ጥቅምት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኬንያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሳምብሩ ምስራቃዊ ኢዞሎ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ሎሲሳ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ገቡ ያላቸውን አስራ አምስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ማሰሩን አስታውቋል። ባለፈው እሁድ ሃያአራት፣ ሰኞ ደግሞ ስድስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአካባቢው በታጣቂዎች በከበባ መያዛቸውን ገልጸዋል።ስደተኞቹ በሕገወጥ መንገድ ካለምንም ሕጋዊ ፍቃድ ድንበር አቋርጠው እንደሚገቡና አስራ አምስቱ ኢዞሎ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን የጸጥታው ሹም ...
Read More »Author Archives: Central
የድርቅ አደጋው እስከ ነሃሴ 2008 ሊቀጥል እንደሚችል ተመድ አስታወቀ
ኢሳት (ጥቅምት 10 ፡ 2008) በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ እስከተያዘው አመት ማጠናቀቂያ ነሀሴ ወር ድረስ ቀጣይ ሊሆን እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዛሬ ማክሰኞ አሳሰበ ። በሀገሪቱ ተከስቶ ያለው የምግብ እርዳታ ፍላጎትም ከአራት አመት በፊት በአፍሪካ ቀንድ ተከስቶ ከነበረው አጠቃላይ መጠን ጋር ሲነጻጸር ከፍ ብሎ መገኘቱን ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። በጉዳዩ ዙሪያ ከለጋሽ ሀገራት የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ...
Read More »ኢትዮጵያ ተጨማሪ ገንዘብ ከግል ባንኮች ልትበደር ነው
ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረዩተርስ እንደዘገበው የኢህአዴግ መንግስት ባለፉት 10 ወራት 1 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከ20 ቢሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ከግል የውጭ አበዳሪ ባንኮች ከተበደረ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ 2 ቢሊዮን ዶላር ወይም 40 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመበደር በድርድር ላይ መሆኑን ረዩተርስ ዘግቧል። አዲሱ ብድር የኢትዮጵያን እዳ ከ32 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከ1 ትሪሊዮን 40 ቢሊዮን ብር ...
Read More »በአዲስ አበባ በርካታ የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ድርጅቶች እየፈሩሰ ነው
ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደገለጹት በአሜሪካ ጊቢ ፣ በአዲስ ከተማና በሌሎች አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ለአመታት ከኖሩበት ቤት ያለበቂ ካሳ እና ተለዋጭ ቤት ቤቶቻቸው እየፈረሰባቸው ነው። መንግስት ቤታቸው ለሚፈርስባቸው የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ተላዋጭ አድርጎ ቢሰጥም፣ ተከራዮች ግን ኪራዩን የመክፈል አቅም የላቸውም መንግስት ከህዝቡ ጋር ሳይማከር የሚወስደው እርምጃ፣ ከፍተኛ የኑሮ ቀውስ እየፈጠረ መሆኑን ...
Read More »የዞን 9 ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ የዋስ መብቱ ሲፈቀድለት የሎሚ መጽሔት አዘጋጅ በሌሉበት 18 ዓመት ተፈረደባቸው
ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድ ዓመት ከአምስት ወር በሽብር ክስ ተከሰው በእስር ሲንገላቱ የነበሩት የዞን 9 አምደ መረብ ጸሐፍት ውስጥ ብቻውን እንዲቀር ተደርጎ የነበረው ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ክሱን ውጪ ሆኖ እንዲከታተል የሃያ ሽህ ብር የዋስትና መብት የልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት19ኛ ወንጀል ችሎት በመፍቀዱ ከእስር ተለቋል። በተጨማሪም የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስምንተኛ የወንጀል ችሎት የሎሚ መጽሄት ...
Read More »እንግሊዝ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ ቅደሚያ እንድትሰጥ በድጋሜ ተጠየቀች
ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስር ላይ የሚገኙትን የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ህገወጥ እስር አስመልክቶ የእንግሊዝ ባለስልጣናት ነገ በሚጀመረው የኢትዮጵያና የእንግሊዝ የንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ላይ ሊያነሱት እንደሚገባ አቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚከታተለው ሪፕሪቭ የተባለው ተቋም ጠይቋል። የንግድ እና የኢንቨስትመንት ስብሰባው ከፍተኛ ቦታ የተሰጠው እንደመሆኑ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ግራንት ሻፕስ ለኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ...
Read More »ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ የ2015 ሽልማት አሸናፊ ሆነ
ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-18 የእስር አመታት በግፍ ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የፔን ካናዳ የ2015 አሸናፊ ሆነ መመረጡን ድርጅቱ አስታውቋል። ለብዙዎች የዲሞክራሲ ሃይሎች የጽናት ምልክት ተደርጎ የሚቆጠረው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ በሽብር ወንጀል ተከሶ ያለፉትን ሶስት አመታት በእስር ቤት አሳልፏል። የእስክንድር ስራዎቹ ድንበር እና ባህል ተሻጋሪ ናቸው በማለት ያወደሰው ድርጅቱ፣ 5 ሺ ዶላር የሚያሸልመው ...
Read More »የወልቃይት ነዋሪዎች ወደ ትግራይ መካለላቸውን እንደማይቀበሉት አስታወቁ
ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎች “መሰረታችን ሕገ መንግስቱ ነው ተብሎ የወልቃይት ነዋሪዎች ቋንቋን ብቻ መሰረት ያደረገና የሕዝቡን ስነ ልቦናዊ፣ ባሕላዊ ወግን ያላማከለና ያላጠቃለለ ክልላዊ አከላለል በማድረግ የወልቃይት ሕዝብ የማይፈልገውንና የማያምንበትን በመጫን በግድ ወደ ትግራይ እንድንካለል መደረጋችን በውስጣችን ያለውን ማንነታችንን በመጨፍለቅ እንድንቀበል እየተደረግን ነው ፣ዛሬ ስነ ልቦናችን የማይቀበለውን ሕወሃት በዘዴ ማንነታችንን ለማሸማቀቅ እየሞከሩ ነው” ብለዋል ። በማህበራዊ ...
Read More »አቶ አበበ ካሴ በማንነቱ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈፀመበት እንደሆነ ገለፀ።
ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ተከሶ በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚገኘው አቶ አበበ ካሴ እስር ቤት ውስጥ በማንነቱ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየደረሰብኝ ነው ሲል ለፍርድ ቤቱ አቤቱታውን አሰምቷል፡፡ በእነ አበበ ካሴ የክስ መዝገብ ሁለተኛ ተከሳሽ የሆነው አቶ ታጠቅ አስማረ የተከላካይ ጠበቃ ለማቅረብ ዛሬ ጥቅምት 9/2008 ዓ.ም ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት ለልደታ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት አቤቱታውን ...
Read More »በአዲስ አበባ የንግድ ተቋማት እየታሸጉ ናቸው
ኢሳት ዜና (ጥቅምት በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ አሜሪካን ግቢ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ሶስት ሺ የሚጠጉ የንግድ ተቋማት ቦታው ለልማት ይፈለጋል ተብሎ ንብረታቸው መታሸጉን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጡ። የንግድ ተቋማት መታሸግን ተከትሎም የአካባቢው ነዋሪዎች መሰረታዊ የፍጆታ እቅርቦቶችን ለማግኘት ተቸግረው እንደሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል። ወፍጮ ቤቶች ሱቆችና ምግብ ቤቶች ከታሸጉበት የንግድ ተቋመት መካከል እንደሚገኙበት የተናገሩት ነዋሪዎች የመንግስት አካላት የወሰዱት ...
Read More »