የካቲት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትግራይ ክልል ስር ሆነው መተዳደራቸውን አጥብቀው የሚቃወሙት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ተወካዮች፣ የአማራ ክልል ፕ/ት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ “ጥያቄያቸው በሽማግሌዎች እየተጠና መሆኑንና በሽማግሌዎቹ ውሳኔ መሰረት የወሰን ማካለል ለማካሄድ መታቀዱን” መናገራቸውን እንዳልተቀበሉት የአዲስ አበባው ዘጋቢ ገለጸ። የወልቃይት ህዝብ ተወካዮች ፣ “ለስርአቱ በወገኑ ሽማግሌዎች ጥያቄያችን ምላሽ ያገኛል ብለን ተስፋ አናደርግም” በማለት በክልሉ የተሰጠውን መግለጫ ...
Read More »Author Archives: Central
በኦሮምያ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ በውጭ ሃይሎች የተፈጠረ አይደለም ሲሉ ጠ/ሚኒስትሩ ተናገሩ
የካቲት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከኦል አፍሪካ ጋዜጠኛ ሪድ ክራመር ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ዘጋርድያን ይዞት የወጣ ሲሆን፣ ጠ/ሚኒስትሩ በኦሮምያ የሚታየው የህዝብ ተቃውሞ ከስራ አጥነት እና ከመሬት ዝርፊያ ጋር የተያያዘ እንጅ የውጭ ተጽእኖ የለበትም ብለዋል። የስራ አጡ ቁጥር 16 በመቶ በላይ መድረሱን፣ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው እድሜው ከ30 አመት በታች መገኘቱን የገለጹት አቶ ሃይለማርያም፣ ለዚህ ...
Read More »የኤፍ 97.1 ዋና ዳይሬክተር ስርዓቱን ትተው እንግሊዝ ገቡ
የካቲት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደገለጹት አቶ አንድነት ዳኘው ስራቸውን በመልቀቅ ጥገኝነት የጠየቁት ከ2 ሳምንት በፊት ነው። በእርሳቸው ቦታ ምክትላቸው የነበሩት አቶ ኤርምያስ ጌታቸው ተተክተዋል። ኤፍ 97.1 በብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ ስር የሚተዳደር የመጀመሪያው የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው።
Read More »ኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር አካባቢ ተቆጣጣሪ ሃይል በሚሰማራበት ሁኔታ መከሩ
ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2008) ከኢትዮጵያ ጋር ድንበርን ለማካለል በዝግጅት ላይ የምትገኘው ሱዳን በሁለቱ ሃገራት የድንበር አካባቢ የጋራ ድንበር ተቆጣጣሪ ሃይል እንዲመሰረት አዲስ ሃሳብ አቀረበች። የኢትዮጵያና የሱዳን መከላከያ ሚኒስትሮች በዚህና ተጓዳኝ ጉዳዮች ዙሪያ በሱዳን መዲና ካርቱም መምከራቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ ዘግቧል። የሱዳኑ መከላከላይ ሚኒስትር አዋድ ኢብን ኡፍ በሁለቱ ሃገራት መካከል በጋራ ሊቋቋም የታሰበው ሃይል የሁለቱን ሃገራት ጥቅም እንደሚያስጠብቅና በድንበሩ ዙሪያ ...
Read More »የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች አሜሪካ ኢምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ተሰማ
ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2008) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች በኦሮሚያ ክልል የሚፈፅሙትን የሃይል እርምጃ በመቃወም ማክሰኞ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። ያልተጠበቀ ነው የተባለውን ሰላማዊ ሰልፍ አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ያካሄዱት ተማሪዎች የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞን በሚያሰሙ ነዋሪዎች ላይ እየወሰዱ ያለውን የሃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ መጠየቃቸውም ታውቋል። ተማሪዎቹ ጥያቄያቸው ሰላማዊ እንደሆነ ለማሳየት ነጭ ጨርቅን እያውለበለቡ ጥያቄያቸውን ቢያቀርቡም ...
Read More »በነቀምቴ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ተደበደቡ
ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2008) በነቀምቴ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ማቅረብ የጀመሩንት ጥያቄ ተከትሎ በዩኒቨርስቲው ትምህርት መቋረጡንና በርካታ ተማሪዎችም በጸጥታ ሃይሎች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል። የዩንቨርስቲ ተማሪዎች በኦሮሚያ ክልል እየተፈፀመ ያለው ግድያ እንዲያበቃ ጥያቄን ማቅረብ በጀመሩ ጊዜ በአካባቢው ሰፍረው የሚገኙ የፀጥታ ሃይሎች እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን ተማሪዎች ገልጸዋል። አራተኛ ወርን ዘልቆ የሚገኘው ይኸው ተቃውሞ ሰሞኑን በምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ አካባቢ ...
Read More »በአርባ ምንጭ ከተማ የተቅማትና ትውከት ወረርሽን ተከሰተ
ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2008) በደቡብ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ የአጣዳፊ ተቅማትጥና ትውከት በሽታ በወረርሽኝ መልክ ተከስቶ ከ40 በላይ ሰዎች ለህክምና ሆስፒታል መግባታቸው ተገለጠ። ታማሚዎችን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለሞት ይዳረጋል የተባለው ይኸው ወረርሽኝ ከአርባ ምንጭ ከተማ በተጨማሪ በዙሪያዋ በሚገኙ የገጠር መንደሮች ጉዳት በማድረግ ላይ መሆኑንም የክልሉ ጤና ቢሮ ማክሰኞ አስታውቀዋል። እስካሁን ድረስ በሰው ህይወት የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የገለጸው የጤና ቢሮም ...
Read More »ለተቃውሞ የወጡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተደበደቡ
የካቲት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው ግድያ ይቁም የሚል መፈክር በመያዝና ነጭ ጨርቅ በማውለብለብ ወደ አሜሪካ ኢምባሲ ያመሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ፣ በአካባቢው ሲደርሱ በፖሊሶች ተደብድበዋል። ተማሪዎቹ “እኛ አሸባሪዎች አይደለንም፣ ግድያው ይቁም!” የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል። ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን ተከትሎ ተማሪዎች ቢበታተኑም፣ ፖሊሶቹ ግን ተቃውሞውን አስተባብረዋል ያሉዋቸውን ይዘው በማሰር ላይ ...
Read More »በአለም በር የሚገኙ አሽከርካሪዎች አድማውን ለሶስተኛ ቀን ቀጥለዋል
የካቲት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት አሽከርካሪዎችን በተመለከተ ያወጣው ህግ የሚያሰራ አይደለም በማለት ፣ በህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ሾፌሮች፣ የጀመሩት አድማ ለሶስተኛ ቀን ቀጥሎአል። ሾፌሮቹ ዛሬ ወደ ደብረታቦር ከተማ በመሄድ ጥያቄያቸው መልስ እንዲያገኝ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ቢነጋገሩም ፣ ባለስልጣናቱ አድማ ላደረጋችሁበት 1 ሺ ብር ቅጣት ካልከፈላችሁ ስራ አትጀምሩም በማለታቸው፣ ተበሳጭተው መመለሳቸውንና በአድማው ለመቀጠል መወሰናቸውን ለኢሳት ...
Read More »በኮንሶ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው
የካቲት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአስተዳደር ጋር በተያያዘ የኮንሶ ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ ተከትሎ በአካባቢው የሚታየው ውጥረት የቀጠለ ሲሆን፣ በደቤና ቀበሌ አቶ ሷይታ ጋራ የተባሉ ሰው በአካባቢው በሰፈሩት ፖሊሶች ተገድለዋል። ትምህርት ቤቶች አሁንም እንደተዘጉ ሲሆን፣በርካታ ሰዎችም ታስረዋል።ባለፈው ቅዳሜ የአካባቢው ህዝብ ከአርባምንጭ ጂንካ የሚወስደውን መንገድ በመዝጋት ተቃውሞውን የገለጸ ሲሆን፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት መንገዱን በመክፈት በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችን ...
Read More »