Author Archives: Central

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ የወልቃይትን ህዝብ ለማነጋገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ

የካቲት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሀትን 40ኛ ዓመት አክብረው ሲመለሱ  እግረ መንገዳቸውን  በ አማራ ክልል የተለያዩ  አካባቢዎችን እየጎበኙ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ  ፤የካቲተ 16 ቀን በወልቃይት ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት የህዝቡን ተቃውሞ በመፍራት መሰረዛቸው ነዋሪውን ክፉኛ አስቆጥቷል። የወልቃይት ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቲት 16 ቀን ወልቃይትን እንዲጎበኙ በአካባቢው ሹመኞች መነገሩን ተከትሎ  በየገጠር የሚኖረው ህዝብ ሳይቀር በመሰባሰብ ...

Read More »

ፋብሪካዎች በውጭ ምንዛሬ እጥረት ስራቸውን ለመስራት ተችግረዋል

የካቲት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የሚታየው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ፋብሪካዎች ስራቸውን በተገቢው መንገድ እንዳያከናውኑ እንቅፋት ፈጥሮባቸዋል። ከዚህ ቀደም ከደንበኞቻቸው ጋር የተለያዩ የስራ ውሎችን ተዋውለው በጊዜው ማድረስ ያልቻሉ ፋብሪካዎች፣ ለደንበኞቻቸው ” በአገራችን በሚታየው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት በሰአቱ ማድረስ አልቻልንም” በማለት የይቅርታ ደብዳቤዎችን በመጻፍ ላይ ናቸው። በማኑካንቸሪንግና በኮንስትራክሽን ዘርፍ እንዲሁም በአስመጪነት የተሰማሩ ባለሃብቶች ለከፍተኛ ችግር የተዳረጉ ...

Read More »

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተቃውሞ ሰልፉን አራዘመ

የካቲት ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲዎቹ ምርጫ ቦርድ የአባል ፓርቲዎችን ዕጩዎች ያለ አግባብ በመሰረዙና እስከዛሬ ድረስ ዕጩዎቻቸውን በዝርዝር ባለማሳወቁ ምክንያት ለየካቲት 22/2007 ዓ.ም በ15 ከተሞች ሊያደርጉ አስበው የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፋቸውን የትብብሩን ጸሃፊ አቶ አቶ ግርማ በቀለን ጠቅሶ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። አቶ ግርማ በቀለ ‹‹ምርጫ ቦርድ ዕጩዎችን እመዘግብበታለሁ ባለበት የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ዕጩዎቻችን በዝርዝር ሊያሳውቀን ...

Read More »

ኢህአዴግ “የቀለም አብዮትና አመጽ የመምራት እድል አለው ያለውን የተማረውን የመንግስት ሰራተኛ ክፍል በፍጹም እንደማያምነው” ገለጸ

የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ” የአገራችን ህዳሴና የሲቪል ሰርቪስ ሚና” በሚል ርዕስ ለከፍተኛ አመራሩ ስልጠና ባዘጋጀው ሰነድ ላይ፣ በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ የሚገኘው የተማረው ክፍል በኢህአዴግ የመጨረሻው የማይታመነው ክፍል ነው ሲል ገልጾታል። “ይህ የተማረው ሃይል” ይላል ሰነዱ ” አመፅየመምራት፤ኢሳትና ቪኦኤን ከመሳሰሉ አፍራሽ ሚዲያዎች ጋር በመተባበር የቀለም አብዮት ለመምራት ፣ አመጽ ለማደራጀት እና መሪ ተዋናይ ...

Read More »

የአቶ አባይ ጸሃየ ንግግር ተጨማሪ ደም እንዲፈስ የሚያደርግ ነው ሲል ሂውማን ራይትስ ሊግ አስታወቀ

የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ አባይ ጸሃየ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በሃይል እንደሚተገበር በድብቅ ሲናገሩ  መደመጣቸው ፣ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ አመጽን የሚጋብዝ ብቻ ሳይሆን ፣ ከዚህ ቀደም የደረሰው ደም መፋሰስ ሳይበቃ ተጨማሪ ደም መፋሰስ እንዲኖር የሚጋብዝና የሰው ህይወት እንዲጠፋ የሚያደርግ ነው ሲል የሰብአዊ መብት ሊጉ ባወጣው መግለቻ ጠቅሷል። የባለስልጣኑ እብሪት የተሞላበት ንግግር ለውይይት፣ ለምክክር እንዲሁም ...

Read More »

በተቃውሞ የተነሳ ተቋርጦ የነበረው በዋልድባ ገዳም የሚያልፈው የመንገድ ግንባታ እንደገና ተጀመረ

የካቲት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የገዳሙ ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ከወልቃይት ተነስቶ በዋልድባ አብረንታት ገዳም አድርጎ ወደ ማይፀብሪ የሚሰራው መንገድ በ2004ዓ/ም በገዳሙ ፣በአካባቢው ሕብረተሰብ እና  በውጭ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጠንካራ ተቃውሞ የተነሳ ተቋርጦ ቆይቷል። መንግስት ወደ ገዳሙ የሚገባው ለአፈር ምርምር እንጂ መንገድ ለመስራት አይደለም በሚል የመንግስት ካድሬዎችና አንዳንድ መነኮሳትና የቤተክነት ሃላፊዎች  የሀሰት ምስክርነት እንዲሰጡ አድርጎ ህዝቡን ...

Read More »

የኬንያ  ፖሊስ  100  ኢትዮጵያውያንን  ይዞ  ማሰሩን  አስታወቀ

የካቲት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኬንያ የወንጀል ምርመራ ልዩ ክፍል ሃላፊ ኖሃህ ካቱሞ  100 ኢትዮጵያውያን ኬንያን እንደመሸጋገሪያ በማድረግ በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት ሲሉ መያዛቸውን ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም አማርኛ የሚያስተረጉም በመጥፋቱ በማግስቱ መቀጠራቸውን የኬንያ ጋዜጦች ዘግበዋል። አምና በተመሳሳይ መንገድ 95 ኢትዮጵያውያን ተይዘው ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። አገራቸውን እየለቀቁ ወደ ደቡብ አፍሪካና አረብ አገራት የሚሰደዱ ...

Read More »

የአለም ባንክ በኢትዮጵያ የተፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በጽሞና እንዲያቸው ተጠየቀ

የካቲት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ  በአለም ባንክ ድጋፍ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ፣ የባንኩን ፖሊሲ የሚጻረሩ ሆነው መገኘታቸውን የአለም ባንክ የውስጥ የምርመራ ክፍል ማሳወቁን ገልጿል። ይሁን እንጅ የባንኩ ማኔጅመንት በባንኩ የውስጥ የምርመራ ቡድን የቀረበውን ሪፖርት የሚቃረንና ባንኩን ከተጠያቂነት የሚያድን ሌላ ሪፖርት አቅርቧል። የአለም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በምርመራ ...

Read More »

ኢህአዴግ በደንብ አላገለገሉኝም ያላቸውን የመጅሊስ አመራሮችን አባረረ

የካቲት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሕዝበ ሙስሊሙ ፍላጎት ውጪ በ2005 ዓ.ም የተመረጡት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) አመራሮች የመንግስትን ፍላጎት ማርካት  ባለመቻላቸውና በአመራሮቹ ላይ እምነት በመጥፋቱ በአስቸኩዋይ ስልጣናቸውን እንዲያስረክቡ በማድረግ በምትካቸው ሌሎች ተመርጠዋል። በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ሼህ ኪያር መሐመድ ኢማንን ወደ ስልጣን ያመጣውን የመጅሊስ ምርጫ  ...

Read More »

በጨለለቅቱ ከተማ በተነሳ ግጭት አንድ ሰው ሲሞት በርካቶች ቆሰሉ

የካቲት ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን በኮቾሬ ወረዳ ጨለለቅቱ ከተማ ሃሙስ የካቲት 12 ቀን 2007 ኣም ከቀኑ 11 ሰአት ላይ በተነሳው ግጭት አንድ ሰው ሲሞት ከ10 በላይ የሆኑ ደግሞ ቆስለው ዲላ ሆስፒታል በመታከም ላይ ናቸው። በከተማዋ ያሉ በርካታ ሱቆች ተዘርፈዋል፣ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎም ተነስቷል። የፌደራልና የዞኑ ፖሊስ ወደ ከተማዋ በማምራት ግጭቱን ማብረዳቸውን ነዋሪዎች ...

Read More »