Author Archives: Central

የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩት ዮናታን ተስፋዬ ላይ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ

ጥር ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባልፈፀመው ወንጀል በሽብር ክስ ተወንጅሎ በደኅንነት ኃይሎች ከመንገድ ታፍኖ ተወስዶ በእስር ላይ የሚገኘው የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው አቶ ዮናታን ተስፋዬ ላይ የአራዳ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለ2ኛ ጊዜ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶበታል፡፡ በአራዳ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥር 17 ቀን 2008 ዓ.ም. በዋለው ችሎት አቃቤ ሕግ ምርመራዬን አልጨረስኩም ተለዋጭ ...

Read More »

በአንዳንድ አካባቢዎች ነዋሪዎች መብራትና ውሃ ከተቋረጠባቸው 5 አመታትን ማሳለፋቸውን ተናገሩ

ጥር ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ ጎጃም ዞን የየስማላ ከተማ ነዋሪዎች መብራት ከተቋረጠባቸው 5 አመታትን ማሳለፋቸውን፣ በሰሜን ጎንደር ሃሙሲት ከተማ ደግሞ የከተማው ነዋሪዎች የቧንቧ ውሃ ከተቋረጠባቸው 5 አመታትን ማሳለፋቸውን ዘጋቢያችን ነዋሪዎችን አነጋግሮ የላከው ዘገባ ያሳያል። ነዋሪዎቹ ችግሮቻቸው እንዲፈቱላቸው በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ሰሚ አካል አላገኙም። በሞጣ ከተማ ደግሞ መብራት ከተቋረጠ 2 ወር ያለፈው ሲሆን፣ በቁንዝላ ከተማ ውሃ ...

Read More »

ታንዛኒያ ከመቶ በላይ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው ልትመልስ ነው

ጥር ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት ሲሞክሩ በድንበር ጠባቂዎች ባለፈው ወር በፖሊስ ተይዘው በእስር ሲንገላቱ የነበሩ 40 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ጨምሮ በዋና ከተማዋ ዳሬሰላም ካለ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩና ይሰሩ ነበሩ ያላቸውን ኢትዮጵያዊያ ስደተኞችን ወደ ትውልድ አገራቸው ለመለስ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የታንዛኒያ የአገር ውስጥ ሚንስቴር አስታወቁ። የአገር ውስጥ ሚንስቴሩ ቻርለስ ኪታዋንጋ እንዳሉት ”ካለ ሕጋዊ የመኖሪያ ...

Read More »

የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ከካርታ ስራ ድርጅት ወጥቶ በደህንነት መስሪያ ቤት እንዲሰራ መደረጉ መሬት እንደፈለጉ ለመስጠት እንዲመች ነው ተባለ

በመረጃና ደህንነት ኤጀንሲ ( ኢንሳ) ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ አንድ ከፍተኛ ባለሙያ ለኢሳት እንደገለጸው፣ የኢትዮጵያን የመሬት መረጃ የሚሰበስብ የኢትዮጵያ ካርታ ስራ ኤጀንሲ የተባለ መስሪያ ቤት ቢኖርም፣ መንግስት ፎቶ የማንሳቱ ስራ በኢንሳ ስራ ማድረጉ የተለያዩ አላማዎችን ለማስፈጸም ነው ይላል። የመረጃ ደህንነት ኤጀንሲ በአንድ ብሄር የተያዘ፣ ከመከላከያው ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው እንዲሁም ለወያኔ ድርጀቶችና ደጋፊዎች መሬት በመስጠት ፣ የወያኔን የፖለቲካ ኢኮኖሚ ደግፈው እንዲይዙ ...

Read More »

በኮንሶ ታጣቂ ሃይሎች ህዝቡን በማዋከብ ላይ ናቸው

ኮንሶ ራሱን ችሎ በዞን ደረጃ ሊተዳደር ይገበዋል በሚል ህዝቡ ከወራት በፊት ያነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የጸጥታ ሃይሎች የተለያዩ ወጣቶችና ጎልማሶችን ይዘው ካሰሩ በሁዋላ፣ ጥያቄው የአርበኞች ግንቦት 7 እንጅ የህዝቡ አይደለም ብላችሁ ፈርሙ በማለት ካለፉት 3 ሳምንታት ጀምሮ ቅስቀሳ ሲያካሄዱና ፊርማ ሲያሰባስቡ ቆይተዋል። ይሁን እንጅ ጥያቄው የአካባቢው ህዝብ በጉልበት ጥያቄያቸውን እንዲቀይሩ ለማድረግ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በመቃወማቸው፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፌደራልና የደቡብ ክልል ...

Read More »

በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ

ኢትዮጵያውያኑ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ጽ/ቤት ፊት ለፊት በመገኘት የመንግስት ወታደሮች በኦሮሞ እና በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አውግዘዋል። የሰልፉ አስተባባሪ ከሆኑት መካከል ዶ/ር ዘውዱ ነቺሳ ለኢሳት እንደገለጹት፣ የተለያዩ ጥያቄያቸውን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለአፍሪካ ክፍል አቅርበዋል። ጉዳዩን እንደሚከታተሉት ባለስልጣናቱ መግለጻቸውንና የተመድ ከፍተኛ ኮሚሽነር በተገኙበት ደብዳቤ ቀርቦላቸዋል። ኮሚሽነሩም ጉዳዩን በቅርብ እንደሚከታተሉት ቃል መግባታቸውን ዶ/ር ዘውዱ ገልጸዋል በተቃውሞ ...

Read More »

ገዢው ፓርቲ የህዝብን ተቃውሞ ለማብረድ የሚወስደው እርምጃ የይስሙላ ነው ሲሉ አባላቱ ገለጹ

ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ከሕዝቡ እየደረሰበት ያለውን ተቃውሞ ለማርገብ ከክልል አስከ ቀበሌ ባሉት መዋቅሮቹ አባሎቹን ማባረር ቢጀምርም ከፍተኛ አመራሩን ያላካተተ መሆኑ ከወዲሁ በራሱ አባሎች ተቃውሞ እያስከተለበት ነው። ኢህአዴግ በነሀሴ ወር 2007 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ ባካሄደው 10ኛው ድርጅታዊ ጉባዔው የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከፍተኛ ደረጃ መድረሳቸውን በማመን የማጥራት ሥራው ከከፍተኛ አመራሩ ጀምሮ እንዲካሄድ ውሳኔ ያሳለፈ ይሁን እንጂ ከፍተኛ አመራር ውስጥ በሙስና የሚጠረጠሩት ነባሮቹ ...

Read More »

ንግድ ሚኒስቴር በስኳር መሸጫ የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ አደረገ

ጭማሪው በኪሎ ግራም 3 ብር ከ40 ሳንቲም ሲሆን ከፍተኛ ነው በሚል እየተተቸ ነው፡፡ ሚኒስቴሩ ለዚህ ጭማሪ የሰጠው ምክንያት የማምረቻ ዋጋ ጭማሪ አሳይቶአል የሚል ቢሆንም ለስኳር ኮርፖሬሽን ቅርበት ያላቸው ምንጮች ግን መንግስት ከድርቁ ችግር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የሆነ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ በመግባቱና ስኳር መሠረታዊ ፍላጎት አይደለም በሚል እንዲጨመር መደረጉን ጠቁመዋል፡፡ የስኳር የማምረቻ ዋጋ በኪሎግራም ከ 7 ብር እንደማይበልጥ የጠቀሱት ውስጥ አዋቂዎች፣ ...

Read More »

በኦሮሚያ ዳግም ያገረሸው ተቃውሞ አርብ ቀጥሎ መዋሉ ተገለጸ

ኢሳት (ጥር 13 ፥ 2008) ከቀናት በፊት በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ዳግም ያገረሸው ተቃውሞ አርብ መቀጠሉን ከሃገር ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል። በምዕራብ ወለጋ እንዲሁም በምስራቁ ሃረርጌ አካባቢዎች በትንሹ ስድስት ሰዎች መገደል ምክንያት የሆነው ተቃውሞ ቀጥሎ የሚገኝ ሲሆን በርካታ ነዋሪዎችም ለእስር መዳረጋቸው ታውቋል። ከሁለት ሳምንት በላይ ትምህርትን ያቋረጡ ዩኒቨርስቲዎችም ትምህርታቸውን ያልጀመሩ ሲሆን የፌዴራልና የክልል ባለስልጣናት ተማሪዎችና ነዋሪዎች ምክክርን እያካሄዱ እንደሚገኝ ለመረዳት ተችሏል። ...

Read More »

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ላይ እርምጃን እንዲወስድ ተጠየቀ

ኢሳት (ጥር 13 ፥ 2008) ሃሙስ በኦሮሚያ ክልል የተፈጸሙ ግድያዎችንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ድርጊት ያወገዘው የአውሮፓ ህብረት 15 ነጥቦችን ያካተተ የውሳኔ ሃሳብ በማጽደቅ የአውሮፓ ህብረት እርምጃን እንዲወስድ መጠየቁ ተገልጿል። የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ቀጣይ ድጋፍም የሰብዓዊ መብት መከበሮችን እየመረመረ እንዲሆን የፓርላማ ቡድኑ አሳስቧል። የአውሮፓ ፓርላማ ያጸደቃቸው የውሳኔ ሃሳቦችም በቀጣይ ተግባራዊ ይደረጋሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ለዚሁ እርምጃ እስካሁን ድረስ ...

Read More »