Author Archives: Central

ኢትዮጵያና ኬንያ ሶማሊያን ለመቀራመት መስማማታቸውን ዊኪሊክስ አጋለጠ

ሐምሌ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዊክሊክስ ባወጣው መረጃ ላይ የኢትዮያና የኬንያ ገዢዎች ሶማሊያን ለአራት ቦታ በመክፈል ለመቀራመት በሚስጥር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስነብቧል። ሶማሊያ ለም እና በማዕድን የበለጸገ ምድር ባለቤት በመሆንዋ የብዙ ሀገራትን ፍላጎትን ትስባለች።ዊክሊክስ ጅቡቲ ከሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤንባሲ መረጃውን እንዳገኘው ገልጿል።በአሁኑ ወቅት ብዙ አገራት በሶማሊያ ውስጥ ይገኛሉ፤የተወሰኑት በግፊት እንዲወጡ ተደርገዋል ብሎአል። ሶማሊያ ለአራት ክልል ትከፈላለች ...

Read More »

ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አስባችኋል በሚል ሰበብ ሰላማዊ ዜጎች እየተደበደቡ ነው ተባለ

ኢሳት ዜና (ሃምሌ 16, 2007) የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በሚገቡ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ተንቀሳቅሳችኋል ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች በእስር ቤት ድብደባ እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ለፍርድ ቤት ገለጹ። ሐሙስ እለት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት አቶ መርከቡ ሀይሌና አቶ አበበ ቁምላቸው ፕሬዘዳንት ኦባማ ወደ ሀገሪቱ በሚመጡ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ተንቀሳቅሳችኋል ተብለው ለእስር መዳረጋቸው ይታወሳል። ...

Read More »

ገዢው ፓርቲ የሽብር ተግባር በመፈጸም በግንቦት7 ለማላከክ አቅዷል ሲል አርበኞች ግንቦት7 ከሰሰ

ሐምሌ ፲፸ (አስራሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ ባወጣው መግለጫ “በሕዝባዊ ኃይሎች ላይ ሊወስድ ያሰበው እርምጃ ተቀባይነት እንዲያገኝለት የሽብር ተግባር ፈጽሞ በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ለማላከክ ወስኗል።” ብሎአል። አርበኞች ግንቦት 7 “በቅርቡ የጀመረው የነፃነት ትግል የፈጠረበት መደናገጥ ለመሸፈንና ንቅናቄውን በኢትዮጵያ ሕዝብና በዓለም ዓቀፍ ማኅበረሰብ ለማስወገዝ ያግዘኛል ብሎ ያመነበት ይህን ዘግናኝ ሴራ ከሳምንት በፊት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁቱን አጠናቆ የነበረ ...

Read More »

በእስር ላይ የሚገኙት የበለሳ ወረዳ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ለወራት ፍርድ ቤት አልቀረቡም

ሐምሌ ፲፸ (አስራሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ ፈንታሁን ታደሰና ሌሎች 6 እስረኞች ለ5 ወራት ያህል ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። በፖሊስ የካቲት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. የታሰሩት እነ አቶ ፈንታሁን በወቅቱ የጉሃላ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ወስዷቸው የነበር ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ”እኛ ይህን ጉዳይ አናይም! ከፈለጋችሁ ወደ ዞን ፍርድ ቤት ወስዳችሁ አሳዩ” ብሎ መልሷቸዋል፡፡ፖሊስ እስረኞቹን ወደ ...

Read More »

ፕ/ት ኦባማ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን ለኢትዮጵያ መሪዎች ያነሳሉ ብለው እንደሚጠብቁ የሂውማን ራይትስ ወች ባለስልጣን ገለጹ

ሐምሌ ፲፸ (አስራሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የድርጅቱ የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሚስ ሌስሊ ሌፍኮ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ የሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት የፕሬዚዳንቱ አንድ አጀንዳ ይሆናል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። ፕ/ት ኦባማ ኢትዮጵያን መጎብኘት አልነበረባቸውም የሚለው አስተያየት ዋናው ጉዳይ አለመሆኑን የገለጹት ሌፍኮው፣ ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ምን ምን ጉዳዮችን አነሱ የሚለው ጥያቄ ዋናው ጉዳይ መሆን እንደሚገባውና የጉብኝታቸው ውጤት ...

Read More »

በባህርዳር የቀድሞ የሰራዊት አባላት ያደረጉት ተቃውሞ በሃይል ተበተነ

ሐምሌ ፲፮ (አስራስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቀድሞው መንግስት ዘመን በውትድርና ሙያ አገራቸውን ያገለገሉ እንዲሁም በኢህአዴግ ዘመን በተመሳሳይ ሙያ ያገለገሉ እና ያለ ስራ ወይም ያለጡረታ የተሰናበቱ ወታደሮች፣ በአገሪቱ የሚታየውን የኑሮ ውድነት መቋቋም አልቻልንም፣ መንግሰት ስራ ይሰጠን ወይም ደሞዝ ይክፈለን በሚል የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ በመነሳት ወደ መስተዳድሩ ጽ/ቤት በማምራት ላይ የነበሩ ወታደሮች ፣ መስተዳድሩ አካባቢ ሳይደርሱ ...

Read More »

ፕ/ት አቦማ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ለሰብአዊ መብት ቦታ እንዲሰጡ አንድ ሴናተር ጠየቁ

ሐምሌ ፲፮ (አስራስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጥያቄውን ያቀረቡት በአሜሪካ ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ግንኙነት የተዘዋዋሪ ወንጀሎችና የሕዝብ ደሕንነት ሊቀመንበር የሆኑት ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ ናቸው። ዴሞክራሲ፣የሰብዓዊ መብትና ዓለምአቀፍ የሴቶች ጉዳይ፣ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ወቅት ቅድሚያ ሊሰጡባቸው የሚገቡ አንገብጋቢ ጉዳዮች መሆናቸውን ሴናተሩ ጠቅሰዋል። ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ ”ኢትዮጵያና አሜሪካ ሽብርተኝነትን በመዋጋት በአካባቢው መረጋጋትን ለመፍጠር ፍላጎት ማሳየታቸውም አስፈላጊ ቢሆንም፤አሜሪካ ...

Read More »

አቶ በፍቃዱ አበበ የመከላከያ ምስክሮችን አሰማ

ሐምሌ ፲፮ (አስራስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብርተኝነት ተከሶ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኘው በአርባ ምንጭ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ዋና ፀኃፊ አቶ በፍቃዱ አበበ በትናንትናው ዕለት ሀምሌ 15 ቀን 2007 ዓ.ም በልደታ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት የመከላከያ ምስክሮቹን አሰምቷል፡፡ ከአምስቱ የመከላከያ ምስክሮች መካከል አራቱ ፣ የአርባ ምንጭ ፖሊስና ደህንነቶች በፍቃዱ አበበ ላይ በሀሰት ከመሰከሩ የተሻለ ጥቅም እንደሚሰጣቸው ቃል ...

Read More »

በአማራ ክልል የበርበሬና የምስር ዋጋ ከእጥፍ በላይ ጨመረ

ሐምሌ ፲፮ (አስራስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ በሚገኙ በሁሉም አካባቢዎች 38 ብር ይሸጥ የነበረው አንድ ኪሎ በርበሬ ፣ 185 ብር በመሸጥ ላይ ሲሆን፣ 26 ብር በኪሎ ይሸጥ የነበረው ምስር ደግሞ ከ50 ብር በላይ እየተሸጠ ነው። በተፈጠረው የዋጋ ንረት የክልሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው። ክልሉ በበልግ ወራት የተጠበቀው የምስር ምርት ባለመገኘቱ የተፈጠረ ነው ሲል፣ የበርበሬ እጥረት ማጋጠሙንም አልሸሸገም። ...

Read More »

ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት የሞከሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በማላዊ የፀጥታ ኃይሎች ተያዙ

ሐምሌ ፲፮ (አስራስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በማላዊ ካሮንጎ ከተማ አቅራቢያ 34 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ማንነቱ ያልታወቀ ማላዋዊ ሕገወጥ ስደተኞችን አስተላላፊ ግለሰብ ”በሙያው የካበተ ልምድ አለኝ፤ከዚህ በፊት ከማላዊ፣ዛምቢያ፣ሞዛምቢክና ዝምባቢዌ ስደተኞችን አሸጋግራለሁ።” በማለት ስደተኞችን አጭበርብሮ በማሳመን 3 ሚልዮን የማላዊ ክዋቻ ተቀብሏቸዋል።የካሮንጋ የስደተኞች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጀርሜህ ፣ ኢትዮጵያውያኑ በካሮንጋ ቺውታ ...

Read More »