ኢሳት ዜና (መስከረም 12 ፣ 2008) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አምስት ከፍተኛ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አመራሮችን ከውጭ ምንዛሪ ጋር በተገናኘ ዛሬ ረቡዕ ከሃላፊነታቸው አነሳ። የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታና የባንኩ የቦርድ ሊቀመንበር ዶ/ር አበራ ደሬሳ፣ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ወንድማገኘሁ ነገራ፣ እንዲሁም ሁለት ምክትል ፕሬዚዳንቶች አቶ ቶሎሳ በየነና፣ አቶ አበበ ጥላሁን ከባንኩ አመራርነት መነሳታቸው ታውቋል። የኦሮሚያ ህብረት ስራ ማህበር ባንክ የአለም አቀፍ ...
Read More »Author Archives: Central
የአባይን ግድብ እንዲያጠና የተሰየመው የሆላንዱ ኩባንያ ስራውን በገለልተንነትና በጥራት ለመስራት ባለመቻሉ ኮንትራቱን ማቋረጡን ገለጸ
መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሆላንዱ ዴልታሬስ ኩባንያ ከፈረንሳዩ ቢአር ኤል አይ ኩባንያ ጋር በመሆን በአባይ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ጥናት እንዲያካሂድ በግብጽና በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተወክሎ ነበር። ይሁን እንጅ ጥናቱ ከመጀመሩ በፊት በምን መንገድ መካሄድ አለበት በሚለው ነጥብ ዙሪያ ከፈረንሳዩ ኩባንያ ጋር ሲነጋገሩ ቢቆዩም መስማማት አልቻሉም። ኩባንያው ከኢሳት ለቀረበለት የጽሁፍ ጥያቄ በሰጠው መልስ ” ጥናቱን በጥራትና ...
Read More »የጸረ ሙስና ኮምሽን ኮምሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን የባለሥልጣናትን ሐብት ምዝገባ መረጃ ለመገናኛ ብዙሃን ክፍት ለማድረግ ፍላጎት አለመኖሩን ተናገሩ
መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኮምሽነሩ ሰሞኑን በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለጉዳዩ በሰጡት ማብራሪያ ከ95 ሺህ በላይ ተሿሚ፣ ተመራጮችና የመንግስት ሠራተኞች ሐብት ኮምሽኑ መመዝገቡን፣ እንዲሁም ከ14 ሺህ በላይ ሐብት አስመዝጋቢዎች የቤተሰቦቻቸውን ሐብት አሳውቀው ማስመዝገባቸውን አረጋግጠዋል፡፡ «ይህ መረጃ ለምን ይፋ አይደረግም» ለሚለው ጥያቄም ሲመልሱ ለመገናኛ ብዙሃን የመናገር ግዴታ እንደሌለባቸው በመግለጽ በግል መረጃ ለሚጠይቁ ሲሰጥ መቆየቱንና ...
Read More »በውቤ በረሃ የሚገኙ ነጋዴዎች የንግድ ቦታቸውን በግዳጅ ሊነጠቁ ነው
መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተለምዶ ውቤ በረሃ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እስከ አፍንጮ በር የሚገኙ ነጋዴዎች፣ ምትክ የንግድ ቦታ ሳይሰጣቸው የንግድ ቤቶቻቸውን በግዳጅ ለማፍረስ እየታሸጉ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ። የከተማው አስተዳደር ነጋዴዎቹን ከዓመት በፊት ሰብስቦ በአክሲዮን እንዲደራጁና እያንዳንዳቸው 25,000 ብር በማዋጣት በባንክ ...
Read More »በደቡብ ክልል ከፍተኛ የስኳር እጥረት ተከሰተ
መስከረም ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው አገሪቱ የሚታየው የስኳር እጥረት እልባት ባያገኝም፣ በደቡብ ክልል እጥረቱ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ህዝቡ ለሻሂ የሚሆን ስኳር ማግኘት አለመቻሉን እየተናገሩ ነው። በሌላ በኩል ግን በኢህአዴግ የአንድ ለአምስት የጥርነፋ ስልት የቡድን መሪ የሆኑ ነጋዴዎች፣ መንግስት የሚያከፋፍለውን ስኳር፣ እየጫኑ ወደ አልታወቀ ቦታ እንደሚያሻግሩት ነዋሪዎች ይገልጻሉ። መሰረታዊ የሚባሉትን ...
Read More »መንግስታዊ ተቋማት ሙስና በመፈጸማቸው ምርመራ ሊደረግባቸው ነው
ኢሳት ዜና (መስከረም 11፣ 2008) የኢትዮጵያ የሐገር መከላከያ ሚኒስቴርን ጨምሮ በ23 መንግስታዊ ተቋማት ላይ ምርመራ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ። የፌደራል የጸረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አሊ ሱለይማን ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ፣ የሀገር መከላከያ ሚኒስቲር ህግን ባልተከተለ መንገድ የ 2 ሚሊየን ዶላር ግዢ መፈጸሙን አመልክተዋል ። በዚህ የሀገሪቱ ወታደራዊ ተቋም ህግን ባልተከተለ መንገድ ተፈጸመ የተባለውን ግዢ በተመለከተ ምርመራ መጀመሩን ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል። ከዚህም ...
Read More »በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት 3ቱ የጋምቤላ ተወላጆች እንዲፈቱ አለማቀፍ ድርጅቶች ጠየቁ
መስከረም ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ መንግስት የአለም ባንክ የቋንቋ አስተርጓሚውን ፓስተር ኦሞት አግዋን ጨምሮ አሽኔ አስቲንና ጀማል ኦማር ሆጀሌ የተባሉ ለጋምቤላ ህዝብ መብት መከበር የሚታገሉ ሰዎች የምግብ ዋስትናን በተመለከተ ለስብሰባ ወደ ናይኖቢ ኬንያ ሲያመሩ ቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ ላይ መያዛቸውን በመጥቀስ፣ ግለሰቦቹ የቀረበባቸው የሽብረተኝነት ክስ ውድቅ ሆኖ በአፋጣኝ እንዲፈቱ 6 አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ...
Read More »ረሃቡ የጠናባቸው ሰዎች ወደ ጎዳና እየወጡ ነው
መስከረም ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጌዲዮ ዞን ከድርቅ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ረሃብ ተከትሎ በርካታ ዜጎች ወደ ከተማ እየፈለሱ ሲሆን፣ እርዳታ ማግኘት ባለመቻላቸው ጎዳና ላይ ማደር መጀመራቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ያሰማሩዋቸው ባለሙያዎች በዞኑ 80 ሺ ህዝብ መራቡን ሪፖርት ሲያደርጉ፣ የዞኑ የመንግስት ባለስልጣናት በተቀራኒው በዞናቸው ምንም የተራበ ሰው የለም የሚል ሪፖርት አቅርበዋል። ማንነታቸው ...
Read More »የመንግስትን ቀጣይ እቅድ አስመልክቶ ለውውይት የተጠራው የአዲስ አበባ ህዝብ “ያልተጠበቁ” ጥያቄዎችን አነሳ
መስከረም ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ መስተዳድር የኢህዴግ ድርጅት ጽ/ቤት ፣ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ረቂቅ ዕቅድ ዙሪያ በከተማው 10 ክ/ከተሞች በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ የህ/ብ ክፍሎችን በሚያወያይበት መድረክ ፣ ነዋሪዎች አወያይ ካድሬዎችን ያስደነገጡ ጥያቄዎችን አንስተዋል። በጉለሌ ክ/ከተማ ስር የሚገኙ የ10 ወረዳዎችን የህብረተሰብ ክፍል በያዘው የወረዳ 9 አዳራሽ በርካታ ጥያቄዎች መነሳታቸውን ስብሰባውን የተካፈሉ ዜጎች ለኢሳት ...
Read More »በኢትዮጵያ የመኪና አደጋ ከፍተኛ ገዳይ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ
መስከረም ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመኪና አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ የሰዎችን ሕይወት ቀጣፊ ከሆነባቸው አገራት ተርታ ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ አገር መሆኗን የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት በሪፖርቱ ገልጿል።ድርጅቱ ከመቶ ሺህ ተሽከርካሪዎች ውስጥ 3 ሺ 874 ሰዎች ለሞት እንደሚጋለጡና 80 % የሚሆነው የአደጋው ምንጭ የአሽከርካሪዎች ጥፋት ሲሆን፣ የተቀረው 20 በመቶ ደግሞ በመንገድ ችግሮች መሆኑን ጥናቱ አመልክቷል። ባለፈው ዓመት ብቻ ...
Read More »