ሚያዚያ ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚያዚያ 17 ንጋት ላይ በድሬዳዋ የጣለው ከባድ ዝናብ እስካሁን ድረስ በትንሹ 15 ሰዎች በጎርፍ መወሰዳቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ወደ መልካ ጀብዱ የሚወስደው ድልድይ የተሰበረ ሲሆን አንድ ገልባጭ የጪነት መኪናም በጎርፍ ተወስዷል። ወደ መልካ ጀብዱ በሚያሻግረው ወንዝ አንድ ድልድይ ተሰብሮ በህዝብ ማመላለሻ መኪና ውስጥ የነበሩ 18 ሰዎች መወሰዳቸውን እንዲሁም 1 ዩዲ ገልባጭ መኪና ረዳትና ...
Read More »Author Archives: Central
በደብረዘይት የመከላከያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) የተሰሩ የእርሻ መኪኖች ጥራት የሌላቸው መሆኑ ቅሬታ መፍጠሩ ተነገረ፡፡
ሚያዚያ ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል የገዢው መንግስት በእርሻ ስራ ያደራጃቸው ወጣቶች እንዲሰሩበት የተሰጣቸው የእርሻ መኪና ጥራት ዝቅተኛ በመሆኑ ስራቸውን አቁመው ማህበራቸወን ለመበተን መገደዳቸውን ተናገሩ፡፡ በክልሉ ልዩ ልዩ ዞኖች የሚገኙት ቅሬታ አቅራቢ ወጣቶች ከዩኒቨርስቲና ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ትምህርታችውን በመጀመሪያ ዲግሪና በዲፐሎማ ያጠናቀቁ ናቸው፡፡ ወጣቶቹ በእርሻ ስራው ለመሰማራት የሚያስችል ፕሮፖዛል አቅርበው ተቀባይነትን በማግኘቱ ገንዘብ በመቆጠብ ብድር ቢፈቀደላቸውም፤ባቀረቡት ...
Read More »አልሸባብ አንድ ወታደራዊ አዛዥን ጨምሮ ስድስት የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ
ሚያዚያ ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡባዊ ሶማሊያ ግዛት አወዲን ከተማ አቅራቢያ አውራጎዳና ላይ በተጠመደ ቦንብ አንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አዛዥን ጨምሮ ስድስት ወታደሮችን መግደሉን ድርጅቱ አስታውቋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በአካባቢው ወደ ነበረው የወታደራዊ ካንፕ ሲያመሩ በነበሩት ወታደሮች ላይ ጥቃቱ መፈጸሙን ተናግረዋል። የአፍሪካ ህብረትም ሆነ የኢህአዴግ መንግስት ስለደረሰው ጥቃት የሰጡት መግለጫ የለም።
Read More »ከጋምቤላ ጭፍጨፋ በስተጀርባ የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ሳይኖሩበት አይቀርም ተባለ
ኢሳት (ሚያዚያ 14 ፥ 2008) ባለፈው ሳምንት በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቁ የሙርሌ ጎሳ አባላት በንጹሃን ዜጎች ላይ የፈጸሙት አሰቃቂ ግድያ፣ በሳልባ ኪርና በሪክ ማቻር መካከል ያለው የስልጣን ፍትጊያ ማሳያ ሊሆን እንደሚችል አንድ አለም አቀፍ ጋዜጣ ዘገበ። በኑዌር ብሄረሰብ ላይ ጥቃት ያደረሱት የሙርሌ ብሄረሰብ አባላት በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቁ መሆናቸውና በዲንቃ ጎሳ አባላት መታጀባቸው የሪክ ማቻር ጎሳ አባላት በአንድ በኩል የሳልባ ኪር ጎሳ ...
Read More »ወደ ውጭ አገር በሚጓዙ የኢህአዴግ ሃላፊዎች ላይ ተቃውሞ ቀረበባቸው
ኢሳት (ሚያዚያ 11 ፥ 2008) በስራና በግል ጉዳይ ከኢትዮጵያ ወደተለያዩ የአለም ክፍሎች በሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትና በተለያዩ ዕርከን ላይ በሚገኙ ሃላፊዎች ላይ የሚካሄደው ተቃውሞ በዚህ በያዝነው ሳምንት ተጠናክሮ መቀጠሉን ለኢሳት የደረሰው ዜና ያስረዳል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በስዊዲን ስቶክሆልም ተከታታይ ተቃውሞ ሲገጥማቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አድማሱ ጸጋዬ ደግሞ ትናንት በዋሽንግተን ዲሲ አቅራቢያ ፔንታገን ሲቲ ውስጥ ተቃውሞ ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ጋር ግንኙነት አላችሁ የተባሉ 20 ሰዎች ክስ ተመሰረተባቸው
ኢሳት (ሚያዚያ 14 ፥ 2008) ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ ክልል ተቀስቅሶ ከነበረው ተቃውሞ ጋር ግንኙነት አላችሁ የተባሉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራርን ጨምሮ ከ20 በላይ ሰዎች አርብ የስብርተኛ ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው። ክሱን የመሰረተው የፌዴራሉ አቃቢ ህግ የፓርቲው አመራር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ እና 22 ግለሰቦች ሁከት እንዲባባስ በማድረግ ለንጹሃን ሰዎች ሞት ምክንያት ሆነዋል ሲል በክሱ አመልክቷል። የፓርቲው አመራር ...
Read More »በጋምቤላ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገደሉ
ሚያዚያ ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት ፣ ሚያዚያ13፣ 2008 ዓም አንድ ኢትዮጵያዊ ሹፌር፣ ከጋምቤላ ከተማ በ 13 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው በጃዊ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ሁለት የደቡብ ሱዳን የኑዌር ተወላጆችን ገጭቶ መግደሉን ተከትሎ፣ ስደተኞቹ በቀን ስራ ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ እስካሁን በትንሹ 13 ሰዎች ተገድለዋል፤ ነዋሪዎች በበኩላቸው የሟቾች ቁጥር ከ20 በላይ ...
Read More »የአዲስ አበባ ታክሲ እና የረጅም ርቀት ተሽከርካሪዎች ባለንብረቶች ስራ ለማቆም እንደሚገደዱ አስጠነቀቁ
ሚያዚያ ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ታክሲ እና የረጅም ርቀት ተሽከርካሪዎች ባለንብረቶች ከመለዋወጫ እቃዎች ዋጋ ንረት ጋር በተያያዘ የታሪፍ ማስተካከያ እንዲደረግላቸው ለአዲስ አበባ እና ለፌደራል የትራንስፖርት ባለስልጣናት በተደጋጋሚ ያቀረቡት አቤቱታ ተግባራዊ ምላሽ ባለማግኘቱ ስራ ለማቆም እንደሚገደዱ አስታወቁ። ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ ሁለት የአዲስአበባ ታክሲዎች ማህበራት አመራሮች ለአዲስ አበባው ዘጋቢያችን እንደተናገሩት፣ ባለፉት አምስት አመታት ብቻ ከ200 ፐርሰንት ...
Read More »ዛምቢያ 16 ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን ማሰሩዋን አስታወቀች
ሚያዚያ ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች በዝምባብዌ አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ ሲሞክሩ መያዛቸውን የአገሪቱ ፖሊስ አስታውቋል። ስደተኞቹን ያመላልሳሉ ተብለው የተጠረጠሩ 2 ሰዎች መያዛቸውንም ፖሊስ አስታውቋል። ኢትዮጵያውያኑ 30 ሺ ሽልንግ ለፖሊሶች ጉቦ ለመስጠት መሞከራቸውን ሉሳካ ታይምስ ዘግቧል። የአሁኑ የእስር ዜና የተሰማው በሕገወጥ መንገድ የታንዛኒያን ድንበር አቋርጣችሁ ገብታችኋል ተብለው በታንዛኒያ ፍርድ ቤት የተበየነባቸውን የእስር ጊዜያት ያጠናቀቁ ...
Read More »በሽብር ወንጀል የተከሰሱት እነ አቶ አለማየሁ መኮንን በዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ
ሚያዚያ ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው መጋቢት 17/08 ተይዘው እስከ ትናንት በሃዋሳ ታስረው የነበሩት የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበርና የዞን ጽ/ቤት ኃላፊ መምህር ዓለማዬሁ መኮንን፣ የኦህዲኅ አባል የሆኑት አቶ አብረሃም ብዙነህና የቀድሞው አንድነት የዞኑ አስተባባሪ የነበሩት አቶ ስለሺ ጌታቸው ሚያዚያ 13-08-08 ዓም ፍርድ ቤት ቀርበው ምንም አይነት ማስረጃም ሆነ መረጃ ያልቀረበባቸው በመሆኑ ፣ ፍርድ ...
Read More »