Author Archives: Central

አቶ ካሳ ተክለብርሃን “መንግስት ችግር አለብኝ፣አርሙኝ ማለቱ ውድቀቱን አያሳይም” አሉ

መጋቢት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶአደሮች አካባቢ ልማት ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለብርሃን መንግስት ችግር አለብኝ፣አርሙኝ ማለቱ እንደውድቀት እንደማይታይ ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ከመንግስታዊው አዲስዘመን ጋዜጣ የመጋቢት 8/2008 ዓም እትም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ መንግስት ይሄ ችግር አለብኝ ብሎ አርሙኝ፣ አስተካክሉኝ፣ማለቱ ታላቅነት ነው፣ውድቀት አይደለም ብለዋል። አንዳንዶች መንግስት ጉድለት አለብኝ ስላለ መምራት አይችልም፣ወድቆአል በማለት የህብረተሰቡን ስሜቶች ወደሌላ ለመውሰድ የሚፈልጉ ...

Read More »

የአዲስአበባ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቆጠራ ውጤት የአዲስአበባን ህዝብ እያነጋገረ ነው

መጋቢት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አስተዳደሩ ባለፉት 11 አመታት ከ143ሺህ በላይ ኮንዶሚኒየም ቤቶችን በመገንባት በእጣ ማከፋፈሉን ሲገልጽ የቆየ ቢሆንም፣ ቤቶቹ በትክክል ስለመተላለፋቸው በቂ መረጃ አልነበረውም።ይህን ተከትሎ ቆጠራ እንዲካሄድ በተወሰነው መሰረት በ15 ቀናት ቆጠራ ብቻ ከ1 ሺ 200 በላይ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ሳይተላለፉ ለአመታት ተዘግተው የተገኙ ሲሆን ፣98 ቤቶች ደግሞ በማይታወቁ ሰዎች ተይዘው ሲጠቀሙባቸው ተገኝተዋል። ከ800ሺህ በላይ እጣ ...

Read More »

በዲላ ውሃ ቀጅዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

መጋቢት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዲላ በውሃ ችግር ከተመታች ወራት ቢቆጠሩም፣ ችግሩ ግን እስካሁን አልተቀረፈም። በአካባቢው ጋሪ ያላቸው ሰዎች ውሃ ከወንዝ በመቅዳት ለከተማው ህዝብ እየሸጡ፣ የውሃ ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት ቢያደርጉም፣ የከተማው መስተዳደር ግን፣ የውሃ ችግሩን ሳይቀርፍ፣ ውሃ ሻጮች ውሃ ከወንዝ አትቀዱም በማለት ክልከላ አስቀምጧል። በዚህ የተበሳጩት ከ70 በላይ የሚሆኑ ውሃ ነጋዴዎች፣ ጋሪዎቻቸውን አሰልፈው ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስትና ዓለም-አቀፍ የእርዳታ ተቋማት ተጨማሪ የእርዳታ ጥሪ ሊያደርጉ ነው

ኢሳት (መጋቢት 7 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በስድስት ክልሎች ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ እየተባባሰ መምጣትን ተከትሎ መንግስትና ዓለም-አቀፍ የእርዳታ ተቋማት ተጨማሪ የእርዳታ ጥሪ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ሮይተርስ ዘገበ። የዘር እህል እርዳታን የሚፈልጉ አርሶ አደሮች ቁጥርም ከ2.2 ሚሊዮን ወደ 3.3. ሚሊዮን ማሻቀቡንና የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የዜና አውታሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። ከሁለት ወር በፊት በተደረገ የእርዳታ ጥሪ 1.4. ...

Read More »

የዓባይ ግድብ ተፅዕኖ እንዲያጠኑ የተመረጡ ኩባንያዎች ጥናቱን ማራዘማቸው ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 7 ፥ 2008) በመገንባት ላይ ያለው የአባይ ግድብ በታችኛው ተፋሰስ ሃገራት ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ተፅዕኖ እንዲያጠኑ የተመረጡ ሁለት የፈረንሳይ ኩባንያዎች በተያዘው ወር ይጀምሩታል ተብሎ የነበረው ጥናት መራዘሙ ተገለጠ። ኢትዮጵያና ግብዕ ከኩባንያዎች ጋር ሊያደርጉት የነበረው የኮንትራት ስምምነት በተለያዩ ነጥቦች ላይ አለመግባባት በመፈጠሩ ምክንያት ጥናቱ እንዲዘገይ መደረጉን የግብፅ ባለስልጣናት ረቡዕ አስታውቀዋል። ከሁለቱ ሃገራት የተውጣጡ የባለሙያዎች ቡድን ይፋ ያልተደረገውን አለመግባባት ለመፍታት ...

Read More »

ዩኒሴፍ ዋና ዳይሬክተር የተከሰተው የድርቅ አደጋ ለመገምገም ኢትዮጵያን እየጎበኙ ነው

ኢሳት (መጋቢት 7 ፥ 2008) የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ዋና ዳይሬክተር አንቶኒ ሌከን በኢትዮጵያ ያለውን የድርቅ አደጋ ለመታዘብ በሃገሪቱ ጉብኝትን እያደረጉ እንደሆነ ድርጅቱ ረቡዕ ገልጿል። በድርቁ ክፉኛ ጉዳይ በደረሰባቸው ህጻናት ስጋቱን በተደጋጋሚ በመግለጽ ላይ ያለው የህጻናት መርጃ ድርጅቱ ክፉኛ የምግብ እጥረት ጉዳት የደረሰባቸውን ህጻናት ለመታደግ 100 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ይፋ አድርጓል። በድርቁ ምክንያት ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ከተጋለጡት ከ10 ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ኣንዲያከብር ኦክላንድ ኢንስቲቲዩት ጠየቀ

ኢሳት (መጋቢት 7 ፥ 2008) የአለም አቀፍ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊ መብት መከበር በሚታገሉ ተቋማትና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን የእስራትና የአፈና ድርጊት እንዲያቆም ግፊትን እንዲያደርጉ መቀመጫውን በዚህ በአሜሪካ ያደረገው የኦክላንድ ኢንስቲቲዩት ጥሪን አቀረበ። ከአንድ አመት በፊት ለእስር የተዳረጉ ሶስት የመሬትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ግለሰቦችም ለቀረበባቸው የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ምንም አይነት ማስረጃ ሳይቅረብላቸው እየተንገላቱ መሆኑን ተቋሙ አውስቷል። ኦሞት ኦግዋ፣ አሽኒ ኦስቲን እና ...

Read More »

መንግስት የመብት ጥያቄዎችን ካልፈታ በኦሮምያ የተነሳው ጥያቄ ይቀጥላል ሲሉ የተለያዩ የክልሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

መጋቢት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በክልሉ በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ ተቃውሞ በማስመልከት ኢሳት ያነጋገራቸው የቦረና ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ተወካይ አቶ ጌታቸው በቀለ እንዲሁም በጉጂ ዞን እስካሁን የቀጠለውን ተቃውሞ ከሚያስተባብሩት መካከል አንድ ግለሰብ እንዳሉት በክልሉ የሚታየው ህዝባዊ እምቢተኝነት፣ መሰረታዊ የሆነው የፍትህና የነጻነት ጥያቄ እስከሚመለስ ይቀጥላል። በሁለቱም ዞኖች እስከዛሬ ድረስ ውጥረትና ተቃውሞ እንዳለ ገልጸው፣ በአካባቢያቸው የሰፈረው የአጋዚ ጦር ...

Read More »

“የብሔር ብሔረሰብ ታሪክና አገራዊ ታሪክን ለማጣጣም ችግር እየተፈጠረ ነው” ሲሉ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ ተናገሩ።

መጋቢት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፕሮፌሰር ባህሩ ይህን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ከምሁራን ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ይለማርያም ውይይቱን ሲከፍቱ ባሰሙት ንግግር፦”መንግሥት ኅብረተሰቡን ለማንቀሳቀስ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን፣ እንዲሁም ሌሎች ፕሮጀክቶችን አገራዊ መግባባት ለመፍጠር በሚያስችል አኳኋን ቀርፆ ተግባራዊ ለማድረግ እየጣረ ቢሆንም፣ ፖለቲከኛው ጥግ ጥጉን ይዞ ከመታኮስ ባለፈ የመቻቻልና የመወያያት ዴሞክራሲያዊ ባህልን ማዳበር ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎችን የማፈን እርምጃ አጠናክሮ እንደቀጠለ ሂውማን ራይትስ ዎች ገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 6 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ሃሳብን በነጻነት ለመግለጽ በሚፈልጉ የሃገሪቱ ዜጎች ላይ የሚወስደውን የአፈና እርምጃ አጠናክሮ መቀጠሉን ሂውማን ራይትስ ዎች ማክሰኞ ገለጠ። የመንግስት የልማት ፖሊሲዎችና እቅዶች ዙሪያ እንኳን ትችትን የሚያቀርቡ ሰዎች መሳሪያ ያነገቡ ሃይሎችን ትደግፋላችሁ የሚል ክስ እየቀረበባቸው ለእስር በመዳረግ ላይ እንደሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ አስታውቋል። ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ተቃውሞና ...

Read More »