መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አብዲ ሙሃመድ 7 የስራ አስፈጻሚ የኮሚቴ አባላትን ማበረራቸውን ተከትሎ ወደ አዲስ አበባ በአስቸኳይ እንዲመጡ ቢታዘዙም፣ የቀረበላቸውን ጥሪ ባለመቀበል ጅጅጋ ውስጥ እንደሚገኙ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምንጮች ተናግረዋል። ለአቶ አብዲ ቅርበት ያላቸው የመከላከያ ባለስልጣኖች በተደጋጋሚ ስልኮችን በመደወል አቶ አብዲን ለማግባባት እየሞከሩ ሲሆን አቶ አብዲ በበኩላቸው ” ኢትዮጵያ ውስጥ 30 መንግስት ነው ያለው እንዴ?” በማለት ...
Read More »Author Archives: Central
የመምህራንና የተማሪዎች ስልጠና በልዩነት እንደቀጠለ ነው
መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለሁለተኛ ዙር እየተካሄደ ያለው የኢህአዴግ ስልጠና በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች በአለመግባባት ሲቀጥል፣ በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ ተማሪዎች በመሰላቸት ውይይቶችን እንደማይከታተሉ ከተሳታፊዎች የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። የተለያዩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ውይይቱ አሰልቺ በመሆኑ አብዛኛው ተማሪ የግሉን ስራ እንደሚሰራና ውይይቱን እንደማይከታተል ገልጸዋል። ለመምህራን በሚሰጠው ስልጠና ደግሞ በአንዳንድ የማሰልጠኛ ቦታዎች መምህራን ሃሳብ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አሰልጣኞች ግፊት ...
Read More »አቶ የሽዋስ አሰፋ የርሃብ አድማ አደረገ
መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማዕከላዊ ምርመራ ታስሮ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ የአራት ቀን የርሃብ አድማ ማድረጉን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። አቶ የሸዋስ ከጳጉሜ 4 ጀምሮ አዲሱን አመት በርሃብ አድማ ያሳለፈ ሲሆን ቅዳሜ መስከረም 3/2007 ዓ.ም ምግብ እንደቀመሰ ባለቤቱ ወይዘሮ ሙሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻለች፡፡ አቶ የሽዋስ የርሃብ አድማ ያደረገው ከታሰረበት ሐምሌ 1/2006 ዓ.ም ...
Read More »የአዳማ ምክትል ከንቲባ ከአገር እንዳይወጡ ታገዱ
መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሶስት ሳምንት በፊት ለአጭር ቀን ስልጠና ወደ አሜሪካ ለመብረር ዝግጅታቸውን ጨርሰው ቦሌ አየር ማረፊያ የተገኙት ምክትል ከንቲባው፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በሚል ከአገር እንዳይወጡ ተደርጓል። ዋናው ከንቲባና አንድ ባለሙያ ስልጠናውን ተካፍለው መመለሳቸው ታውቋል። ምክትል ከንቲባው የእስልምና እምነት ተከታይ እና በኦነግ አባልነት እንደሚጠረጠሩ ምንጮች ገልጸዋል። በከንቲባውና በምክትሉ መካከል የተፈጠረው ልዩነት እየሰፋ መምጣቱም ይነገራል። ምንጮች እንደሚሉት ...
Read More »በሞያሌ ለተነሳው ግጭት ተጠያቂ የተደረጉ ተፈረደባቸው
መስከረም ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሁለት አመት በኦሮምያና በሶማሊ ክልሎች የድንበር ከተሞች የተነሳውን ግጭት መርተዋል የተባሉና ቁጥራቸው በውል ላልታወቀ ዜጎች ሞትና ለንብረት መውደም ምክንያት ሆነዋል የተባሉ የሞያሌ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ ሌሎች 29 ሰዎች እስከ 19 አመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል። 21 ተከሳሾች በሌሉበት ሲወሰንባቸው የሞያሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጉዩ ዋርየን በ14 አመት፣ ዳማ ዱዮን የተባሉት ደግሞ ...
Read More »በ 2007 ዓ.ም ለሚደረገው ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሚሊሻዎች ልዩ ተልዕኮ እንደተሰጣቸው ተገለጸ
መስከረም ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2007ዓ.ም ለሚደረገው ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ ህብረተሰቡ ለተለያዩ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ድምፁን እንዳይሰጥ ለማፈን በሚያስችል ሁኔታ በክልሉ የሚገኙ ሚሊሻዎች ልዩ ተልዕኮ እንደተሰጣቸው ተገለጸ የአማራ ብሄራዊ ክልል መንግስት ሚሊሽያ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መኳንንት መልካሙ ሰሞኑን ለታማኝ አመራሮች በሰጡት ድርጅታዊ መግለጫ ላይ በያዝነው ዓመት በሚካሄደው ምርጫ ህዝቡ የተለያየ ፅንፍ በመያዝ ገዢው ፓርቲ ላይ ስጋት የሚፈጥሩ ...
Read More »የተከፋፈሉት የሶማሊ ክልል ስራ አስፈጻሚ አባላት አንዱ ሌላውን ከስልጣን ማገዳቸውን አስታወቁ
መስከረም ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሁለት ሳምንት በፊት በጠ/ሚንስትር ጽ/ቤት የሶማሊ ክልል መሪዎች፣ የደህንነት ሃላፊዎችና በክልሉ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች በተገኙበት በተደረገው ግምገማ በፕሬዚዳንቱ አብዲ ሙሃመድ ላይ በርካታ ወንጀሎች ተዘርዝረው ከቀረቡ በሁዋላ ፣ ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ለማውረድ በሚፈልጉት የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋና በክልሉ የመከላከያ ሹም ጄኔራል አብርሃ መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል። ውሳኔ ለመስጠት የተቸገሩት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ፣ ግምገማው ...
Read More »ባለፈው አመት በርካታ የመካላከያ ሰራዊት አባላት መልቀቃቸውን ወታደሮች ገልጹ
መስከረም ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ጳጉሜ ወር የመከላከያ ሰራዊትን ጥለው የጠፉ ወታደሮች ለኢሳት እንደገለጹት፣ በጠጠናቀቀው አመት በርካታ ወታደሮች እየለቀቁ የተቃዋሚ ድርጀቶችን ከመልቀቅ ባሻገር ወደ ማሃል አገር እየሄዱ ኑሮአቸውን እየመሩ ነው። የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ትወስዳለህ ተብሎ ያለፍለጎቱ መከላከያን የተቀላቀለና ባለፈው ሳምንት መስሪያ ቤቱን በመልቀቅ የግል ኑሮውን ለመምራት የፈለገ ወታደር እርሱ በነበረበት የሁመራ እና በአድሜ አካካቢዎች በሰራዊቱ ላይ ...
Read More »በጋምቤላ የተነሳውን ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል
መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመዠንገር ብሄረሰብ ተወላጆች ጎደሬና ሜጫ በሚባሉት አካባቢዎች እንደ አዲስ በጀመሩት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና እስካሁን አስከሬኖች እንዳልተነሱ የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። ከጋምቤላ ብሄረሰብ ውጭ ያሉ የሌሎች አካባቢ ተወላጆች በሙሉ ይወጡ በሚል የተጀመረው ግጭት ፣ ደም አፋሳሽ ሆኖ ከመቀጠሉ ባሻጋር፣ በትናንትናው እላት ብቻ ከ1 ሺ ያላነሱ ሰዎች ተፈናቅለው ቴፒ ከተማ መግባታቸው ታውቋል። ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች እንደሚሉት ...
Read More »በሽብርተኝነት የተከሰሱት አርባ ምንጭ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ወደ ማእከላዊ እስር ቤት ተወሰዱ
መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፯ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ሆነው ለግንቦት7 የአርባ ምንጭና አካባቢው ወጣቶችን በመመልመል ወደ ኤርትራ ይልካሉ በሚል ጥርጣሬ ተይዘው ለሳምንታት በአርባ ምንጭ እስር ቤት ታስረው የቆዩት የፓርቲው የአርባ ማንጭ ምክትል ሰብሳቢ በፍቃዱ አበበ እንዲሁም የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ኢንጂነር ጌታሁን ወደ ማእከላዊ እስር ቤት መወሰዳቸውን የፓርቲው ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለኢሳት ገልጸዋል። ኢንጂነር ጌታሁን በየነ ቀደም ብሎ ...
Read More »