Author Archives: Central

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለአዳር የሚቆይ ተቃውሞ በመስቀል አደባባይ ለማካሄድ የእውቅና ጥያቄ አቀረበ

ኀዳር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትብብሩ ህዳር 18 ለመስተዳድሩ ባስገባው የእውቅና ጥያቄ ፣ የተቃውሞ ሰልፉን በመስቀል አደባባይ ከህዳር 27 እስከ ህዳር 28፣ 2007 ዓም ለማካሄድ ማቀዱን ገልጿል። የእውቅና ደብዳቤውን ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲና የትብብሩ ሊቀመንበር፣ የከንባታ ህዝቦች ሊቀመንበርና የትብብብሩ ም/ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርጌሎ፣ አቶ ግርማ በቀለ ከኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅትና የትብብሩ ፀኃፊ እና የመኢዴፓ ሊቀመንበርና ...

Read More »

አንድ የአርበኞች ግንባር አባል በእስር መቀጣቱ

ኀዳር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርበኛ ጋሻው ሽባባው በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ ወረዳ ከመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ጋር ለ4 ወራት ሲፋለም በቁጥጥር ስር መዋሉን ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት የገለጸ ሲሆን፣ በዚህም ድርጊቱ የ4 አመት ከ8 ወር እስራት እንደፈረደበት ገልጿል። አርበኞች ግንባር በወቅቱ ባደረገው ተደጋጋሚ ጥቃት ከ60 ያላነሱ የመንግስት ወታደሮችን መግደሉን አስታውቆ ነበር። መንግስት ምንም አይነት ...

Read More »

በምእራብ አርማጭሆ ወጣቶች የጸረሰላም ሃይሎች መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተነገራቸው

ኀዳር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የብአዴን አመራሮች ሰሞኑን በዞኑ ባካሄዱት የወጣቶችና ሴቶች ጉባኤ ላይ ፣ የአካባቢው ወጣቶች የጸረ ሰላም ሃይሎች መሳሪያ ከመሆን እን  ዲቆጠቡ ጠይቀዋል። ወጣቶቹ በግፍ የታሰሩ የአካባቢው የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የሆኑት አንጋው ተገኝ፣ አባይ ዘውዱና ሌሎችም አባላት ታፍነው መወሰዳቸውን ተቃውመዋል። በተለይ የጋብላ እና የዘመነ መሬቅ ወጣቶች እውን ዲሞክራሲ የሚባለው በዚህ አገር አለ ወይ በማለት ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲን ያቀፈው የ9 ፓርቲዎች ትብብር በመንግስት አፈና ትግሉን እንደማያቆም አስታወቀ

ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትብብሩ ባወጣው መግለጫ ህዳር 21 ለሚደረገው ስብሰባ ለመስተዳድሩ የሰለማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ ቢላክለትም ለመቀበል ፈቃደኛ ካለመሆኑም በተጨማሪ፣ ስብሰባውን የሚያስተባብሩት የመኢዴፓ ሊቀመንበርና የትብብሩ ገንዘብ ያዥ የሆኑት አቶ ኑሪ ሙደሲር ላይ የድብደባ ወንጀል እንደተፈጸመባቸው ገልጿል።‹‹ነጻነታችን በእጃችን›› ነው የሚለው ትብብሩ፣  በኢህገመንግሥታዊና ኢዲሞክራሲያዊ እርምጃዎች ወደኋላ እቅዱን በህጋዊ መንገድ ለማስቀጠል እስከ ህይወት መስዋትነት ለመክፈል ...

Read More »

ኢትዮጵያ ከአለማቀፍ የገንዘብ ገበያ ለመበደር ድርድር ጀመረች

ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት የጀመራቸውን የሃይል፣ የመንገድ፣ የባቡርና የስኳር ፋብሪካዎችን ለመጨረስ የሚያስችለውን ገንዘብ ከአለማቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ለመበደር የሚያስችለውን ድርድር ከሁለት የአውሮፓ እና ከአንድ የአሜሪካ ባንክ ጋር ጀምሯል። መንግስት ገንዘቡን ለመበደር የሚያስችለውን ቦንድ ለገበያ የሚያቀርብ ሲሆን፣ አለማቀፍ አበዳሪ ተቋማትም የመንግስትን የመክፈል አቅም በማየት ብድሩን ይፈቅዳሉ። መንግስት ከአለማቀፍ የግል አበዳሪ ድርጅቶች ገንዘብ ለመበደር ወደ አለማቀፍ የካፒታል ...

Read More »

የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት በተቀናጀ የከተማ ፕላን ላይ የመስተዳድሩን ሰራተኞች ሊያሰለጥን ነው

ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ከላከው ቅጽ ለመረዳት እንደሚቻለው ፓርቲው በአዲስ አበባና ኦሮምያ የተቀናጀ የከተማ እቅድ ዙሪያ በመንግስት ሰራተኛው ውስጥ ያለውን የአመለካከት ክፍተት ለመሙላት ስልጠና ይዘጋጃል። ፓርቲው የተለያዩ ቅጾችን ለሰራተኛው በመበተን ሰራተኛው እስካሁን ስለነበሩት ክንውኖችና ድክመቶች አስተያየቱን እንዲጽፍ ተጠይቋል። እጅግ አወዛጋቢ ሆኖ ተቃውሞ ያስነሳውንና በርካታ ሰዎች የሞቱበትን የአዲስ አበባ አዲስ ...

Read More »

130 የግል ትምህርት ቤቶች ክስ ተመሰረተባቸው

ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ ከተማ የተጋነነ የትምህርት ቤት ክፍያ ዋጋ በመጨመር ህብረተሰቡን ለአላስፈላጊ ወጪ ዳርገዋል በተባሉ 130 የግል ትምህርት ቤቶች ላይ ክስ መመስረቱን የአዲስአበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን እና የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር በጋራ ያጠኑትና በሐምሌ ወር 2006 ዓ.ም ይፋ የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው በአዲስአበባ በግል ት/ቤቶች የአንድ ተማሪ ክፍያ ...

Read More »

በኮምቦልቻ ከተማ በመጠጥ ውሃ ታሪፍ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ሊደረግ ነው

ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ካቢኔ የከተማዋ ነዋሪዎች ጭማሪው እንዲከፍሉ የወሰነው ለከተማው ውሃ ለመዘርጋት ከፍተኛ ገንዘብ ማውጣቱን በመግለጽ ነው። የክልሉ የውሃ ሀብት ም/ል ሃላፊ ለክልሉ ካቢኔ እንደገለጹት ለከተማዋ የውሃ መስመር ዝርግታ 6 ሚሊዮን 300 መቶ ሺ ብር ለማስፋፊያ ስራ ደግሞ 60 ሚሊዮን ብር በመውጣቱ፣ አጠቃላይ ወጪውን ለማስመለስ ተጠቃሚው ህብረተሰብና የንግድ ተቋማት ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍሉ ባቀረቡት ...

Read More »

በአዊ ዞን  የኢህአዴግን የአባልነት ፎርም አንሞላም ያሉ ተማሪዎች ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

ኀዳር ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዊ ዞን አንከሻ ወረዳ ውስጥ የሚማሩ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች የኢህአዴግን የአባልነት መሙያ ፎርም ወስደው እንዲመዘገቡ በርእሰ መምህራቸው አማካኝነት ቢጠየቁም፣ ከ700 ያላነሱ ተማሪዎች ድርጊቱን ተቃውመዋል። ተማሪዎቹ የአባልነት ቅጹን በሁለት ቀናት ውስጥ የማይሞሉ ከሆነ ከትምህርት ቤት እንደሚባረሩና ለፈተናም እንደማይቀርቡ ተነግሯቸዋል። “ከእንግዲህ ኢህአዴግ የሚባል ነገር ማየት አንፈልግም” ያሉት ተማሪዎች ፣ በትምህርት ቤት አስተዳደሪዎች የቀረበላቸውን ...

Read More »

በአማራ ክልል ቅርሶች በከፍተኛ ሁኔታ እየዘረፉ ከሐገር እየወጡ ነው፡፡

ኀዳር ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል የደቡብ ወሎና የሰሜን ሸዋ ዞን ወረዳዎችና አብያተክርስቲያናት ተገቢ ጥበቃ ባለማግኘታቸው የተለያዩ ቅርሶች የተዘረፉና የጠፉ መሆኑን የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ በአመት አንድ ጊዜ በሚዘጋጀው የቅርስ ጉባኤ ላይ ገለጸ፡፡ በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በተለያዩ ወረዳዎች 37 ቅርሶች መሰረቃቸውን ይፋ ያደረጉት የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ አለበል ደሴ  ፣በክልሉ ከ2001 በጀት ዓመት ...

Read More »