Author Archives: Central

ሰማያዊ ፓርቲ ከምርጫ በኋላ እየተወሰደ ያለው እስርና ግድያ እንዲቆም ጠየቀ

ሐምሌ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው ሐምሌ 7 ቀን 2007 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ሀገራዊ ‹‹የውሸት ምርጫ›› ከተጠናቀቀበት ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም ማግስት በምርጫው በንቃት ይሳተፉ የነበሩና በአስተሳሰባቸው በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን ዜጎች በማንአለብኝነት መደብደብ፣ ከሰራ ማፈናቀል፣ ማሰር፣ ማሸማቀቅና መግደል የአገዛዙ ዋና መገለጫ ሆኗል” ብሎአል። ይህንን ድርጊቱን ገዥው ፓርቲ በአስቸኳይ እንዲያቆም ፓርቲው ጠይቋል። ሰማያዊ ‹‹በሰላማዊ ...

Read More »

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ሦስተኛው ዓለማቀፍ የፋይናንስ ልማት ጉባዔ ላይ አክሽን ኤይድ በበለጸጉ ሀገሮች ላይ ተቃውሞ ማሰማቱ ተዘገበ።

ሐምሌ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አዲስ ስታንዳርድ እንደዘገበው አክሽን ኤይድ በካናዳ፣ በአሜሪካና በአውሮፓ ህብረት ይሽከረከራሉ ያላቸውን 77 ሀገሮችን የአዲስ አበባው ጉባዔ አላማ እንዳይሳካ እንቅፋት እየፈጠሩ ነው ሲል ተቃውሞ አቅርቧል። የድርጅቱ ኃላፊ አዲያምኖ ካምፖሊና የበለጸጉት ሀገሮች ጥቂት ሀብታም ሀገሮች የበለጠ ሀብታም ፤ብዙሀኑ ደሀ ሀገሮች ደግሞ ይበልጥ እንዲደኸዩ እየሠሩ ነው ሲሉም ከሰዋል። አሁንም በዚህ ጉባዔ ላይ የበለጸጉት ሀገራት ...

Read More »

ኢትዮጵያ ኢንተርኔት ስለላ በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር አውጥታለች ተባለ

ኢሳት ዜና (ሐምሌ 6 2007) የኢትዮጵያ መንግስት ከጣሊያኑ የሳይበር ሴኩሪቲ ኩባኒያ ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ሲገልጽ ቢቆይም የኩባኒያው ሀላፊዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ትናንት ሰኞ ማረጋገጫ መስጠታቸውን የእንግሊዙ ዘጋርዲያን ጋዜጣ ዘገበ። የሀኪንግ ቲሙ መስራችና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ዴቪድ ቭንሴንዜቲ ድርጅታቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ ለግብጽ ለሱዳንና ለሞሮኮ የአፍሪካ ሀገራት አገልግሎቱን ሲያቀርብ መቆየቱን የፋ አድርጓል። “ኢትዮጵያ አገልግሎታቸንን ጋዜጠኞችንና የመንግስት ተቃዋሚዎችን ለመሰለል መጠቀሟን በሰማን ግዜ ሀገሪቱ ...

Read More »

5ኛው የመድረክ አባል ተገደለ

ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መድረክ ባወጣው መግለጫ ከ2007 ምርጫ በሁዋላ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የተገደሉ የመድረክ አባላት ቁጥር 5 ደርሷል። የኢህአዴግ አገዛዝ በደቡብና ኦሮምያ የሚፈጽማቸው ድብደባዎችና እስራቶች መጨመራቸውንም መድረክ ገልጿል። በከፋ ዞን በግንቦ ወረዳ በአድዮ ካካ ምርጫ ክልል በጎጀብ ምርጫ ጣቢያ የመድረክ ምርጫ ታዛቢ/ወኪል ሆነው የሠሩት አቶ አሥራት ኃይሌ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ቅዳሜ ሰኔ 27 ቀን ...

Read More »

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት በመተማና አብርሃጅራ የሚገኙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹን ወደ ጎንደር ሊያዛውር ነው

ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን በአርበኞች ግንቦት7 እና በገዢው ፓርቲ ወታደሮች መካከል የተደረገውን ጦርነት ተከትሎ በዶ/ር አዲስ አለም ባሌማ የሚመራው የምርት ገበያ ድርጅቱ በመተማና አብርሃ ጅራ የሚገኙ ቅርንጫፎቹን በመዝጋት ወደ ጎንደር ከተማ ለማዛወር እቅድ እንዳለው ምንጮች ገልጸዋል። ድርጅቱ በሰሜን አካባቢ በሁመራ፣ ጎንደርና መተማ ለሰሊጥ ጥራት ምደባና ማከማቻ ቅርንጮፎችን የከፈተ ሲሆን፣ የአብርሃ ጅራ ...

Read More »

ፍርድ ቤቱ የእነ ደብሬ አሸናፊን ጉዳይ አላይም አለ

ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመናገሻ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት ሀምሌ 3/2007 ዓ.ም በደህንነትና ፖሊሶች ተይዞ የታሰረውን የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ደብሬ አሸናፊንና በወቅቱ ከእሱ ጋር ተይዘው የታሰሩትን ወጣቶች ጉዳይ እንደማያይ አስታውቋል፡፡ ዛሬ ሀምሌ 6/2007 ዓ.ም ደብሬ አሸናፊ፣ ቴዎድሮስ ሻንካና ኤፍሬም የተባሉት ታሳሪዎች አምስት ኪሎ በሚገኘው የመናገሻ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ዳኛው ‹‹ይህን ጉዳይ ...

Read More »

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር አፍራሽ ግብረ ኃይል በከተማዋ ዳርቻ የሚገኙ የይዞታ ቦታዎች አፈረሰ

ሐምሌ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በርካታ ፖሊሶችና የታጠቁ ኃይሎች በመኪና በመሆን ከተማዋን ሲዞሩ መዋላቸውን ዘጋቢያችን ገልጻለች። የፖሊስ አባላት በተጠንቀቅ (stand by) ሆነው እዲጠብቱ የታዘዙ ሲሆን፣ ከአሁን በፊት ለምርጫ ቅስቀሳ በሚል ለባለ ይዞታ ቦታ ባለቤቶች የተሰጠው ጊዜያዊ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ከተቀማ በሁዋላ፣ ዛሬ ደግሞ ይባስ ብሎ አንዳንድ ቤቶችን በግዳጅ እያፈረሱ ነው። ህብረተሰቡ አመጽ ሊያስነሳ ይችላል በሚል የታጠቁ ...

Read More »

በሰሜን የአገሪቱ ክፍል የሚታየውን ውጥረት ተከትሎ አየር ሃይል በጠንቀቅ እንዲቆም ታዘዘ

ሐምሌ ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት የአርበኞች ግንቦት7 በወሰደው ፈጣን ጥቃት በርካታ የኢህአዴግ ወታደሮች መገደላቸውን ፣ ይህንን ተከትሎ የወልቃይትና አካባቢው ህዝብ ያሳያው ድጋፍ እና ሽምቅ ተዋጊዎችን ለመቀላቀል የሚጠይቀው ወጣት መበራከት ያሰጋው ገዢው ፓርቲ፣ የአየር ሃይል አባላት በጠጠንቀቅ እንዲቆሙ ማዘዙን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የአየር ሃይል አባላቱ ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በሌሊት ፈረቃ እንዲሰሩ ...

Read More »

ሙስሊሙ ማህብረሰብ ለመሪዎቹ ያለውን ድጋፍ ገለጸ

ሐምሌ ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሰሞኑን በእስር ላይ የሚገኙ የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላትን ጥፋተኛ ማለቱን ተከትሎ ፣ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዛሬ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ድምጹን አሰምቷል። በቤኒን መስጊድ እጅግ በርካታ ህዝብ በተገኘበት በተደረገው ተቃውሞ ሙስሊሙ ህዝብ፣ የመሪዎቹን ነጻነት ከሚያረጋግጠው የፍርድ ቤት ውሳኔ ውጭ ሌላ ውሳኔ እንደማይቀበል ግልጽ አድርጓል። ፍርድ ቤት ...

Read More »

በሰሜን ሸዋ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ታድነው እየታሰሩ ነው

ሐምሌ ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ሐምሌ 3/2007 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋ ሮቢት ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ቤታቸውን ድረስ በመሄድ ፖሊስ እያደነ እንዳሰራቸው የአይን እማኞች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ከጠዋቱ 4 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ የነበሩትን አቶ ዘነበ ደሳለኝ፣ የፓርቲው ንብረት ያዥ የሆኑትን አቶ መንግስቱ ተበጀና የቀድሞው አንድነት የቀጠና ...

Read More »