Author Archives: Central

6 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ህጻናት ለከፋ የምግብ እጥረት ተዳርገዋል

ሚያዚያ ፫( ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ረሃብ አለማቀፍ ትኩረት እያገኘ ነው፡፡ ቢቢሲና አልጀዚራን የመሳሰሉ ታላላቅ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የተመለከተ ዘገባ አቅርበዋል፡፡ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች፣ መንግስትን ላለማስከፋት ፈራ ተባ እያሉም ቢሆን ሁኔታው አስፈሪ መሆኑን ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ አሁን ችግሩ አሳሳቢ መሆኑን ሲመለከቱ፣ ስጋታቸውን በአደባባይ መግለጽ ጀምረዋል፡፡ 6 ሚሊዮን ህጻናት ለከፋ ረሃብ መዳረጋቸውን የአለማቀፉ ...

Read More »

በውጭ ብድር ላይ የተመሰረተው የልማት ፕሮጄክት ኢኮኖሚውን ሊያንኮታኩት ይችላል ተባለ

  ኢሳት (መጋቢት 30 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት በውጭ ብድር ላይ ተመስርቶ እያካሄደ ያለው የልማት ፕሮጄክቶች የሃገሪቱ ኢኮኖሚን አደጋ ውስጥ መክተቱንና ሊንኮታኮት እንደሚችል የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች አሳሰቡ። መንግስት ከቻይና ብቻ ለመሰረተ-ልማቶች ማካሄጃ 17 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ መበደሩን ያስታወቁትና በለንደን ዩንቨርስቲ መምህር የሆኑት ዶ/ር አለማየሁ ገዳ ሃገሪቱ በአሳሳቢ የኢኮኖሚ አቅጣጫ ውስጥ መሆኗን እንደገለፀ ዘ-ኢስት አፍሪካን መጽሄት ዘግቧል። ሃገሪቱ ለውጭ ንግድ ከምታቀርበው ...

Read More »

በኢትዮጵያ የፌዴራሊዝም ስርዓት አተገባበር ጥያቄ እንዳስነሳ የብሪታኒያው ዘ-ጋሪድያን ዘገበ

ኢሳት (መጋቢት 30 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልዩነቶችንና አመለካከቶችን በተገቢው ሁኔታ ሊስተናገዱ ባለመቻላቸው በሃገሪቱ ተቃውሞ ኣየተባበሱ መምጣቱን የብሪታኒያው ዘ-ጋሪድያን ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎች ዋቢ በማድረግ አርብ ዘገበ። በተለያዩ ክልሎች መጠኑን እያሰፋ የመጣው ይኸው ተቃዎሞ በኢትዮጵያ የፌዴራሊዝም ስርዓት አተገባበርና በዴሞክራሲያዊ የመብት ጥያቄዎች ላይ ጥያቄ አስነስቶ እንደሚገኝም ጋዜጣው አስነብቧል። በኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰው ተቃውሞ በትንሹ 266 ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች መገደላቸውን ያወሳው ጋዜጣው አስተዳደራዊ ጥያቄን ...

Read More »

ጋዜጠኛ አበበ ገላው የኢሳት አለም-አቀፍ ዳይሬክተር ሆኖ ተሾመ

ኢሳት (መጋቢት 30 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ቦርድ ለኢሳት አለም-አቀፍ አዲስ ዳይሬክተር መሾሙን ይፋ አደረገ። የቀድሞውን የኢሳት አለም አቀፍ ዳይሬክተር አቶ ነዓምን ዘለቀ በክብርና በምስጋና የሸኘው የኢሳት ቦርድ ጋዜጠኛ አበበ ገላው የኢሳት አለም አቀፍ ዳይሬክተር እንደሆነ ከኤፕሪል 1 ፥ 2016 ጀምሮ መሾሙን አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት በካሊፎርኒያ ግዛት ሲልከን ቫሊ የሚገኘው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ከኢሳት አስተዳደር ቦርድ በተሰጠው ሹመት ...

Read More »

በአቶ አለማየሁ መኮንን ላይ እንዲመሰክሩ የሃሰት ምስክሮች እየተመለመሉ ነው ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 30 ፥ 2008) በጂንካ ከተማ እቶ አለማየሁ መኮንንን በሽብርተኛ ፈርጆ የሚመራው ቡድን እስካሁን የሄደበት መንገድ ህገ-ወጥና በማሰረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ በፈጠራ ውንጀላ የሃሰት ምስክሮችን ለማዘጋጀት እየተሯሯጠ መሆኑን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለኢሳት አድርሰዋል። ለዚሁ ውንጀላ ይረዳቸው ዘንድ እቶ አለማየሁ ከመያዛቸው በፊት ሃሙስ ዕለት ምሽት በከተማው ውስጥ ቦንብ መፈንዳቱን እንደመነሻ በስፋት እያስወራ መሆኑን ምንጮቹ አስታውሰው፣ በገንዘብና ጥቅማ-ጥቅሞች የሃሰት ምስክሮች እየተመለመሉ ያሉት ...

Read More »

ከማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አሁንም ድረስ ቀጥሏል

ኢሳት (መጋቢት 30 ፥ 2008) ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ ተቀስቅሶ የነበረው ተቃውሞ በመንግስት ባለስልጣናት ዘንድ እልባትን እንዳገኘ ቢገልጽም ተቃውሞ አሁንም ድረስ እልባት አለማግኘቱን ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል። ከተቃውሞው ጋር በተገናኘ ለእስር የተዳረጉ ሰዎች እንዲፈቱና በየከተሞቹ ያሉ የጸጥታ ሃይሎች ከአካባቢው እንዲወጡ የሚጠይቁ ተቃውሞዎች በምስራቅ ሃረርጌና በተለያዩ የክልል ከተሞች እየተካሄዱ መሆኑም ታውቋል። አራተኛ ወሩን ዘልቆ የከሚገኘው ከዚሁ ተቃውሞ ...

Read More »

በድርቅ የተመቱት የሰቆጣ አካባቢ ነዋሪዎች ቀያቸውን ጥለው እየሸሹ ነው

ኢሳት (መጋቢት 30 ፥ 2008) በሰቆጣ የተከሰተው ድርቅ እየተባባሰ በመምጣቱ ነዋሪዎች ቀዬአቸውን ጥለው በመሰደድ ላይ መሆናቸው ታወቀ። ከፊሉ ነዋሪ ወደ ባህር ዳርና መቀሌ ሲሰደድ፣ 400 የሚሆኑ ደግሞ ደብረ-ብርሃን መድረሳቸው ታውቋል። ረሃቡን ሸሽተው ምግብ ፍለጋ ደብረ-ብርሃን ከደረሱት የሰቆጣ ነዋሪዎች ውስጥ አንዱ ለኢሳት እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት በሰቆጣ የቀሩት የመንግስት ሰራተኞችና ዕድሚያቸው የገፉ አዛውንቶች ብቻ ናቸው። ነዋሪው በርሃብ ከደረሰበት ችግር ባሻገር የሚጠጣ ውሃ ...

Read More »

በሶማሊ ክልል 24 ወረዳዎች ለረሃብ ሊጋለጡ እንደተቃረቡ ተመድ ገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 30 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ መባባስን ተከትሎ በሶማሊ ክልል ብቻ ለረሃብ ሊጋለጡ የተቃረቡ ወረዳዎች ቁጥር 24 መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አርብ አስታወቀ። በዚሁ የድርቅ አደጋ ከቀያቸው የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥርም መጨመርን አሳይቶ እስከ ባለፈው ወር ድረስ በክልሉ ከ 147 ሺ በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው መሰደዳቸውን ድርጅቱ ይፋ አድርጓል። የሶማሊ ክልል በድርቅ ከተጠቁት ስድስት ክልሎች አንዱ ሲሆን፣ ...

Read More »

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችና ደህንነቶች በዋልድባ ቁጥጥር ሲያደርጉ መሰንበታቸው ታወቀ

መጋቢት ፴( ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የገዳሙ አባቶች እንደገለጹት መጋቢት 27 የተከበረውን የመድሃኒአለም በአል ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችና ደህንነቶች በገዳሙ በመግባት ቁጥጥርና ክትትል ሲያደርጉ ሰንብተዋል፡፡ ሁሉም ደህንነቶች ትግርኛ ብቻ የሚናገሩ የህወሃት ደህንነቶች መሆናቸውን የሚናገሩት አባቶች፣ ከወልቃይትና ከጎንደር ወደ ገዳሙ የሄዱ ምእመናን ከቤተሚናስ መነኮሳት ጋር ምን አይነት ግንኙነት አላችሁ በማለት ሲያዋክቡዋቸው እና ሲከታሉዋቸው ሰንብተዋል፡፡ የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ ያሰጋቸው ...

Read More »

በአፋር መጪው ጊዜ እጅግ አስፈሪ ነው ተባለ

መጋቢት ፴( ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ20 ሚሊዮን ያላነሱ ዜጎችን ለረሃብ አደጋ ያጋለጠው ድርቅ፣ በአፋር ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍቶአል፡፡ እናቶች በየሳምንቱ በሞትና በህይወት መካከል ያሉ ህጻናትን ይዘው ረጅም ርቅት ተጉዘው ህክምና ለማግኘት ይጥራሉ፡፡ ረሃቡ የከፋ መሆኑንና አለማቀፉ ማህበረሰብ ባይደርስ ኖሮ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል የአይ ቲ ቪ ኒውስ ጋዜጠኛ ቦታው ድረስ በመሄድ ዘግቦአል፡፡ በአንድ የህክምና ማእከል ውስጥ የሚሰራ ...

Read More »