ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቤንሻንጉል ህዝብ ነጻ አውጭ ንቅናቄ፣ የጋምቤላ ህዝብ ነጻ አውጭ ንቅናቄ፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ንቅናቄ፣ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባርና የሲዳማ ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ” የህዝቦች የነጻነትና የዲሞክራሲ ጥምረት” የተባለ የጋራ ጥምረት መመስረታቸውን ለኢሳት በላኩት መግለቻ አስታውቀዋል። ጥምረቱ በመግለጫው ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን እድል በራሳቸው መወሰን የሚችሉበትን፣ በነጻ ምርጫ ስልጣን የሚይዙበትን መንገድ ለማፈላለግ ...
Read More »Author Archives: Central
ከ30 አመታት ወዲህ አስከፊ ነው ለተባለው ድርቅ እርዳታ ቢቀርብም በቂ አይደለም ተባለ
ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ክፍል ባወጣው ዘገባ፣ አገሪቱ ለገጠማት አስከፊ ረሃብ አንዳንድ የምእራብ አገራት እርዳታ እያደረጉ ቢሆንም፣ እርዳታው አሁንም በቂ አይደለም ብሎአል። አንዳንድ መንግስታት ለልማት በሚል ለመንግስት ሊሰጡት ያሰቡትን እርዳታ፣ለተጎጂዎች ለማዋል እያሰቡ መሆኑንም መጽሄቱ ገልጿል። በሶማሊ ክልል በኤሚ ወረዳ የሸበሌ ወንዝ በከፍተኛ ሁኔታ በመሙላቱ 700 የሚጠጉ ሰዎች በምስራቅ ኤሚ ወረዳ ...
Read More »የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬድዮ የተመሰረተበት 5ኛ ዓመት በአውስትራልያ ብሪዝቤን ከተማ በልዩ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ።
ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቅዳሜ ጥቅምት 13 2007 ዓም በተካሄደው በዚህ ዝግጅት ላይ ነዋሪነታቸው በኪዊንስላንድ ግዛት የሆኑ የሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የታደሙበት ሲሆን ለንደን ከሚገኘው የኢሳት ማሰራጫ ጣቢያ ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀጸላ ተገኝታ ከነዋሪዎቹ ጋር ውይይት ተካሂዷል። ዝግጅቱን በቡራኬ የከፈቱት በብሪዝበን የደብረ ጸሃይ ቅዱስ ጊዎርጊስ ቤ/ክ አስተዳዳሪ ቀሲስ መንግስቱ ሃይሉ ሲሆን እሳቸውም ከቡራኬው አስከትለው ባደረጉት ንግግር ሃገራችንና ...
Read More »በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት እነ ዘመነ ምህረት ስርዓቱን በፍርድ ቤት አወገዙ
ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ ጌትነት ደርሶ ” ‹‹ሽብር ተፈፅሞብኛል እንጅ አሸባሪ አይደለሁም››፣ ‹‹ፍትህ ቢኖር ኖሮ እኔ ሳልሆን ወያኔና ግብረ አበሮቹ ነበሩ እዚህ መቆም የነበረባቸው›› ሲል፣ አቶ ዘመነ ምህረት ደግሞ ” ‹‹የተከሰስኩት ድርቡሽ እንኳ ያልደፈረውን የጎንደር ጥምቀት ላይ ፈንጅ ልታፈነዳ ነበር ተብዬ ነው፡፡ ምርመራ ላይ ግን ለምን የመኢአድ አባል ሆንክ ይሉኛል›› ማለቱን ለኢሳት የደረሰው ...
Read More »ሙስሊሙ ማህበረሰብ በመንግስት ላይ ቅሬታውን እየገለጸ ባለበት ወቅት መጅሊሱ የጸሎት ስነስርአት አደረገ
ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሳውድ አረቢያ በጸሎት ስነስርአት ላይ በነበሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ከፍተኛ አደጋ ተከትሎ መንግስት የሃዘን መግለጫ ባለመውጣቱና ሰንደቅ አላማም ዝቅ ብሎ ባለመውለብለቡ የሃይማኖቱ አባቶች ቅሬታቸውን እየገለጹ ባለበት ወቅት፣ የእስልምና ምክር ቤቱ ሟቾቹን ለመዘከር የጸሎት ስነስርዓት አድርጓል። በአብዛኛው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው መጅሊሱ፣ ያካሄደውን የጸሎት ስነስርአት አንዳንድ የሃይማኖት አባቶች የለበጣ ...
Read More »እነ ፓስተር ኦሞት አግዋ በድጋሜ ተቀጠሩ
ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት ፓስተር ኦሞት አግዋ ፡ አሽኔ አስቲንና ጀማል ኡመር ትናንት ፍርድ ቤት ቀርበው በድጋሜ ለጥቅምት 25 ተቀጥረዋል። ቀጠሮ የተሰጠው ሁለተኛው ተከሳሽ አቶ አሽኔ አስቲን የምክር ቤት አባል በመሆናቸው፣ ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ በመታሰራቸው ፣ ጉዳዩን ለማየት ነው። እነፓስተር ኦሞት የታሰሩት የውጭ አገር የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በክልሉ ...
Read More »የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአየር ላይ አደጋ ተረፈ
ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሶስት መቶ መንገደኞችን ጭኖ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በደብሊን አድርጎ ወደ አሜሪካ ሲጓዝ የነበረው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው ድሪምላይን 787-8 አውሮፕላን ዛሬ ማለዳ ላይ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር በድንገት አንድ ሞተሩ አየር ላይ ቢጠፋም በአየርላንድ ዋና ከተማ ደብሊን በሰላም ማረፍ ችሏል። መንገደኞቹ ከጀርመን ፍራንክፈርት በተላከ ተቀያሪ አውሮፕላን ወደ አሜሪካ ማቅናታቸውን ሜይል ...
Read More »ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በግብጽ ታሰሩ
ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡባዊ ግብጽ ሉዞር ላይ በባቡር አድርገው በህገወጥ መንገድ የግብጽን ድንበር ተሻግረው የገቡ አስራ አንድ ሶማሊያዊያን እና አስር ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን መያዛቸውን የአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች ምንጭ ጠቅሶ ዮም ሰበን ዘግቧል። በህገወጥ መንገድ በግብጽ አድርገው ወደ ሊቢያ የሚገቡ ስደተኞች በቅርብ ጊዜያት ውስጥ እየበዙ መሆናቸውንና ከ2 ሺ 215 በላይ ሕገ ወጥ ስደተኞች ባለፈው መስከረም ...
Read More »የሞያሌ ወጣቶች ለውትድርና ምዝገባ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ አደረጉት
ጥቅምት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ሞያሌ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ወጣቶችን ለውትድርና ለመመዝገብ በድምጽ ማጉያ የታገዘ ቅስቀሳ ቢያካሂዱም፣ አንድም ለምዝገባው ፈቃደኛ ሆኖ የሄደ ወጣት አለመኖሩን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ። ወጣቶቹ የተደረገላቸውን የስብሰባ ጥሪ ባለመቀበላቸውም፣ መንግስት በሞያሌና አካባቢዋ አዳዲስ ምልምል ወታደሮችን ለመመዝገብ ያቀደው እቅድ ሳይሳካ ቀርቷል። አምና 10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ወጣቶችን ለወትድርና ለመመዝገብ ማቀዱን የገለጸው መንግስት፣ ሂደቱ ...
Read More »ብአዴን ለበአል ማክበሪያ በሚል ህዝቡን በመዋጮ እያስጨነቀው ነው
ጥቅምት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-35ኛ አመቱን ለማክበር በዝግጅት ላይ ያለው ብአዴን ፣ በአማራ ክልል የሚኖረው ህዝብ ለበአሉ ማድመቂያ ገንዘብ እንዲያዋጣ እያስገደደ ነው። ነጋዴዎች ከብአዴን ጽ/ቤት የተጣለባቸውን ክፍያ ያለፍላጎታቸው በግድ እንዲከፍሉ ታዘዋል። ከፍተኛ የረሃብ አደጋ በክልሉ ባንዣበበት በዚህ ወቅት፣ ብአዴን እንደ ህወሃትና ኦህዴድ መቶ ሚሊዮኖችን አፍስሶ በአሉን ለማክበር መሞከሩ ፣ ከታሪክ አለመማሩን ያሳያል የሚሉት አንድ በክልሉ ...
Read More »