መስከረም ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ችግር በማጋለጥ እንዲሁም የተለያዩ የሰብአዊ ድጋፎችን በማድረግ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ግሩም ተክለሃይማኖት ፣ በየመን የጸጥታ ሃይሎች መታሰሩ ታውቋል። ጋዜጠኛ ግሩም በምን ምክንያት እንደታሰረ የታወቀ ነገር የለም። ኢሳት ባለቤቱን ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም አልተሳካለትም። በየመን በመካሄድ ላይ ያለውን አስከፊ ጦርነት ተከትሎ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ግፍ እንዲሁም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ...
Read More »Author Archives: Central
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዘረኝነት እየተወነጀለ ነው
መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአጼ ሃይለስላሴ ዘመን ስራውን የጀመረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በትርፋማነቱ በተለያዩ አለማቀፍ የንግድ ተቋማት እየተመሰገነ ቢመጣም፣ የድርጅቱ ሰራተኞች ” ከዘረኝነት ጋር በተያያዘ ክሶችን እያቀረቡ ነው። አየር መንገዱ ጀምሮት ከነበረው የቁልቁለት ጉዞ የታደጉት አቶ ግርማ ዋቄ ስራቸውን ከለቀቁ በሁዋላ፣ በምትካቸው የተሾሙት አቶ ተወልደ ገብረማርያም ፣ ድርጅቱን ሙሉ በሙሉ በአንድ ብሄር ሰዎች ለማስያዝ እንቅስቃሴ ...
Read More »ቤት ሰሪ የመንግሰት ሰራተኞች አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸውን ገለጹ
መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህርዳር ከተማ የ1997ቱን ምርጫ ውጤት ተከትሎ በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብቶ የነበረው ኢህአዴግ የህዝቡን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ በሚል የቤት ፈላጊዎችን በማህበር ካደራጀ በሗላ ፣ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በየወሩ እንዲቆጥቡ በማድረግ ከ9 ዓመታት በሗላ የቤት መስሪያ ቦታቸውን ለቤት ሰሪዎች ሰጥቷል፡፡ ይሁን እንጅ ቤቱን መስራት የሚችሉት መንግስት ባወጣላቸው የቤት እቅድ መሰረት ባለፎቅ ቤት ...
Read More »ለመስቀል የታሰበው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በድጋሚ ተሰረዘ።
መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ለአዲስ አመት ዋዜማ በላፍቶ ሊያዘጋጀው የነበረው ኮንሰርት በመሰረዙ በአድናቂዎቹ ዘንድ የፈጠረው ቅሬታ ሳይረሳ ፣ አሁን ደግሞ ለመስቀል በአል ያዘጋጀው ኮንሰርት በድጋሚ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዳይካሄድ መከልከሉን የፎርቺን ሳምንታዊ ጋዜጣ ዘገባ ያመለክታል። የአዲስ አበባ መስተዳድር የካቢኔ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አቶ ፈለቀ ነጋሽ የ አዲስ አመት ኮንሰርቱ የተሰረዘው በአስተባባሪዎቹ የፈቃድ ...
Read More »ብሪታኒያ በደርዘን የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ ልትልክ ነው።
መስከረም ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን እንዳስታወቁት ወታደሮቺ የሚላኩት አልሸባብን እየተዋጉ ላሉት የ አፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ልዑክ ድጋፍ ለመስጠት ነው። በመሆኑም እስከ 70 የሚደርሱ የ እንግሊዝ ወታደሮች በቅርቡ የሰላም አስከባሪ ልኡኩን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ብሪታኒያ ከዚህም በተጨማሪ እስከ 300 የሚደርሱ ወታደሮቿን በደቡብ ሱዳን እንደምታሰፍር የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል። ውሳኔውን አስመልክቶ በመንግስታቱ ድርጅት ...
Read More »የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት (IOM) 387 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከማላዊ ሊመልስ ነው
ኢሳት ዜና (መስከረም 14 ፣ 2008) በማላዊ እስር ቤቶችን የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኙ 36 ህጻናትን ጨምሮ 387 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደሃገራቸው ለመመለስ ከአሜሪካ መንግስት በኩል ድጋፍ መገኘቱን የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት (IOM) ዛሬ አርብ ገለጠ። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ወደ ማላዊ በህገወጥ መንገድ ገብታችኋል ተብለው የተላለፈባቸውን የዘጠኝ ወራት የእስር ቅጣት ቢያጠናቅቁም ወደኢትዮጵያ የሚመልሳቸው አካል በመጥፋቱ በእስር ቤት ለወራት መቆየታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ...
Read More »ግብፅ የአባይን ግድብ ሁኔታ በልዩ ሳተላይት እንደምትከታተል አስታወቀች
ኢሳት ዜና (መስከረም 14 ፣ 2008) የግብፅ መንግስት በመገንባት ላይ ያለውን የአባይ ግድብን በልዩ የሳታላይት ቴክኖሎጂ እየተከታተለ እንደሆነ ዛሬ አርብ ይፋ አደረገ። ሰሞኑን በግብፅ መገናኛ ብዙሃን በግድቡ የውሃ መሙላት ሂደት በግብፅ ላይ የውኋ እጥረት ተፈጥሯል ሲሉ ላቀረቡት ዘገባ ምላሽን የሰጡት የሃገሪቱ ባለስልጣናት፣ በሳተላይት ቴክኖሎጂ በደተረገ ክትትል ግድቡን በውሃ የመሙላት ስራ እንዳልተጀመረ ሊረጋገጥ መቻሉን ገልጸዋል። በግብፅ የመስኖ ልማት ሚኒስትር ሆሳም ሆግሃዚ ...
Read More »አርበኞች ግንቦት7ን ለመቀላቀል ጥያቄ የሚያቀርበው ህዝብ ቁጥር ጨምሯል
መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከድርጅቱ በተገኘው መረጃ መሰረት በቀን ውስጥ ወደ ንቅናቄው ከሚደውሉ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ስልኮች መካከል 80 በመቶው ፣ ንቅናቄውን ለመቀላቀል መረጃ የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው። በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣው ደግሞ የማበረታቻ ሃሳቦችን ለመስጠት የሚፈልጉ ሰዎች ሲሆኑ፣ 2 በመቶ የሚሆነው ደግሞ መረጃ ለመስጠት የሚፈልገው ነው። የድርጅቱ የስልክ መረጃ አያያዝ እንደሚያመለክተው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለድርጅቱ የሚደወሉ ስልኮች ...
Read More »የአሜሪካ ኤምባሲ የኢትዮጵያን የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማስረጃ (TVET) እንደ ትምህርት ማስረጃ እንደማይቀበለው ገለጸ
መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኤምባሲው የ2015 የዲቪ ሎተሪ የመጨረሻ ቀን ረቡዕ መስከረም 19 ቀን 2008 ዓ.ም. መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን የቴክኒክና ሙያ የትምህርት ማስረጃን እንደሁለተኛ ደረጃ የትምህርት ማስረጃነት ከዚህ ቀደም ሲቀበል መቆየቱን በማስታወስ ከአሁን በኃላ የማይቀበል መሆኑን አስታውቆአል፡፡ ኤምባሲው ይህን ለምን እንዳደረገ በመግለጫው የጠቀሰው ነገር ባይኖርም የኤምባሲው ምንጮች እንደጠቆሙት የአሜሪካ መንግስት የትምህርት መስፈርት ለውጥ ሊያደርግ የተገደደው ...
Read More »ሀዲያ ውስጥ በአባ ሰንጋ በሽታ ሰዎችና ከብቶች እየሞቱ ነው
መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በሀዲያ ዞን “አባ ሰንጋ” የተሰኘው የከብቶች በሽታ ተከስቶ በርካታ ሰዎችና ከብቶች ለሞት እየተዳረጉ መሆናቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በስፍራው የሚገኘው ዘጋቢያችን እንዳጠናቀረው መረጃ እስካሁን በበሽታው አስራ ስድስት ሰዎች ሞተዋል። በበሽታው እጅግ በርካታ ከብቶች እያለቁ በመኾናቸውም የ አካባቢው ህዝብ መጪውን የመስቀል በዓል ከስጋ ተዋጽኦ ውጪ እንዲውል ተገዷል። በአሁኑ ወቅት ለተወሰኑ ...
Read More »