ኢሳት (መጋቢት 13 ፥ 2008) በቅርቡ ወደ ዚምባብዌ በህገወጥ መንገድ ገብታችኋል ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ 13 ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት በምግብ እጦት በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። የኢትዮጵያውያኑን ጉዳት ለመመልከት ተሰይሞ የነበረ ችሎትም ስደተኞቹ ያቀረቡት የረሃብ ቅሬታ ተከትሎ ጉዳዩን ሳይመለከት ለሌላ ጊዜ መቅጠሩን ክሮኒክል የተሰኘ እለታዊ ጋዜጣ አስነብቧል። ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት ስደተኛ ኢትዮጵያውያንም የደረሰባቸውን የምግብ እጥረት ችግር በመግለጽ ...
Read More »Author Archives: Central
በድርቅ በተጎዱ ክልሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች 75% የሚሆኑት የውሃ አቅርቦት የሌላቸው መሆኑን ተመድ አስታወቀ
ኢሳት (መጋቢት 13 ፥ 2008) በድርቅ በተጎዱ ክልሎች ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል 75 በመቶ የሚሆኑት የውሃ አቅርቦት የሌላቸው መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማክሰኞ አስታውቋል። አስር በመቶ ጭማሪን ያሳየው ይኸው የውሃ እጥረት ተማሪዎች በአግባቡ ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ አድርጎ እንደሚገኝም ድርጅቱ በድርቁ ዙሪያ በየሳምንቱ በሚያወጣው ሪፖርት ገልጿል። በስድስት ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ወደ አንድ ሚሊዮን አካባቢ ሰዎችም ካለባቸው የውሃ እጥረት የተነሳ ውሃን በተሽከርካሪ ለማቅረብ ...
Read More »በአማራ ክልል ዳንሻ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በአጎራባች አካባቢዎች ተጠናክሮ መቀጠሉ ተነገረ
ኢሳት (መጋቢት 13 ፥ 2008) በሳምንቱ መገባደጃ እሁድ በአማራ ክልል በዳንሻ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ማክሰኞ ለሶስተኛ ቀን መቀጠሉንና በአጎራባች ያሉ ነዋሪዎች ከወልቃይት ተወላጆች ጎን በመሰልፍ ላይ መሆናቸው እማኞች ለኢሳት ገለጡ። በሶሮቃ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶችና ነዋሪዎች “ጥያቄው የእኛም ነው” በማለት ከወልቃይት ተወላጆች ጎን በመቆም ተቃውሞን እንደተቀላቀሉት ማክሰኞ ከስፍራው የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በዳንሻና በሶሮቃ መንገዶች ተዘግተው መዋላቸውን የተናገሩት እማኞች በፀጥታ ሃይሎችና በወልቃይት ተወላጆች ...
Read More »በአርሲ አዳባ የመንግስት ካድሬዎች የሃይማኖት ግጭት ለማስነሳት ቅስቀሳ ሲያደርጉ እንደነበር ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 13 ፥ 2008) ከኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ጋር ተያይዞ በተነሳው ግጭት በአርሲ አዳባ ከተማ የመንግስት ካድሬዎች በሙስሊሞችና ክርስቲያኖች መካከል ግጭት ለማስነሳት ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርጉ እንደነበር በአካባቢ የሚኖሩ ኢሳት ያነጋገራቸው ሰዎች ገለጹ። የመንግስት ካድሬዎች በመስጊድ ውስጥ ከአንድ ወር በፊት ለፈነዳው ቦምብ ተጠያቂዎቹ “የአማራ ብሄር ተወላጆች” እንደሆኑ መስጊድ ውስጥ በመገኘት ሲቀሰቅሱ እንደነበር እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። እነዚህ የመንግስት ካድሬዎች በኦሮሚያ በተቀሰቀሰው ግጭት ...
Read More »የኦህዴድ አባላት አቶ አባይ ጸሃዬ በህግ እንዲጠየቁላቸው ጠየቁ
መጋቢት ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜ በተጠናቀቀው የኦህዴድ የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ግምገማ ፣ የህወሃቱ መስራችና ነባር ተጋይ አቶ አባይ ጸሃዬ፣ ኦህዴድን በተመለከተ የተናገሩት ንግግር በክልሉ ለደረሰው የሰው ህይወት መጥፋትና ለንብረት ውድመት ዋና ተጠያቂ ነው በማለት ህወሃት አቶ አባይን ገምግማ ለፍርድ እንድታቀርብ ጠይቀዋል። ቤቱ በውይይቱ ” ችግራችን የመስመር ወይም የአላማ ችግር ሳይሆን የአመራር ችግር ነው” ...
Read More »የፌዴራል ፖሊስ ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ እንዲሆን የሚደነግግ አዋጅ በዛሬው ዕለት ለፓርላማ ቀረበ፡፡
መጋቢት ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአሁኑ ወቅት ፌዴራል ፖሊስ ተጠሪነቱ ለፌዴራልና አርብቶአደር ልማት ሚ/ር ሲሆን አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ፖሊስን ለአንድ አስፈጻሚ መ/ቤት ብቻ ተጠሪ አድርጎ መቀጠል የአሰራር ክፍተት ይፈጥራል ተብሎ በመታሰቡ ወደፊት በጥናት ላይ ተመስርቶ እስኪወሰን የፌዴራል ፖሊስ ተጠሪነት ለጠ/ሚኒስትሩ እንዲሆን በረቂቅ አዋጁ ተደንግጎአል፡፡ በመሆኑም አሁን በስራ ላይ ያለው የፌዴራል ፖሊስ ኮምሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ...
Read More »በአዲስ አበባ ከተማ የውሃ ችግር ተባብሶ ቀጥሏል
መጋቢት ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎች እንደሚሉት በተለይ በአራት ኪሎ ቤተ መንግስት አካባቢ፣ መገናኛ፣ ልደታ፣ ኮተቤ፣ ጉርድ ሾላ፣ አብነት አካባቢ ችግሩ በከፋ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል። የአካባቢው ነዋሪዎች ለአራት ቀናት ያክል ውሃ ማግኘት እንዳልቻሉና በዚህም ሳቢያ እናቶች ልጆቻቸውን ምግብ አብስሎ ለመመገብና ንጽሕናቸውን ለመጠበቅ እንዳልቻሉ ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል። አቅሙ ያላቸው የታሸገ ውሃ በመግዛት ሲጠቀሙ ድሃው አብዛሃኛው የከተማዋ ነዋሪ ...
Read More »የቀበሌ ቤቶችን ሲጠቀሙ የነበሩና ሃብት ያፈሩ ከፍተኛ የመንግስት ተሿሚዎችና ነዋሪዎች የተለያዩ ምክንያት በመፍጠር ቤቶችን ለተቸገሩት ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተነገረ፡፡
መጋቢት ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በአማራ ጠቅላይ ፍርድቤት ለተመረጡ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ በፍርድ ቤት ዙሪያ ለሚሰሩ ባለሙያዎችና ለመንግስት አመራሮች ባቀረበው የስድስት ወር የስራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ የቀበሌ ቤትን በተመለከተ የቀረቡ በርካታ አቤቱታዎች ቢኖሩም ፍርድቤቶች አፋጣኝ ምላሽ ያልሰጡ መሆኑን ተሰብሳቢዎችና ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡ በጠቅላይ ፍርድቤት በኩል ሪፖርት ያቀረቡት ባለሙያ ተሰብሳቢዎች ያቀረቡት አስተያየት ትክክል መሆኑን አምነዋል፡፡የራሳቸውን መኖሪያቤት ከመንግስት ...
Read More »ለባለሃብቶች ሲሰጥ የነበረው የእርሻ መሬት ፈቃድ የተፈለገውን ውጤት ባለማምጣቱ እንዲቆም ተደረገ
ኢሳት (መጋቢት 12 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ላለፉት አስር አመታት ያህል ከሃገር ውስጥና ከውጭ ባለሃብቶች ለሰፋፊ የእርሻ መሬቶች ሲሰጥ የቆየውን ፈቃድ እንዲቀር አደረገ። የግብርና ኢንቨስትመንት እና የመሬት አስተዳደር ኤጀንሲ ከዘርፉ ይመጣል ተብሎ የታሰበው የቴክኖሎጂ ሽግግር የተፈለገውን ውጤት ሊያመጣ ባለመቻሉ ምክንያት ፕሮግራሙ እንዲቆም መደረጉን ገልጿል። ኤጀንሲው ባለፉት ጥቂት አመታት ከአራት ክልሎች 470 ሺህ ሄክታር መሬትን ተረክቦ ለ131 ባለሃብቶች ቢሰጥም ውጤታማ የሆኑት ...
Read More »በአዲስ አበባ የከፋ የውሃ እጥረት ሊከሰት ይችላል ተባለ
ኢሳት (መጋቢት 12 ፥ 2008) ለአዲስ አበባ ከተማ የመጠጥ ውሃን ለሚያቀርበው ለገዳዲ የውሃ ግድብ ተጨማሪ ውሃን በማቅረብ ሲያገልግል የነበረው የድሬ ግድብ በቀጣዩ ወር ሙሉ ለሙሉ አገልግሎትን እንደሚያቋርት የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ። የግድቡ አገልግሎት ማቋረጥም በከተማ ነዋሪዎች ዘንድ የከፋ የውሃ እጥረት እንዲከሰት እንደሚያደርግ ባለስልጣኑ አሳስቧል። ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የ24 ሰዓት የውሃ አገልግሎት የሚያገኙ ዋና ዋና አካባቢዎች ከተያዘው ...
Read More »