ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብር ወንጀል ተከሶ ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኘው አበበ ካሴ ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመበት ታወቀ አበበ ካሴ፣ በማእከላዊ እስር ቤት የሁሉም ጣቶቹ ጥፍሮች ተነቅለው፣ በዘር ፍሬው እና በመላ አካላቱ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበት መረጃ ለማውጣት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ በመጨረሻ ቂሊንጦ እስር ቤት ከተወረወረ በሁዋላ፣ የደረሰበትን ችግር ሁሉ ዘርዝሮ በመጻፍ ለመገናኛ ብዙሃን በድብቅ እንዲደርስ ...
Read More »Author Archives: Central
በኢትዮጵያ ወታደሮች ለተገድሉት አምስት ንፁሃን ሰላማዊ የሶማሊያ ዜጎች የአፍሪካ ህብረት ጦር ይቅርታ ጠየቀ
ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ባለስልጣናትና የሶማሊያ መንግስት ባለስልጣናት በሂራን ክልል ቡሎ ቡርዴ እና በለድ ወይኔ ከተማ ውስጥ ከአካባቢው የአገር ሽማግሌዎች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ሽማግሌዎቹ፣ ከአምስት በላይ ንፁሃን የሶማሊያ ዜጎች በኢትዮጵያ ወታደሮች በግፍ መገደላቸውን ተናግረዋል። የሶማሊያ ምክትል የመከላከያ አዛዥ መሀመድ አደን ግድያው መፈፀሙን አምነው የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ይቅርታ ጠይቀውናል ብለዋል። ከዚህ ክስተት አንድ ...
Read More »በማላዊ የታሰሩ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ናቸው ተባለ
ኢሳት (ነሐሴ 4፣ 2007 ዓም) 200 የሚጠጉ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች በማላዊ እስር ቤቶች የጤንነታቸው ሁኔታ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አንድ አለምአቀፍ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ገለጠ። ኢትዮጵያዉያኑ ከባለፈው አመት ታህሳስ ወር ጀምሮ በማላዊ መዲና ሊሎንግዌ በእስር ላይ መሆናቸውን ዶክተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስ (Doctors Without Borders) የተሰኘ የፈረንሳይ ድርጀት አስታውቋል። በማላዊ የበጎ አድራጎት ድርጅት ተወካይ የሆኑት ኒኮሌት ጃክሰን ስደተኛ ኢትዮጵያኑ በተጨናነቀ ሁኔታ በእስር ...
Read More »በሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ድርቅ አስከፊ ጉዳት እያደረሰ ነው ተባለ
ኢሳት ዜና (ነሐሴ 4፣ 2007) ሰሞኑን በአፋር ክልል የተከሰተው ድርቅ ተባብሶ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቁምና የቤት እንስሳት መሞታቸውን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ በክልሉ በክረምት ወቅት የሚጠበቀው ዝናብ በሚፈለገው መጠን ባለመዝነቡ ምክንያት ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን በመግለፅ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ከአዲስ አበባ ወደ አፋር ክልል መዲና በሚወስደው ዋናው አስፋል መንገድ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቁምና የቤት እንስሳት በድርቁ ምክንያት ...
Read More »ምዕራባውያን ፖለቲከኞች አንዳርጋቸው ጽጌ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቁ
ኢሳት ዜና (ነሐሴ 4፥ 2007) የአሜሪካ ፤ የብሪታኒያ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ አመራሮች አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር እንዲፈቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ደብዳቤ መላካቸውን አልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገበ። የፖለቲካ አመራሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ደብዳቤ አቶ አንዳርጋቸው ለብቻቸው 24 ሰአት የተፈጥሮ ብርሀን በማያገኙበት ሁኔታ እስር ላይ መሆናቸውን እንደጠቀሱ አልጀዚራ በብቸኝነት ማግኘት ችያለሁ ያለውን መረጃ ዋቢ በማድረግ አስነብቧል። ለኢትዮጵያ መንግስት ጥያቄያቸው ያቀረቡት ...
Read More »የሁለቱ ክልሎች ገዢዎች እርስበርሳቸው እየተወነጃጀሉ ነው
ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትግራይ እና በአማራ ክልል ገዢዎች መካከል ያለው አለመግባባት በተለያዩ አጋጣሚዎች ከፍ ዝቅ ሲል ቆይቶ ፣ ሰሞኑን ኢህአዴግ በአካሄደው ግምገማ ላይ እንደገና አገርሽቶበታል። የትግራይ ክልል ገዢ አቶ አባይ ወልዱ የተወሰኑ የህወሃት ደጋፊዎችን በመያዝ በሁለቱ ክልሎች መካከል ስላለው አወዛጋቢ መሬት ፣ ከአማራ ክልል ገዢ ጋር በድንበር አካበባ ያደረጉት ውይይት፣ በዘለፋና በጸብ ከተቋጨ ከወራት በሁዋላ፣ ...
Read More »አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከህወሃት የደህንነት አባላት ጋር መስማማት አልቻሉም።
ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ኢህአዴግ ባደረገው ግምገማ ፣ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ እርሳቸውንና ቤተመንግስቱን ከሚጠብቁ የደህንነት ሃይሎች ጋር ተስማማተው መስራት አልቻሉም የሚል ትችት ከቀረበባቸው በሁዋላ፣ ግንኙነቱ ወደ ባሰ ደረጃ መውረዱን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሃይለማርያም “በቤተሰቦቼና እና በእኔ ላይ በሚደረገው አላግባብ ክትትል ተሰላችቻለሁ” የሚል ንግግር በሁለተኛው ዙር የኢህአዴግ ሂስ እና ግለ ሂስ የአቋም ግምገማ ላይ ተናግረዋል። ...
Read More »የደቡብ ሱዳን መንግስት ድርድሩ ከአዲስ አበባ እንዲወጣ፣ ስዩም መስፍንም እንዲቀየሩ ጠየቀ
ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደብዩብ ሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ መሄዱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን መንግስት ተደራዳሪን ከአገሯ አስወጥታለች። እርመጃው የተወሰደው የደቡብ ሱዳን መንግስት አንድ የተቃዋሚ አባል ወደ አዲስ አበባ እንዳይሄድ ማገቱን ተከትሎ ነው። ደቡብ ሱዳን የድርድሩ ቦታና አደራዳሪው ስዩም መስፍን እንዲቀየር የጠየቁ ሲሆን፣ ለዚህ የሰጡት ምክንያትም፣ አዳራዳሪዎቹ ራሳቸው በአገራቸው የተቃዋሚ ሃይሎችን ያስተናግዳሉ፣ እነሱ ሰላማዊና ...
Read More »በአዲስአበባ ከተማ የሚገኙ ሆቴሎች አብዛኛዎቹ ከደረጃ በታች ናቸው ተባለ
ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስአበባ ዓለም አቀፍ መስፈርት የሚያሟሉ ሆቴሎችን ደረጃ ለመመደብ በተካሄደው ጥናት 98 ያህል ሆቴሎች ከደረጃ በታች ሆነው መገኘታቸው ይፋ ሆኗል። በዓለም አቀፉ ቱሪዝም ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያዎች ተጠንቶ ባለፈው ቅዳሜ ይፋ በተደረገው ውጤት መሠረት ለውድድር ከቀረቡት 136 ያህል ሆቴሎች ደረጃ ማግኘት የቻሉት 38 ያህሉ ብቻ ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት ባለ5 ኮከብ ያገኙት 3 ሆቴሎች፣ ባለ4 ...
Read More »አርበኞች ግንቦት7 በሜልቦርን የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ማድረጉን አስታወቀ
ነኅሴ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአውስትራሊያ የሜልቦርን የአርበኞች ግንቦት7 ጽ/ቤት ” ሀገራችን ስላለችበት ሁኔታ እንምከርበት” በሚል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ስብሰባ በስኬት ተጠናቋል ብሎአል። የድርጅቱ የሜልቦርን ከተማ ተጠሪ አቶ ነብዩ መላኩ ፣ “የድርጅት አጥር ሳይከልለን ትግሉን እንርዳ” የሚል መልእክት ሲያስተላልፉ፣ ዶ/ር ታደሰ ብሩ በስካይፕ ባስተላለፉት መልእክት ደግሞ ” ትግሉ አድማሱን እያሰፋ መምጣቱን ገለጸው፣ “ትግላችን ...
Read More »