Author Archives: Central

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ጀርመን አቀኑ

ኀዳር ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትሩ አገሪቱ ከግል የገንዘብ ተቋማት ለመበደር መወሰኑዋን ተከትሎ የኢትዮጵያን ብድር በበላይነት በሚያስተባብረው በጀርመን ትልቁ ባንክ አማካኝነት በተዘጋጀ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ ተብሎአል። ኢትዮጵያ ከአለማቀፍ ገንዘብ ተቋማት ለመበደር መወሰኑዋ ብዙ ኢኮኖሚስቶችን እያነጋገረ ነው። ጠ/ሚኒስትሩ ከጀርመን ቻንስለር አንግላ መርክል ጋር እንደሚነጋገሩም ታውቋል። አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ቀደም ለኢትዮጵያ ማዳበሪያ ከሚያቀርብ አራ ከተባለ የማዳባሪያ ድርጅት የግብርና ...

Read More »

ህጋዊ ተቃዋሚዎችን በአክራሪነት ሰበብ ለመምታት የሚያስችሉ ሃሳቦች ቀረቡ

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃገሪቱ ህገ መንግስት አንቀጽ 31 መሰረት በህጋዊ መልኩ ተመዝግበው ሰላማዊ የፖለቲካ እንቃስቃሴ የሚያደርጉ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን በሽብርተኝነት እና ጽንፈኝነት በመፈረጅ የጥቃት ኢላማ ለማድረግ መታሰቡን ኢሳት የፌደራል መንግስት የጸጥታ ጉዳዮች ሰሞኑን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር  ካካሄደው ውይይት ለመረዳት ተችሎአል፡፡ የትግራይ፣ቤንሻንጉል ጉሙዝና አማራ ክልል ሃላፊዎች ሰማያዊ ፣አንድነትና መኢአድ ፓርቲዎች ጽንፈኞች በመሆናቸው በአክራሪነት ሲሳተፉ የነበሩ ወጣቶችን በማሰባሰብ ...

Read More »

ዘጠኙ ፓርቲዎች የህዳር 27 እና 28 የተቃውሞ ሰልፉን እንደሚያካሂዱ አስታወቁ

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን፣ ፓርቲዎቹ ይህን አስታወቁት ባወጡት መግለጫ ነው። ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ደብዳቤ ለመቀበል አሻፈረን ሲል የነበረው መስተዳድሩ በፖስታ የተላከለትን ደብዳቤ ከተቀበለ በሁዋላ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ ቁጥር 3/1983 ተቃራኒ የሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር ለሠላማዊ ሠልፉ ዕውቅና አልሰጠሁም ሲል ህዳር 22 ቀን  ድብዳቤ መጻፉን አስታውቀዋል፡፡ “በመሠረቱ መስተዳድሩ ጊዜና ቦታ እንዲቀየር አስተያየት ከማቅረብ ያለፈ ዕውቅና የመንፈግ መብት ...

Read More »

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን አስገራሚ የደሞዝ ጭማሪ አደረገ

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት 111 በመቶ የደሞዝ ጭማሪ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን፣ በአማራ እና በኦሮምያ ክልል በተከታታይ ተገቢ የሆነ የደሞዝ ማስተካካያ አላደረገም በሚል ጥያቄ ሲቀርብብት ቆይቷል። ሰሞኑን የካቢኔ አባላት ተሰብስበው   የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ከግንቦት ሰባት እና አርበኞች ግንባር እንዲሁም  የኦሮምያ ክልል ጋዜጠኞች ከኦነግ ጋር የሚሰሩትና ለኢሳት መረጃ በማቅረብ በክልሎች መንግስት ላይ ህዝቡ አመኔታ እንዲያጣ ...

Read More »

በድቡብ ሱዳን አራት  ኢትዮጵያውያን በጥይት ተመቱ

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን እንዳለው በዋና ከተማዋ ጁባ አንድ ወንድና አንድ ሴት ሲገደሉ ሁለት ሴቶች ግን በጠና ቆስለው ወደ ኢትዮጵያ ተወስደዋል። የሁለቱም ሟቾች አስከሬንም በኢትዮጵያውያን እርዳታ ወደ ኢትዮጵያ መሄዱ ታውቆል:: ሰዎቹ በምን ሁኔታ እንደተገደሉና እንደቆሰሉ እንዲሁም ጥቃቱን ያደረሱትን ወገኖች ዝርዝር ለማወቅ አልተቻለም። በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በኢትዮጵያውያን የሚደረገውን ግፍና እንግልት ከመከታተል ይልቅ በዶላር ጥቁር ...

Read More »

መንግስት ከጸጥታ ችግሮች መካከል የተወሰኑትን መቅረፉን አስታወቀ

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም ከፌደራልና ከክልሎች ለተውጣጡ የጸጥታና ደህንነት ሃላፊዎች እንደተናገሩት መንግስት አራት የጸጥታ ችግሮች አጋጥመውታል፡፡ የመጀመሪያው የሽምቅ ውጊያ የሚያደርጉ ሃይሎች የፈጠሩት ስጋት ነው ያሉት ዶ/ር ሽፈራው እነዚህን ሃይሎች እና ሽብርተኞችን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ፈተና መሆኑን ሲገልጹ፣ ከሃይማኖት ጋር ተያይዞ የሚፈጠረውን የአክራሪነት አደጋ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር መቻሉንም ተናግረዋል። በብሄሮች ...

Read More »

በአብዛኛው በቀድሞ ባለስልጣናት የተመሰረተው ራያ ቢራ ፋብሪካ በቅርቡ ወደምርት ሊገባ መሆኑ ተሰማ፡፡

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀድሞው የመከላከያ ኢታማጆር ሹም ሌተናንት ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳይ የቦርድ ሰብሳቢነት የሚመራው ራያ ቢራ በቀድሞ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና ህወሃትን ተጠግተው በሚነግዱ ነጋዴዎች ከፍተኛ አክስዮን የተመሰረተ መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ። ማይጨው ከተማ ላይ የተገነበው ፋብሪካው 600 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል አለው። ከራያ ቢራ አክስዮን ባለድርሻዎች መካከል   ሌተናንት ጄኔራል ጻድቃንን እና  የቀድሞ የህወሃት ታጋይና የውጪ ...

Read More »

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአቶ አንዳርጋቸውን  መታሰር በመቃወም ሰልፍ አደረጉ

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያኑ ኦስሎ በሚገኘው የእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ገዢው ሃይል የወሰደውን እርምጃ ከማውገዝ በተጨማሪ የኢንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስላሉበት ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ባዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ አቶ አንዳርጋቸው የፍትህ ተምሳሌት፣ የነጻነት በር ከፋች ነው የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል። ኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አቶ አንዳርጋቸው በግፍ የመን ውስጥ ...

Read More »

በሃረር የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች የሚያመልኩበት አንድ ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ ተደረገ

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው የመንግስት ታጣቂዎች ወደ ሰማያዊ ብርሃን ቤተክርስቲያን በመሄድ ማፍረሳቸውን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን አንድ ፓስተር እስከባለቤታቸውና ሌላ አገልጋይ ታስረዋል። የሃረር አብያተ ቤተከርስቲያናት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዮሴፍ አምደማርያም ታስረው ሲፈቱ ሌላው የቤተክርስቲያኑዋ ፓስተር አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ። ቤተክርስቲያኗ በአገር አቀፍ ደረጃ ተመዝግባ የምትንቀሳቀስ መሆኗ ታውቋል። የክልሉ አፍራሽ ግብረሃይል አባላት 30 በሚሆኑ ታጣቂዎች ...

Read More »

በሚሰሩት መንገዶች ደስተኞች አይደለንም ሲሉ የባህርዳር ነዋሪዎች ገለጹ

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የገዢው መንግስት በምርጫ 2007 ያለውን ተቀባይነት ለማጠናከር በማሰብ የተለያዩ የህብረተሰቡን ክፍሎች በየክፍለ ከተማው በማሰባሰብ የተሰሩ ስራዎችን በማቅረብ ለመመስገን ሙከራ ቢያደርግም፤ተሰብሳቢዎች ግን ምንም እንዳልተሰራና ተሰራ የተባለውም ችግር ያለበት እንደሆነ  ተናግረዋል፡፡ የመንገዶች መበላሸት ያሳሰባቸው ነዋሪዎች በአካባቢው ላሉ አመራሮች የስራውን የጥራት ጉድለት ቢያሳውቁም የተስተካከለ ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡  “በ2006 የተሰራው ስራ በሙሉ ዜሮ ነው፡፡ በየክፍለ ...

Read More »