ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከምሁራንና ከዲሞክራሲ አቀንቃኞች ጋር በጋራ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ፣ ተጋባዥ እንግዶች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ወረቀቶችን ያቀርባሉ። ምሁራኑ ኢትዮጵያ የገጠሙዋትን ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች በማንሳት ተጨባጭ የመፍትሄ ሃሳቦችንም ያመላክታሉ ተብሎ ይጠበቃል። በውይይቱ ላይ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ምሁራን፣ የዲሞክራሲ አቀንቃኞችና የውጭ አገር ዜጎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። በፈረንጆች አቆጣጠር ሜይ 9 ...
Read More »Author Archives: Central
በርካታ ወጣቶችን በጨለማ እየታፈሱ ነው
ሚያዝያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን አሰቃቂ አደጋ ተከትሎ ለተቃውሞ የወጡ ኢትዮጵያውያን በፌደራል ፖሊሶች ተደብድበው እንዲታሰሩ በተደረገ ማግስት፣ የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች በአዲስ አበባ በተለያዩ ክፍለከተሞች የሚገኙ ወጣቶችን በምሽት በማፈን ወደ እስር ቤት እያጋዙ ነው። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ...
Read More »ራሱን በእሳት አቃጥሎ የገደለው መምህር ፍትህ ማጣቱን የሚያትት ደብዳቤ ጽፎ ማለፉ ታወቀ
ሚያዝያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው አርብ ባሃድያ ዞን በሶሮ ወረዳ በጊምቢቾ ከተማ የፊዚክስ መምህር የነበረው ጌታቸው አብራሃም ፣ በወረዳው አስተዳደር ግቢ ውስጥ ቤንዚን አርከፍክፎ ራሱን አቃጥሎ ገድሏል። የመድረክ አባል የነበረው መምህር ጌታቸው ከምርጫው ጋር በተያያዘ የምርጫ ቅስቀሳ ያደርግ ነበር። የተቃዋሚ አባል በመሆኑ ብቻ የ3 ወር ደሞዙን እንዳያገኝ የተከለከለው መምህር፣ አቤቱታውን ለተለያዩ ባለስልጣናት ሲያቀርብ ቆይቷል። በመጨረሻ ...
Read More »በባህርዳር ከተማ ሁለት ወጣቶች ታፍነው ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰዱ
ሚያዝያ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢችል ቀሬ እና ብርሃኑ ታየ የተባሉ ወጣቶች መጋቢት 29 ቀን 2007 ዓም በፌደራል ፖሊሶች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ የደረሱበት አልታወቀም። ወጣቶቹ በምን ምክንያት ታፍነው እንደተወሰዱም ሆነ ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ በህይወት ይኑሩ አይኑሩ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።
Read More »የኢህአዴግ መንግስት የአንድ ቀን የሰላም ጉባኤ ጠራ
ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በመላው አገሪቱ በሚታየው የሕዝብ ቁጣ ስጋት ላይ የወደቀው ኢህአዴግ መራሹ መንግስት፣ በምርጫ ቦርድ አማካይነት ግንቦት 16 ቀን ሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሠላም ስለሚጠናቀቅበት ለመምከር የአንድ ቀን ስብሰባ ጠርቷል፡፡ በሒልተን ሆቴል በሚካሄደው ስብሰባ ላይ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡ በተቃዋሚዎች ሁልጊዜም ቅሬታ የሚቀርብበት ምርጫ ቦርድ በተለይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ...
Read More »በሊቢያ ሚስቱንና የሶስት ወር ልጁን ትቶ የደረሰበት ያልታወቀው ሰው ከእስር ቤት አምልጦ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቀለ
ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያ ቤንጋዚ የሚኖር አንድ ሙስሊም ኢትዮጵያዊ በጦርነት መሃል አልፎ ከ3 ወር ልጇ ጋር ለሶስት ቀናት ቤት ዘግታ የተቀመጠቸውን ኢትዮጵያዊት ማዳኑን ኢሳት በልዩ ዘገባ ካቀረበ በሁዋላ፣ ባልየው ከ4 ቀን በሁዋላ ከእስር ቤት አምልጦ ከቤተሰቡ ጋር ተቀላቅሏል። በቀሌ አስፋው የተባለው ኢትዮጵያ ወደ ሊቢያ የሄደው በቅርብ ሲሆን፣ የሊቢያ ፖሊሶች መንገድ ላይ በድንገት እንደያዙት ገልጿል። ከተያዘ ...
Read More »በማምረቻ ዘርፍ የመንግስት ዕቅድ አልተሳካም
ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማምረቻ ወይንም በማኒፋክቸሪንግ ዘርፍ መንግስት በያዘው የአምስት ዓመት የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ መሰረት መከናወን ካለባቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች መካከል ከሲሚንቶ በስተቀር አለመሳካቱን አንድ ሰነድ አመልክቷል፡፡ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘ ሰነድ እንዳመለከተው በሰኔ ወር 2007 ዓ.ም በሚጠናቀቀው የአምስት ኣመት እድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ከተካተቱት መካከል ጥቅም ላይ የዋሉ ወረቀቶችና ከነባር ፋብሪካዎች ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተደምሮ 19 ሺ ...
Read More »አቶ ስንታየሁ በደህንነነቶች ታፍኖ ተወሰደ
ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የነበረው እና በአሁኑ ወቅት የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ሚያዝያ 20/2007 ዓ.ም በደህንነቶች ታፍኖ ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ አራት ሲቪል የለበሱ ደህንነቶች ‹‹ትፈለጋለህ!›› በማለት በመኪና አፍነው ወዳልታወቀ ቦታ የወሰዱት ሲሆን ለእስሩ ምንም አይነት ...
Read More »ኢትዮጵያ ከ15 አመታት በሁዋላ የነፍስ ወከፍ ገቢዋ 1 ሺ ዶላር እንደማይደርስ አንድ የኢኮኖሚ ትንበያ አመለከተ
ሚያዝያ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ የግብርና ዲፓርትመንት ባወጣው ጥናት በፈረንጆች አቆጣጠር በ2030 ወይም ከ15 አመታት በሁዋላ የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢ 820 ዶላር ይደርሳል። ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በቅርቡ ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ እንደሚያሰልፋት በተደጋጋሚ ቢናገርም፣ የጥናት ውጤቱ እንደሚያሳየው በ2030 ኢትዮጵያ ፣ የመካከለኛ ገቢ ዝቅተኛ መነሻ ከሆነው 1 ሺ ዶላር ለመድረስ አትችልም ። በርካታ የአፍሪካ አገሮች ...
Read More »በስደት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸሙትን አሰቃቂ ድርጊቶች የሚያወግዙ ሰልፎችንና የሻማ ማብራት ስነስርአቶች ተካሄዱ
ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባሳለፍነው ሳምንት በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪካና በየመን በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግፍ የሚቃወሙ ሰልፎች፣ የሻማ ማብራት ስነስርአቶችና ጸሎቶች በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በእስያና በአውስትራሊያ ተካሂዷል። በለንደን ሰኞ ሚያዚያ 19 ቀን 2007 ዓም በተካሄደው ከፍተኛ ተቃውሞ ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው ላይ የደረሱትን በደሎች አጥብቀው ኮንነዋል። ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ በስፍራው ተገኝቶ እንዳለው እስከ አንድ ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ...
Read More »