Author Archives: Central

በሜዲትራኒያን ባህር ከሰጠሙት ስደተኞች አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ታወቀ

ኢሳት (ሚያዚያ 10 ፥ 2008) እሁድ ሚያዚያ 9 ፥ 2008 ዓም ከግብፅ ተነስተው ወደ ጣልያን ሲጓዝ ከነበሩትና በሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ ከሰጠሙት 400 ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተገለጸ። ህይወታቸውን ያጡት ወጣቶች ከሃገራቸው የተሰደዱት ምክንያትም ከዚህ አመት ከህዳር ወር ጀምሮ እየተካሄደ ባለው የኦሮሚያ ተቃውሞ የተነሳ መንግስት የሚወስደውን የሃይል እርምጃ ሸሽተው መሆኑን የሟች ቤተሰቦች ለኢሳት ገለጹ። እሁድ እለት የሶማልያ መገናኛ ብዙሃን እና ...

Read More »

ሪክ ማቻር ወደደቡብ ሱዳን ጁባ ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ ተራዘመ

ኢሳት (ሚያዚያ 10 ፥ 2008) መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ አድርገው የነበሩት የደቡብ ሱዳን አማጺ ቡድን መሪ ሪክ ማቻር በጋምቤላ ክልል በኩል አድርገው ወደ ደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ ልያደርጉት የነበረው ጉዞ ተራዘመ። የልተጠበቀ ነው የተባለው የአማጺ ቡድኑ መሪ መዘግየት በጋምቤላ ሊያጓጉዝ የነበረው አውሮፕላን የጉዞ ማስተካከያ ማድረጉን ጁባ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ማቻርን በመጠባበቅ ላይ ለነበሩት ጋዜጠኞች አስታውቀዋል። ላለፉት አንድ አመት ያህል መቀመጫቸውን በአዲስ ...

Read More »

የጋምቤላው ጭፍጨፋን አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ዘገቡ

ኢሳት (ሚያዚያ 10 ፥ 2008) አርብ እና ቅዳሚየ የተፈጸመውን የጋምቤላውን ጭፍጨፋ አለም አቀፍ ብዙሃን እየዘገቡ ነው። ኒው ዮርክ ታይምስ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው፣ ባለፈው አርብና ቅዳሜ ከ80 በላይ ቁስለኞች በጋምቤላ ሆስፒታል መድረሳቸውንና፣ አብዛኞቹ ጉዳተኞች በሰውነታቸው ውስጥ ጥይት እንዳለባቸው ዘግቧል። ሆስፒታሉም ከአቅሙ በላይ በቁስለኞች ስለተጥለቀለቀ፣ አብዛኞቹ ተጎጂዎች በሆስፒታሉ በረንዳ ላይ ተኝተው እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል ሲል ጋዜጣው ለንባብ አብቅቷል። ክላሺንኮብ መሳሪያ ...

Read More »

በጋምቤላ ክልል በንጹሃን ላይ ጥቃት የፈጸሙ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ የአፍሪካ ህብረት ጥሪ አቀረበ

ኢሳት (ሚያዚያ 10 ፥ 2008 መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ህብረት በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃትን የፈጸሙ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ ሰኞ ጥሪን አቅርቧል። የግድያ ድርጊቱን ያወገዘው ህብረቱ የኢትዮጵያና የጎረቤት ደቡብ ሱዳን መንግስታት ያላቸውን ዘርፈ-ብዙ ስምምነት በመጠቀም ጥቃት የፈጸሙ አካላትን ለፍርድ እንዲቀርቡ አሳስቧል። በዚሁ ጥቃት ታፍነው የተወሰዱ ኢትዮጵያውያንም በአስቸኳይ እንዲለቀቁ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ባወጣው መግለጫው የጠየቀ ሲሆን፣ መቀመጫቸውን በዚህ በአሜሪካና የተለያዩ ሃገራት ...

Read More »

በጋምቤላ በደረሰው ጭፍጨፋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን መከላከያም እየየተቸ ነው

ሚያዚያ ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው አርብ ከደቡብ ሱዳን የተነሱ ታጣቂዎች ከ35 እስከ 40 ኪሜ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቀው በመግባት በላሬ፣ ጃካዋ ወረዳዎች አካባቢ በሚኖሩ የኑዌር ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ላይ አሰቃቂ የሚባል ግድያ በመፈጸም እስካሁን ባለው ቆጠራ 208 ሰዎች የተገደሉ፣ሲሆን ከእነዚህ መካከል 50 የሚሆኑት ህጻናት ናቸው፡፡ የኢሳት የጋምቤላ ታማኝ ምንጮች እንደገለጹት አስከሬን የመሰብሰቡ ስራ በተለያዩ ወረዳዎች እየተካደ ሲሆን፣ ...

Read More »

የኦህዴድ ካድሬዎች የህዝቡን አመጽ ተቆጣጥረነዋል በሚል ስሜት ጥይት በመተኮስ ደስታቸው ሲገልጹ ዋሉ

ሚያዚያ ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ በሃይል መቆጣጠራቸውን የሚናገሩት የኦህዴድ ኢህአዴግ ታማኝ ካድሬዎች፣ ከትናንት ወዲያ ሚያዚያ 8 ቀን 2008 ዓም በቦረና ገላና ወረዳ ቶሬ ወረዳ የ26ኛውን የኦህዴድ በአል እናከብራለን በሚል ሰበብ፣ ከጡዋቱ 3 ሰአት ተኩል እስከ ቀኑ 11 ሰአት ተኩል በአየር ላይ ጥይት እየተኮሱ ደስታቸውን ሲገልጹ፣ በተዘዋዋሪም ህዝቡን ሲያሸብሩ ውለዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት አመጸኞችን ...

Read More »

ከስድስት ሚሊዮን በላይ የኢትዮጵያ ሕጻናት የምግብ እጥረትና ንጹሕ የመጠጥ ውሃ ማግኘት እንደማይችሉና አፋጣኝ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ዩኒሴፍ አስታወቀ።

ሚያዚያ ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የተከሰተው አስከፊ ርሃብ የዜጎችን ሕይወት አስጊ ሁኔታ ውስጥ ያስገባ ሲሆን በተለይ ሕጻናት ቀዳሚ የችግሩ ገፈት ቀማሽ መሆናቸውን ድርጅቱ ተገልጿል። በሃምሳ ዓመታት ውስጥ ተከስቶ የማያውቅ አደገኛ ችጋር በኢትዮጵያ ያንዣበበ ሲሆን ጉዳተኞችን ለመታደግ ከስድስት መቶ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ አፋጣኝ እርዳታ ከለገሽ አገሮች ይጠበቃል። ዩኒሴፍ ሕጻናት በውሃ ጥምና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በፈጠሩባቸው የጤና ...

Read More »

አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በድርቅ ለተጎዱ ኢትዮጵያውያን ዕርዳታ ሰጠ

  ኢሳት (ሚያዚያ 7 ፥ 2008) አለም-አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) በድርቅ ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን የሚሆን እርዳታና ቁሳቁስ እያቅረበ መሆኑን አስታወቀ። የአለም-አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በቅርቡ 442 የመጠለያ ፕላስቲክ፣ የወባ መከላከያ አጎበር፣ ፍራሽ፣ ብርድ ልብስና፣ ለቤት አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ቁሳቁሶች በአፋር ክልል በዱብቲ፣ ሚሌና፣ አሳይታ ወረዳዎች ለሚኖሩ ወገኖች ማቅረቡን አስታውቋል። በሚሌ 87, በዱብቲ 305 እና በአሳይታ 50 በድርቅ ምክንያት ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር የህወሃት ታጣቂዎች ነዋሪዎችን እየገደሉና እያሳደዱ ነው ተባለ

ኢሳት (ሚያዚያ 7 ፥ 2008) በሰሜን ጎንደር አርማጭሆ ውስጥ የህወሃት ታጣቂዎች በአካባቢው የሚኖሩ ገበሬዎችን እየገደሉ፣ እያሳደዱና፣ ዝርፊያ እየፈጸሙባቸው እንደሆነ ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አመለከቱ። ከሶስት ቀን በፊት ማለትም ሚያዚያ 3 ፥ 2008 ላይ አርማጭሆ ኩርቢት በተባለ ቦታ ተሰማርተው የነበሩ የህወሃት ታጣቂዎች አንድ ገበሬ ገድለው ንብረታቸውን እንደዘረፏቸው የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። በአካባቢው ተሰማርተው የሚገኙ የህወሃት ታጣቂዎች ተቃዋሚዎችን በተለይም አርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት ናቸው ...

Read More »

የደህንነት ሃላፊ የነበሩት ወልደስላሴ ወልደሚካዔል በሰባት ክሶች ጥፋተኛ ተባሉ

ኢሳት (ሚያዚያ 7 ፥ 2008) ከአንድ አመት በፊት ስልጣናቸውን ተጠቅመው ሙስና ፈጽመዋል ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የሃገር ውስጥ የደህንነት ሃላፊ በሰባት ክሶች ጥፋተኛ ተባሉ። የደህንነት ሃላፊ የነበሩት አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካዔል በስልጣን ላይ በነበሩ ጊዜ የተለያዩ ሙስናዎችን ፈጽመዋል ተብለው 12 ክሶች ተመስርቶባቸው እንደነበር ይታወሳል። የተከሳሹን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አርብ በሰጠው ውሳኔ አቶ ወልደስላሴን በሰባት ክሶች ጥፋተኛ ...

Read More »