ኢሳት (ታህሳስ 21 ፣ 2008) በጋንቤላ ክልል 100ሺ ሄክታር መሬትን በርካሽ ዋጋ ለ 50 ዓመታት ተረክቦ የነበረው የህንዱ ካራቱሪ ኩባንያ ከመንግስት ጋር የነበረው ውል ተቋረጠ። ድርጅቱ ከመንግስት የተሰጠውን ወደ 60 ሚሊዮን ብር ብድርም መክፈል ሳይችል የቀረ ሲሆን፣ ከተረከበው 100ሺ ሄክታር መሬት ውስጥ ባልፉት ስድስት አመታት 1ሺ 200 ሄክታር መሬት ብቻ ማልማቱ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ግብርና ኢንቨስትመንት መሬት አስተዳደር ኤጀንሲ የህንዱ ኩባንያ ...
Read More »Author Archives: Central
በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን አፈና ተጠናክሮ እንደቀጠለ አንድ አለም አቀፍ ተቋም ገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 21 ፣ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት በሃገር ውስጥ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ አለም አቀፍ ትኩረትን እንዲያገኝ ለማድረግ ከውጭ ሃገር የሚሰራጩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ የቁጥጥር ዘመቻ መክፈቱን ግሎባል ቦይስ የተሰኘ አለም አቀፍ ተቋም ይፋ አደረገ። በዚሁ የመንግስት ዘመቻም በ10 ሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ተከታታይ ያለው ኢሳት እና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ስርጭት መስተጓጎሉን በሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ የሚሰራው ተቋም አስታውቋል። በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመወን ግድያ ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል ሰዎች በገፍ እየታሰሩ ነው፣ አቶ በቀለ ነገአ እንደተደበደቡ ገለጹ
ኢሳት (ታህሳስ 21 ፣ 2008) በበርካታ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ከተቀሰቀሰው ተቃውሞ ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች እየታሰሩ እንደሆነ ከሃገር ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራሮች ላይ እየተካሄደ ባለው በዚሁ ዘመቻ ከ4ሺ የሚበልጡ አባላት ለእስር መዳረጋቸውን ገልጸዋል። ይሁንና የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ያለውን የእስር ዘመቻ በመቀጠሉ ቁጥሩ በየእለቱ እየጨመረ መምጣቱንና ትክክለኛ ቁጥሩን በአንድ ጊዜ መግለጽ አስቸጋሪ ኣየሆነ መምጣቱን ...
Read More »የአሜሪካ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት ከማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ እየወሰደ ያለው የእስር እርምጃ አሳስቦኛል አለ
በኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ያለው የእስር ዘመቻ ስጋት እንዳሳደረበት የአሜሪካ መንግስት በድጋሚ ገለጠ። ተቃውሞውን ተከትሎም ለእስር የተዳረጉት ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱና በሃገሪቱም ሃሳብን በነጻነት የመግለጥ መብቱ እንዲከበር አሜሪካ አሳስባለች። የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቃል-አቀባይ የሆኑት ኔድ ፕራይስ ሃገራቸው ለእስር የተዳረጉ ጋዜጠኞችንና ሌሎች ሰዎችም በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥያቄ ማቅረቧን ሃላፊው ዋቢ በማድረግ ...
Read More »በኦሮምያ ተቃውሞው መቀጠሉን ተከትሎ የጸጥታ ሃይሎች የተቃዋሚ መሪዎችን መሪዎችን ማዋከብ ቀጥለዋል
በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች ለሳምንታት ሲካሄድ የሰነበተው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎአል። በተለይ በምእራብ ሃረርጌዋ መቻራ ከተማ ህዝብ ነቅሎ በመውጣት ተቃውሞውን ሲያሰማ በሆድሮ ጉድሩ ደግሞ የተማሪዎችን ሰላማዊ ተቃውሞ ሌላ አቅጣጫ ለመስጠት በአካባቢው የተሰማሩት ወታደሮች በትምህርት ቤት ላይ ቦንብ ወርውረው አንድ ተማሪ መግደላቸውን የአሮሞ ፌደራሊስ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራርና የቀድሞው የፓርላማ አባል አቶ ገብሩ ገብረማርያም ለኢሳት ተናግረዋል። አቶ ገብሩ በክልሎ የሚካሄደው ተቃውሞ መንግስት እንደሚያስወራው ሳይሆን ...
Read More »አለም የፈረንጆችን የ2016 መግቢያ እያከበረ ነው
አውስትራሊያና ኒውዚላንድ 2016 ከሌላው አለም ቀድመው የተቀበሉ ሲሆን፣ በተለይ በአውሮፓ የጸጥታ ቁጥጥሩ በመጥበቁ የበአሉን ድምቀት እንዳይጎዳው ተሰግቷል። የአውሮፓ ህብረት መቀመጫዋ ቤልጂየም፣ በሽብር ስጋት ምክንያት በብራሰልስ ሊታደርግ ያሰበችውን ዝግጅት ሰርዛለች። የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ሲሉ ደርሸባቸዋለሁ ያለቻቸውን 6 ሰዎች ይዛ አስራለች። ፈርሳይም እንዲሁ በተለምዶ የምታደርገውን ዝግጅት መሰረዟን አስታውቃለች። ቱርክ በበአሉ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ሲዘጋጁ ነበር ያለቻቸውን 2 ሰዎች ይዛ ስታስር፣ ሩስያ በበኩሉዋ ...
Read More »የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ጥምረትና የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ንቅናቄ ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር አብረው እንደሚሰሩ አስታወቁ
ኢሳት (ታህሳስ 19 ፣ 2008) በቅርቡ ግንባር የፈጠሩት የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ጥምረት እና የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ንቅናቄ የጀመሩትን ትግል በቁርጠኝነት ለማካሄድ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር በመሆን የጋራ የትግል ስምምነቶን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ወሰኑ። የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ጥምረት ግንባርን የመሰረቱት ድርጅቶቹ የተጀመረውን ትግል ለማጠናከርና ከግብ ለማድረስ በጋራ መስራትን ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። “የጋራ ትግላችን ፈርጀ ሰፊና፣ ሁሉን አቀፍ ነው” ሲል የገለጸው ...
Read More »በኦሮምያ ክልል ልዩ የቁጥጥር ስርዓት ተዘረጋ
ታኀሳስ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በክልሉ የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ ፖሊስ አዲስ የቁጥጥር ስርዓት ዘርግቶ ህዝቡን በማስፈራራት ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ማንኛውም ሰው በክልሉ በሚገኙ ሆቴሎች አልጋ ለመያዝ እንዲሁም ለስራ ወይም ለሌሎች ጉዳዮች ሲንቀሳቀስ ከተገኘ ተይዞ ይጠየቃል:፡ በተለይ ሆቴሎች አዲስ ልዩ ቅጽ እንደሚሉ እየተገደዱ ሲሆን፣ በቅጹ ላይ አልጋ የሚይዘው ሰው በአካባቢው ለምን እንደተገኘ መናገር ይኖርበታል። የሆቴል ...
Read More »በአባይ ግድብ ስምምነት ዙሪያ ግብጾች ደስታቸውን እየገለጹ ነው
ታኀሳስ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሱዳን፣ ግብጽና ኢትዮጵያ መካከል ካርቱም ላይ የተፈረመው ስምምነት የግብጽ ባለስልጣናትን ማስደሰቱን የተለያዩ የግብጽ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው። አህራም ኦን ላይን የግብጽ የመስኖ ሚኒስትርን ጠቅሶ እንደዘገበው ስምምነቱ የግድቡን አጠቃላይ አሰራር የሚገመግሙት ሁለቱ የፈረንሳይ ኩባንያዎች ውሳኔ እስከሚሰጡ ድረስ ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ የምታደርገውን ግንባታ እንድታቋርጥ እንዲሁም በግድቡ ውሃ ለመሙላት እንደማትችል በወረቅት ላይ ስምምነቷን መግለጿን ተናግረዋል። ...
Read More »ከታገደ ከአንድ አመት ተኩል በላይ ያስቆጠረውን የውጭ አገር ስራ ስምሪት ያስጀምራል የተባለ አወዛጋቢ አዋጅ በትላትናው እለት ፖርላማው አፀደቀ።
ታኀሳስ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አዋጁ በተለይ ወደአረብ አገራት የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያን ቢያንስ ስምንተኛ ክፍል እንዲያጠናቅቁና በሚሰማሩበት መስክ ቢያንስ የሶስት ወራት ተጨማሪ ስልጠና እንዲወስዱ ያስገድዳል። በተጨማሪ ከኤጀንሲዎች ውጪ በግል ግንኙነት ስራ ዜጎች ቢያገኙም እንዳይቀጠሩ ይከለክላል። አዋጁ በተለይ የትምህርት እድል ያላገኙ በገጠር የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያንን በውጭ አገር እንኩዋን ሰርተው እንዳይበሉ ያደርጋል በሚል ነቀፋ ሲሰነዘርበት ቆይቶአል። እነዚህ ተቺዎች መንግስት ...
Read More »