዘዋወር፣ ሰብሰብ ብሎ መቆም እንዳይችል እየተደረገ ነው። ...

Read More »

የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ መሪውን ከሃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ

ነሃሴ ፳፰(ሃያስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ  “ኮ/ል አለበል አማረ የድርጅቱ መስራችና ሊቀመንበር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን፣ ውጭ አገር ከሄዱም በሁዋላ ድርጀቱን በማጠናከር ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን” ካወሳ በሁዋላ፣ ድርጅቱ መስዋትነት እየከፈለበት ያለው የነጻነት ትግል በቶሎ ግቡን እንዲመታ መሬት ላይ ወርዶ መታገሉ የበለጠ ውጤታማ ያደርገዋል ተብሎ ስላሚታመን  በተደጋጋሚ እንዲመጡ ቢነገራቸው ሊመጡ ባለመቻላቸውና አሁን ባለንበት ጊዜ ድርጅቱን ውጭ ሃገር ...

Read More »

አገር አቀፉ የኪነጥበብ ሽልማት ፕሮግራም ተሰረዘ

ነሃሴ ፳፰(ሃያስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጳጉሜ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊያካሂደው የነበረው የኪነጥበብ ሽልማት  አርቲስቶች ከፍተኛ ቅሬታ ከማቅረባቸው ጋር ተያይዞ እንዲሰረዝ መወሰኑ ተሰማ፡፡ ሚኒስቴሩ ኪነጥበብን ለማበረታታት በሚል በሥነጹሁፍ፣ በሥዕል፣በሙዚቃ እና በፊልም ዘርፎች ብቻ የየዘርፎቹ ማህበራት መርጠው የላኩዋቸውን 10፣ በድምሩ 40 ዕጩዎች በማወዳደር ከየዘርፉ የተሻለ ውጤት ያገኘውን ለመሸለም አቅዶ እየተንቀሳቀሰ የነበረ ቢሆንም ምርጫው ኢ-ፍትሐዊ ...

Read More »

በእስር ላይ የሚገኙት የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው

ነሃሴ ፳፯(ሃያ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሃብታሙ አያሌው፣ የድርጅቱ ም/ል የድርጅት ጉዳይ ሃለፊ ዳንኤል ሽበሺ፣ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት/ምክትል ሰብሳቢ የሺዋስ አሰፋ ከሰአት በሁዋላ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበረ ቢሆንም፣ ፖሊስ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ በሚል የጊዜ ቀጠሮ በመጠየቁ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል። የእስረኞችን ጉዳይ የሚከታተሉት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ፖሊስ እስካሁን ...

Read More »

ኢህአዴግ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ለሰራተኞች የሚሰጠውን ስልጠና ለማስቀጠል አቅዷል

ነሃሴ ፳፯(ሃያሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለሁለት ሣምንታት ለዩኒቨርሲቲ አዲስና ነባር ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው የመጀመሪያ ዙር አስገዳጅ ሥልጠና የፊታችን ቅዳሜ የሚጠናቀቅ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ሥልጠና ወዲያውኑ ለመቀጠል ትምህርት ሚኒስቴር መዘጋጀቱን መረጃዎች ጠቁመዋል። ተማሪዎችተገድደውበገቡበትበዚሁየሥልጠናቆይታቸውደስተኛያለመሆናቸውንበመናገርላይናቸው፡፡ በዋነኛነት የመንግሥት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ለተማሪዎች ለማስተዋወቅ በሚል በመንግሥት ከፍተኛ በጀት ከ33 በላይ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጠው በዚሁ ሥልጠና ላይ የኢህአዴግ ዋና ዋና ካድሬዎች በአሰልጣኝነት የግንባሩን ርዕዮተ ዓለም ለማስተዋወቅና ...

Read More »

ተማሪዎች ዘንድሮም ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በግዴታ እንዲከፍሉ ታዘዙ

ነሃሴ ፳፯(ሃያሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጪውን የትምህርት ዘመን ለመጀመር የሚያስችል ምዝገባ ለማካሄድ በትምህርት ቤቶች የተገኙ ተማሪዎች ለአባይ ግድብ ገንዘብ የማያዋጡ ከሆነ እንደማይመዘገቡ ተገልጸላቸዋል። ተማሪዎቹ በነፍስ ወከፍ 120 ብር የማይከፍሉ ከሆነ ምዝገባ እንደማያካሂዱ እንደተነገራቸው ለኢሳት እንደተነገራቸው ገልጸዋል። ሁለት እና ከዚያ በላይ  ልጆች ያላቸው ወላጆች በቤተሰብ ደረጃ ሳይሆን በእያንዳንዱ ልጅ ስም የመክፈል ግዴታ ተጥሎባቸዋል። አንዳንድ ተማሪዎች በእያመቱ ለአባይ ግድብ እየተባለ የምንከፍለው ...

Read More »

የአማራ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን በኪራይ ሰብሳቢነት መሸነፉን አመነ፡፡

ነሃሴ ፳፯(ሃያሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአማራ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን  ኪራይ ሰብሳቢዎች በባለሃብቱ እና በመስሪያ ቤቱ መካከል በመግባት ከፍተኛ ብዝበዛ እየፈጠሩ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡ ሰኞ ነሃሴ 19/2006 ዓ.ም የመስሪያ ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ስማቸው ንጋቱ በሰጡት መግለጫ የመስሪያቤቱ ወሳኝ ሰራተኞች ከደላሎች ጋር በፈጠሩት የረዢም ጊዜ ቁርኝት እያንዳንዱ ጨረታ ህጉን በተከተለ መንገድ ለመስራት አስቸግሮ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ በአመትእስከ 300 ሚሊዮን ብር ድረስ ...

Read More »