መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት፣ ሲፒጄ የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ የሆኑት ቶም ሮድስ፣ የዞን 9 ጸሃፊዎች የዚህን አመት የአለማቀፍ የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ማሸነፋቸውን ተከትሎ ለኢሳት እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ሽልማት የሚገባቸው በርካታ ጋዜጠኞች አሉ ሲሉ ጋዜጠኞች ለፕሬስ ነጻነት እየከፈሉ ያለውን መስዋትነት አወድሰዋል። የዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎችን ለመሸለም የፈለግነው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፕሬስ አፈና ለአደባባይ ...
Read More »Author Archives: Central
ኢህአዴግ ከሚያደርገው የካቢኔ ሹምሽር አዲስ ነገር ላይጠበቅ ይችላል ተባለ
መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፊታችን መስከረም 24 ቀን በኢህአዴግ መቶ በመቶ የተያዘው ፓርላማ ስራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የአቶ ሃይለማርያም የጠ/ሚኒስትርነት ሹመት ካጸደቀ በሃላ በጠ/ሚኒስትሩ አቅራቢነት የሚካሄደው የካቢኔ ሹም ር አዲስ ነገር ይዞ አይመጣም ተብሎአል። ለግንባሩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለአዲስአበባው ዘጋቢያችን እንደተናገሩት ግንባሩ በሙስናና በመልካም አስተዳደር ችግሮች በተጨማለቁ የካቢኔ አባላት ላይ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ካልቻለ ...
Read More »የህንዱ ፓወር ግሪድ ከ 400 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ተከፍሎት ስራውን ለቀቀ
መስከረም ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ድርጅትን እንዲያስተዳደር ለሁለት አመታት 21 ሚሊዮን 700 ሺ ዶላር ወይም ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ የተከፈለው ፓወር ግሪድ ይህ ነው የሚባል ስራ ሳያከናውን ተሰናብቷል። በአገሪቱ ውስጥ የሚታየው የመብራት መጥፋት ሊሻሻል ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ፣ ቀድሞውንም ይህን ያክል ገንዘብ ማውጣት ለምን አስፈለገ የሚል ጥያቄ አስነስቷል። ስራ አስኪያጅ የሚሾሙትና የሚያወርዱት ዶ/ር ደብረጺዮን ...
Read More »ገዢው ፓርቲ በአቶ ሞላ አስጎደም መክዳት ዙሪያ ለሚሰራው ፕሮጋንዳ ህዝብ የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጠ ነው
መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ የቀድሞው የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን) ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስጎደም ለ14 ዓመታት የነበሩበትን ድርጅት ከድተው ለኢህአዴግ ባለስልጣናት እጃውን መስጠታቸውን ተከትሎ ገዢው ፓርቲ እየሰራ ያለው የቅስቀሳ ስራ በህዝብ ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው። የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ትህዴን የአርበኞች ግንቦት7 አንድ የጦር ክፍል እንደሆነ አድርገው ማቅረባቸው፣ እንዲሁም ውስጥ ለውስጥ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ...
Read More »የተወሰኑት የኮሚቴ አባላት ስለተፈቱ ብቻ ትግሉ እንደማይቆም ድምፃችን ይሰማ አስታወቀ
መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ከሆኑት መካካል ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ ሳቢር ይርጉ፣ አቡበከር ዓለሙ እና ገጣሚው ሙኒር ሁሴን ከእስር መለቀቃቸውን አስመልክቶ ድምፃችን ይሰማ ባወጣው መግለጫ፣ ሁሉም እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች እስካልተፈቱ ድረስ ትግላቸው እንደሚቀጥሉ በአጽንኦት ገልጿል። ድምፃችን ይሰማ ፣ ” ተፈቺዎቹም ይሁኑ ታሳሪዎቹ ጀግኖቻችን ሃይማኖታችን በተደፈረበት፣ መንግስታዊ አምባገነንነት በሰፈነበት በዚህ ቁርጥ ...
Read More »በለቡ አንዲት የሃያ ዓመት ወጣት በፌደራል ፖሊስ አባል ተገደለች
መስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በለቡ መዝናኛ ውስጥ ከሴት ጓደኛዋ ጋር በመዝናናት ላይ የነበረችው ሰሎሜ ጉልላት የተባለችው የ20 ዓመት ወጣት ”አንቺ ሰው የማታናግሪው ለምንድ ነው?” በሚል ተልካሻ ምክንያት መሳሪያ የታጠቀው የፌደራል ፓሊስ አባል ተኩሶ ገድሏታል። ታጣቂው በወቅቱ እራሱንም ለማጥፋት ጭንቅላቱ አካባቢ ላይ ያቆሰለ ሲሆን፣ ሳይሞት በሕይወት መትረፉንና በሕክምና ላይ እንዳለ ለማወቅ ተችሏል። በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት ...
Read More »ሞላ አስገዶም የሸሸው ሰራዊቱ የአመራር ለውጥ ከመቀየሩ ጋር በተያያዘ ነው ሲሉ ምክትል አዛዡ ተናገሩ
መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታጋይ መኮንን ተስፋዬ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጹት ድርጅቱ ከሚያዚያ እስከ ነሃሴ በነበሩት ወራት ከታች እስከ ላይ የ7 ዓመታት ግምገማ አድርጓል። የሞላ አመራር “ትህዴንን ወደ ድል አላበቃውም ይቀየር” የሚል ጥያቄ በመላ ሰራዊት አባላት መነሳቱን የተነገሩት ምክትል አዛዡ፣ ሞላ አስጎደም አገርህን አድን ከሚለው አዲስ ጥምረት መመስረት ጋር የተያያዘ አይደለም ብለዋል። ድርጅቱ ከ2 ...
Read More »የዞን ፱ ጦማሪያን የዓለማቀፉን የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸላሚ ሆኑ
መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “ስለሚያገባን እንጦምራለን” በሚል መሪ ቃል ከዛሬ አራት ዓመት በፊት የተቋቋመው የዞን ፱ ዐምደ መረብ ጸሃፍት የሕገመንግስቱ የመጻፍ ነጻነት በሚፃረረው መልኩ እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በአሸባሪነት ተከሰው ካለ ፍትሕ በእስር ቤት የሚገኙት ጦማሪያኑና የቡድኑ አባላት ለፕሬስ ነፃነት ላደረጉት አስተዋፆ ዓለማቀፉን የፕሬስ ነጻነት ሽልማት ተሸላሚ አድርጓቸዋል። የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ እንዳስታወቀው የመገናኛ ...
Read More »የባለስልጣናት ሐብት ምዝገባ መረጃ እንደታፈነ ነው
መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የባለስልጣናትን ሐብት ምዝገባ ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ እንደተሳነው የኮምሽኑ ምንጮች አጋለጡ፡፡ ለጠ/ሚኒስትሩ ተጠሪ የሆኑትን የኮምሽኑ ኮምሽነር ዓሊ ሱሌይማን ትዕዛዝ ተቀብለው ብቻ የሚያስሩና የሚፈቱ በመሆናቸው በአዋጁ መሰረት ለህዝብ ይፋ መደረግ የነበረበት የባለለስጣናት የሐብት ምዝገባ በወቅቱ ለማከናወን ድፍረት ማጣታቸው ታውቆአል፡፡ የሐብት ምዝገባ ሥራን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በማድረግ ማንኛውም መረጃ ...
Read More »አልሸባብ ሁለት ወንድማማቾችን ሰላይ ነበሩ በማለት በአሰቃቂ ሁኔታ ገደለ
መስከረም ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በማዕከላዊ ሶማሊያ ሂራን ግዛት ራሶ መንደር አቅራቢያ የ20 ና የ25 ዓመት ወጣት የሆኑት ወንድማማቾች ሶማልያዊያንና አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በአልሸባብ ታጣቂዎች በግፍ ተገለው ተገኝተዋል። ሁለቱ ወንድማማቾች ባለፈው ሳምንት ነበር በቡቃበል ከተማ ውስጥ በድንገት የኢትዮጵያ ወታደሮችና የሶማሊያ መንግስት ሰራዊቶች አካባቢውን ለቀው ሲወጡ በአልሸባብ ሚሊሻዎች ታግተው የተያዙት። የአካባቢው ነዋሪዎች እማኝነታቸውን ሲሰጡ እንደተናገሩት አልሸባብ ...
Read More »