Author Archives: Central

የብአዴን የቀድሞ ታጋዮች መንገድ ላይ ወጥተው በመለመን ላይ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን የተመሰረተበትን 35ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ በማድረግ የተለያዩ ጋዜጠኞችንና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ያካተተ ጉዞ ላይ ፣ የትግል ተሞክሮ እንዲያካፍሉ የተጋበዙት የቀድሞ ታጋዮች በርካታ ጓዶቻቸው መጠለያ በማጣት በየከተማው በላስቲክ ቤት መንገድ ላይ እንደሚኖሩ ለጎብኝዎች ተናግረዋል፡፡ ‹‹ ህዝብ እንደኖረው ለመኖር ዕድሉን አልተሰጠንም፡፡ ›› የሚሉት ነባር ታጋዮች ...

Read More »

በአዋሽ መልካሳ አንድ የፌደራል ፖሊስ ተገደለ

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፖሊሱ የተገደለው በከተማዋ ውስጥ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር ተጣልቶ ነው። ፖሊሶች አንድ የግሮሰሪ ሰራተኛን ሲደበድቡ ፣ ወጣቶች በብስጭት በፌደራል ፖሊሱ ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ለማወቅ ተችሎአል። በከተማዋ ከፍተኛ ግርግር መኖሩን የተናገሩት ነዋሪዎች፣ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ገዳዮችን ለመያዝ ጥረት እያደረጉ ነው። የከተማው ወጣቶች የፌደራል ፖሊስ አባላት ከፍተኛ የሆነ ጫና እንደሚፈጥሩባቸው ለኢሳት ገልጸው፣ አሁኑ እርምጃም ...

Read More »

የአለም የመገናኛ ብዙሃን ስለኢትዮጵያ ድርቅ ሰፊ ሽፋን በመስጠት ላይ ናቸው

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከታላላቆቹ የአለም የመገናኛ ብዙሃን መካከል ዘ ኒውዮርክ ታይምስና ቢቢሲን ጨምሮ በርካታ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ስለተከሰተው ድርቅ የዜና ሽፋን በመስጠት ላይ ሲሆን፣ ዘ ኒዮርክ ታይምስ ባወጣው ዘገባ ድርቁ አሳሳቢ መሆኑን ገልጿል። “ያሲን ሙሃመድ ከአነስተኛ የእርሻ ማሳው ላይ እየወሰደ ጫት ይቅማል፣ ለምን ተብሎ ሲጠየቅ ፣ ጫት ረሃብን ያስታግሳል “የሚል መልስ መስጠቱን የዘገበው ዘ ኒዮርክ ...

Read More »

የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አባላት ለሌላ ቀን ተቀጠሩ

ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስብሰባ አውካችሁዋል በሚል ወንጀል የተከሰሱት የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ ማህበራዊ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አለነ ማህፀንቱና የቀድሞ የፓርቲው አባል አቶ እስማኤል ዳውድ መከላከያ ምስክሮቻቸውን ሳያሰሙ እንደተቀጠሩ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡ አቶ እስማኤል ዳውድና አቶ አለነ ማህፀንቱ እስር ቤቱ” መኪና ላገኝ ስላልቻልኩ” ተከሳሾቹን ላቀርብ አልቻልኩም፤ በማለቱ የተነሳ መዝገባቸውን እየተመለከተ የሚገኘው የአራዳ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 5ኛ ...

Read More »

ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት የዲጂታል ሸግግር በሙስና ምክንያት በታቀደው መሰረት ሳይሳካ ቀረ

ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን ጨምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል ለሚደረግ የቴክኖሎጂ ሽግግር ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ቢደረግም አልተሳካም። ፕሮጀክቱ በ2001 ዓም ተጀምሮ በ3 አመታት ውስጥ መጠናቀቅ ነበረበት። ከብሮድካስት ባለስልጣን የወጣ መረጃ እንደሚጠቁመው ስራው ሊሳካ ያልቻለው በሙስናና በብልሹ አሰራር ምክንያት ነው። ሀገር አቀፍ የሬዲዮና የቴሌቭዥን የማስፋፊያ ማሻሻያ በ2001 ተጀምሮ በሁለት ዓመት ...

Read More »

የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ የዋጋ ንረቱን እያባባሰው ነው ተባለ

ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገሪቱ የሚታየው የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እጥረት ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ ለታየው አጠቃላይ የዋጋ ንረት መባባስ አንድ ምክንያት መሆኑን ከንግድ ሚኒስቴር የተገኘ አንድ የጥናት ሰነድ ጠቆመ፡፡ በምግብ ነክ ምርቶች ላይ ማለትም በምግብ ዘይት፣ ዱቄት፣ ፓስታና ሞኮረኒ፣ በዳቦ ምርቶች ላይ የተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ አንዱስትሪዎች በኤሌክትሪክ እጥረት ምክንያት ከማማረት አቅማቸው በታች ለማምረት በመገደዳቸው በገበያ ላይ ...

Read More »

በሽብርተኝነት ሕግ ተከሰው አንድ ዓመት ከአምስት ወራት በእስር ሲንገላቱ የቆዩት የዞን ፱ ጦማሪያን በነጻ ተሰናበቱ

ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንደኛ ተከሳሽ ሶሊያና ሽመልስ በሌለችበት፣ሶስተኛ ተከሳሽ ናትናኤል ፈለቀ ፣ አምስተኛ ተከሳሽ አጥናፍ ብርሃኔ፣ስድስተኛ ተከሳሽ አቤል ዋበላ፣ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ የተሰናበቱ ሲሆን፣ ሁለተኛ ተከሳሽ በፍቃዱ ኃይሉ ከሽብር ክስ ነፃ የተባለ ቢሆንም ማአከላዊ ምርመራ በኃይል እና በማሰቃየት የሰጠው ቃል ላይ አመፅ እንዳነሳሳ አምኗል በሚል በወንጀል ህጉ 257 መሰረት እንዲከላከል ይሁን እንጅ ዋስትና መጠየቅ እንደሚችል ...

Read More »

የኔዘርላንድስ ፖሊስ አንድ በቀይ ሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ ኢትዮጵያዊን አሰረ

ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማንነታቸው ያልተገለጸው የ61 አመቱ ኢትዮጵያዊ አምሰተልፊን በምትባል ከተማ ውስጥ የተያዙ ሲሆን፣ ግለሰቡን ወደ ኢትዮጵያ ይመለሱ ወይም አይመለሱ የሚልውን ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ የ90 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል። ግለሰቡ በደብረማርቆስና መተከል አውራጃዎች በርካታ ሰዎችን መግደላቸውንና ማሰራቸውን በውጭ አገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መረጃ መሰብሰቡን ፖሊስ አስታውቋል። በግለሰቡ ላይ ቀድም ብሎ የሞት ፍርድ ተፈርዶ የነበረ ቢሆንም፣ ...

Read More »

የአምባሳደር ዘውዴ ረታ የቀብር ሥነስርዓት በቅድስት ስላሴ በተክርስቲያን ተፈጸመ

ጥቅምት ፭ (አምት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ፣ዲፕሎማትና የታሪክ ተመራማሪ የነበሩት የቀድሞ አምባሳደር ዘውዴ ረታ ባለፈው ሳምንት እንግሊዝ ለንደን ውስጥ መንገድ ላይ በመውደቃቸው ባጋጠማቸው ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። አምባሳደር ዘውዴ በአዲስ አበባ ከተማ ነሐሴ 7ቀን 1927 ዓ.ም በወቅቱ ሥጋ ቤት ሠፈር ተብሎ በሚጠራውና በአሁኑ ወቅት ኦርማ ጋራዥ በሚባለው አካባቢ የተወለዱ ሲሆን የሦስት ልጆች አባትም ነበሩ። የኤርትራ ጉዳይ፣የተፈሪ መኮንን ...

Read More »

ዞን 9 ጦማሪያን በነጻ እንዲሰናበቱ ፍርድቤት ወሰነ

ኢሳት ዜና (ጥቅምት 5፡ 2008) የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድቤት በሽብርተኛ ወንጀል ክስ፣ የክስ ሂደታቸው በመታየት ላይ የነበሩ አራት ጦማሪያን ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ ዛሬ አርብ ወሰነ። በጦማሪያኑ ላይ የመጀመሪያ ዙር ውሳኔውን ይሰጣል ተብሎ የተጠበቀው ፍርድ ቤቱ በጦማሪያኑ ክሳቸውን መከላከል ሳያስፈልጋቸው በአንድ አመት በላይ የቆየው የእስር ጊዜያቸው አብቅቶ በነጻ እንዲሰናበቱ ትዕዛዝ መስጠቱ ታውቋል። ይሁንና ተከሳሽ በፍቃዱ ሃይሉ ከተመሰረበተ የሽብርተኛ ...

Read More »