Author Archives: Central

በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ሰበብ እየሞቱ ያሉ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው ተባለ

ኢሳት (ጥር 6 ፥ 2008) ሁለተኛ ወሩን በያዘው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ፣ በየዕለቱ የሚገደሉ ሰዎችና ለእስር የሚዳረጉ ተማሪዎች ቁጥር በማሻቀብ ላይ መሆኑ ሂውማን ራይትስ ዎች አርብ ጃንዋሪ 15 አስታወቀ። በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ቀጥሎ በሚገኘው በዚሁ ተቃውሞ የሟቾችንም ሆነ ለእስር የተዳረጉ ነዋሪዎችን ቁጥር በአግባቡ ማወቅ እንዳልተቻለም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጀት ለሁለተኛ ጊዜ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። ሃሙስ ከሌሎች ሁለት አለም ...

Read More »

ሂውማን ራይትስ ወች “መንግስት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን መሰረዙ ለተቃዋሚዎች ትልቅ ድል ቢሆንም ውሳኔው ዘግይቷል” አለ

ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሂውማን ራይትስ ወቹ ፍሊክስ ሆርን ፣ ደም አፋሳሽ ከሆነው የ9 ወራት ተቃውሞ በሁዋላ መንግስት ተቃዋሚዎች ላቀረቡት ጥያቄ ፣ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመሰረዝ መልስ ቢሰጥም፣ ኦሮምያን ለማረጋጋት ግን የዘገየ ውሳኔ ነው ብሎአል። መንግስት ተቃዋሚዎች ላቀረቡት ጥያቄ መልስ መስጠቱ ያልተለመደ ነው የሚለው ሆርን፣ ለተቃዋሚዎች ደግሞ ትልቅ ድል ነው መሆኑን ገልጿል። በመጀመሪያ ተቃውሞው ...

Read More »

“ያለንበት ዘመን ጨለማና መከራ የበዛበት ነው”ሲሉ አርሶአደሮች ተናገሩ

ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በድርቁ በተጎዱ የአማራ ክልል አካባቢዎች በመዘዋወር ተጎጂዎችን ለተመለከቱት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ያለባቸውን ችግር የተናገሩት አርሶአደሮች ‹‹ አሁን ያለንበት ዘመን አስከፊ የሆነ አሰቸጋሪ ጊዜ ነው ፡፡››በማለት እየደረሰባቸው ያለውን የውሃ ችግር በምሬት ቢናገሩም እስካሁን ምንም መፍትሄ እንዳልተሰጠ ተጊጂዎች ቅሬታቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ የደረሰብን ድርቅ ታይቶ የማይታወቅ እጅግ አሳዛኝ ነው ›› ያሉት ተጎጂዎች ዛሬ የደረሰብን ...

Read More »

በሽብር ሕግ የተከሰሰው ሙባረክ ይመር በቂሊንጦ እስርቤት አረፈ

ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ሆን ብሎ ባቀነባረው የሽህ ኑሩ ግድያ ላይ እጁ አለበት በማለት ተወንጅሎ ፍርዱን ሲጠባበቅ የነበረው ሙባረክ ይመር በቂሊንጦ እስርቤት ሕይወቱ አልፏል። በእነ አሕመድ እንድሪስ መዝገብ 9ኛ ተከሳሽ የነበረው ሙባረክ ይመር ፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ በሰላም ደርሶ ከተመለሰ በኋላ በድንገት ታሞ ወደ ሕክምና ማእከል ቢወሰድም ሊተርፍ አልቻለም። ሙባረክ ይመርን ለሞት ያበቃው የጤና እክል ...

Read More »

በሰርጉ ዋዜማ በጥይት የተመታው መምህር ፍጹም አባተ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ቀዶ ጥገና ተደረገለት

ኢሳት (ታህሳስ 5 2008) በኢሊባቡር መቱ በሰርጉ ዋዜማ በጥይት የተመታው መምህር ፍጹም አባተ ህይወቱ አስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ከቤተሰቦቹ የተገኘው መረጃ አመለከተ። ታህሳስ 29 ቀን 2008 ዓ ም ጭንቅላቱን በጥይት የተመታው መምህር ፍጹም፣  በመቱ ሆስፒታል ከታየ በኋላ ለከፍተኛ ቀዶ ጥገና ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከዚያም ወደ ወደአለርት ሆስፒታል ተልኮ የነበረ ሲሆን በመጨረሻም ወደ ጥቁር አንበሳ ተመልሶ ቀዶ ጥገና እንደተደረገለት ...

Read More »

ከአምስት ሚሊዮን የሚበልጡ ህጻናት በድርቁ ሳቢያ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው ተባለ

ኢሳት (ጥር 5 ፣ 2008) ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ህጻናት ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ ምክንያት የሆነው የድርቅ አደጋ በ60 ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ ህጻናት ላይ ከፍተኛ ጉዳትን እያደረሰ እንደሚገኝ የህጻናት አድን ድርጅት (Save the Children) ሃሙስ ገለጠ። በድርቁ አደጋ ክፉኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ህጻናት ለመታደግም የአለም አቀፍ ማህበረሰብ አፋጣኝ ርብርብ ማድረግ እንዳለበት የብሪታኒያው የህጻናት አድን ድርጅት መጠየቁን አፍሪካን ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግቧል። የፊንላንድ፣ ኖርዌይ፣ የአሜሪካ ...

Read More »

ያለበቂ ካሳ ከገበሬ የሚወሰደው የመሬት ወረራ በኦሮሚያ ክልል ያለውን ተቃውሞ አባብሷል ተባለ

ኢሳት (ታህሳስ 5 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ከገበሬዎች መሬትን በመውሰድ ያለበቂ ካሳ ለባለሃብቶች ሲሰጥ የቆየው አካሄድ በኦሮሚያ ክልል ያለውን ተቃውሞ እንዲባባስ ማድረጉን ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ በተለያዩ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ሃሙስ ዘገበ። መንግስት ከገበሬዎች የሚፈልገውን መሬት ወስዶ በቂ ካሳና ምላሽ አለመስጠቱ ነዋሪዎችን አስቆጥቶ ተቃውሞው እንዲበረታ አድርጎታል ሲሉ ከአዲስ አበባ ከተማ በ60 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው አስጎሪ ከተማ የሚገኙ ገበሬዎች ለጋዜጣው ...

Read More »

አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በኢትዮጵያ ስላለው ግድያና የጅምላ እስር ምላሽን እንዲሰጥ ጠየቁ

ኢሳት (ጥር 5 ፣ 2008) አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጨምሮ ሶስት አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት፣ የአለም አቀፍ ማህበረሰብና የኢትዮጵያ የልማት አጋሮች በሃገሪቱ እየተካሄደ ስላለው ግድያና የጅምላ እስር በይፋ ምላሽን እንዲሰጡ ጠየቁ። የጋራ መግለጫን ያወጡት ድርጅቶቹ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ያለውን የሃይል እርምጃ ተባብሶ መቀጠሉንና ድርጊቱ ወደ አሳሳቢ ደረጃ መሸጋገሩን ገልጸዋል። ወርልድ አሊያንስ ፎር ሲቲዝንስ ፓርቲሲፔሽን (World Alliance for Participation) ኢስት ...

Read More »

ገዢው ፓርቲ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እያደረሰ ያለውን ጥፋት የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎች ተደረጉ

ጥር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች እና በሰሜን ጎንደር የገዢው ፓርቲ ታጣቂዎች በህዝቡ ላይ ያደረሱትን እልቂት የሚያወግዝ፣ በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች እንዲፈቱ የሚጠይቅ እንዲሁም ከሱዳን ጋር በመሬት ዙሪያ የሚደረገው ድርድር እንዲቆም የሚጠይቁ የተቃውሞ ሰልፎች በአውሮፓ ህብረት መቀመጫና ብራሰልስ እና በሙኒክ ጀርመን ተካሂደዋል። ከተለያዩ አጎራባች ከተሞች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ...

Read More »

በረሃብ ምክንያት በሰሜን ወሎ ወረዳዎች የሚኖሩ አርሶአደሮች ቀያቸውን እየለቀቁ ወደ ባህርዳር በመፍለስ ላይ ናቸው

ጥር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአካባቢያቸው በተከሰተው ድርቅ የሚበሉትና የሚቀምሱት እንዳጡ የሚናገሩት ስደተኞች፣ ሰሞኑን ባህርዳር ገብተዋል፡፡ በየመንገዱ በመለመን የእለት ምግባቸውን ለማግኘት እየሞከሩ መሆኑን በፎቶ አስደግፎ ዘጋቢያችን የላከው መረጃ ያሳያል፡፡ የክልሉ መንግስት ምንም አይነት እገዛም አላደረገላቸውም፣ ማረፊያ ቦታም አላዘጋጀላቸውም ፡፡ አብዛኞቹ ስደተኞች ሴቶችና ህጻናት ናቸው። ህብረተሰቡ ለዜጎቹ እገዛ በማደረግ ላይ ቢሆንም፣የአለማቀፍ ድርጅቶችም ሊጎበኙዋቸው እንደሚገባ ዘጋቢያችን አስተያየቱን አስፍሯል። ...

Read More »