ሚያዚያ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲን የሚደግፉና በድጎማ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ጋዜጦች በገበያ እጦትና በድጎማ መቀነስ እየተዘጉ ሲሆን፣ በዜድ ፕሬስና ማስታወቂያ ኤጀንሲ ኃ/የተ/የግ/ማ በመባል በሚታወቀው የአቶ ሳምሶን ማሞ ድርጅት አማካይነት በየሳምንቱ ቅዳሜ የሚታተመው «ኢትዮቻናል» ጋዜጣ በኪሳራ ምክንያት መዘጋቱን አሳታሚው እንደገለጸላቸው አንዳንድ ጋዜጠኞች ለኢሳት ተናግረዋል። ኢትዮቻናል ጋዜጣ ፣ የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤት አቶ አማረ አረጋዊ ከሼክ አልአሙዲ ጋር ...
Read More »Author Archives: Central
የኢንዱስትሪ ምርቶች የወጪ ንግድ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር ከአምስት በመቶ በላይ ቀነሰ ተባለ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2008) በተያዘው አመት የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ምርቶች የወጪ ንግድ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር ከአምስት በመቶ በላይ መቀነሱንና ድርጊቱ በውጭ ምንዛሪ ገቢ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ ተገለጠ። መንግስት ለተለያዩ ድርጅቶች ልዩ የማበረታቻ ድጋፍን በመስጠት የውጭ ንግድ ገቢን ለማሳደግ ጥረት ሲያደርግ ቢቆይም የተገኘው ውጤት ግን እጅግ አነስተኛ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቀዋል። የሃገሪቱ የኢንዱስትሪ ምርቶች ወጪ ንግድ በማስመልከት ለተወካዮች ምክር ...
Read More »በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ጎርፍ የእርዳታ አቅርቦትን አስተጓጎለ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2008) በቅርቡ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የጣለው ከባድ ዝናብ በአገሪቷ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የእርዳታ አሰጣጥ ሂደት እያስተጓጎለና እያወሳሰበ እንደሚገኝ ተገለጸ። የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች በጎርፉና ጭቃ ምክንያት እርዳታ ወደሚፈልጉ አካባቢዎች መሄድ እንዳልቻሉ ለመረዳት ተችሏል። በመሆኑም ራቅ ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ እርዳታ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን፣ እርዳታውን ሳያገኙ ለሳምንታት ችግር ላይ ወድቀው እንደሚገኙ አሶሼይት ፕሬስ ረቡዕ አስነብቧል። በአንዳንድ አካባቢዎች ከከባድ ዝናብ ...
Read More »መንግስት በጅቡቲ ወደብ ወደ ሃገር ውስጥ ገብተው ከአንድ ወር በላይ የቆዩ ንብረቶችን ልወርስ ነው ማለቱ ነጋዴዎችን አስቆጣ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2008) መንግስት በጅቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በደረቅ ወደብ ከአንድ ወር በላይ የቆዩ ንብረቶችን ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ እንደሚወርስ ማሳወቁ ከአስመጪ ነጋዴዎች በኩል ተቃውሞን ቀሰቀሰ። በተያዘው አመት በሞጆ ደረቅ ወደብ ከተከማቹት ወደ 12ሺ ኮንቴይነሮች መካከል ወደ 1ሺ የሚገመቱ ከሁለት ወር በላይ ጊዜን ያስቆጠሩ እንደሆነ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አስታውቋል። እነዚሁ በደረቅ ወደብ የተከማቹ ንብረቶች እሰከ ግንቦት 1 ድረስ ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት ላይ በቀን ከ 1ሺ በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራ ይፈጸምብኛል አለ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2008) አዲስ የኢንተርኔት አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅን በህግ ለማጽደቅ በዝግጅት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ መንግስት በየዕለቱ ከ1ሺ በላይ የሳይበር ጥቃቶችን በሃገሪቱ ይፈጸማሉ ሲል ገለጠ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማትና ግለሰቦች በበኩላቸው ረቂቅ አዋጁ በአለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡ የሰብዓዊ መብቶች የሚጻረር እንደሆነ መግለጽ መጀመራቸውን ከሃገር ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል። በረቂቅ አዋጁ ላይ ለመምከር ረቡዕ በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደ የውይይት መድረክም ...
Read More »አዲስ አበባ በሚገኙ የማላዊ ኤምባሲ ባልደርቦች ከ4.2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዘረፉ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2008) በቅርቡ መቀመጫውን በአዲስ አበባ ከተማ ባደረገው የማላዊ ኢምባሲ ባልደርቦች የተፈጸሙው የገንዘብ ዝርፊያ ከአራት ሚሊዮን ዶላር በላይ መሆኑን የማላዊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሃሙስ አስታወቀ። ከዚሁ ዝርፊያ ጋር በተገናኘ የማላዊ መንግስት በኢትዮጵያ የማላዊ ምክትል አምባሳደር የነበሩትንና ጸሃፊውን ወደሃገሩ እንዲመለሱ ማድረጉ ይታወሳል። በኤምባሲው ልዑካኖች ተፈጽሟል የተባለን ዝርፊያ በመመርመር ላይ የሚገኘው የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድርጊቱ በታወቀ ጊዜ በመቶ ...
Read More »የኢትዮጵያ ገበሬዎች የሚዘሩት ዘር የላቸውም ተባለ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2008) 1.7 ሚሊዮን የሚሆኑ የኢትዮጵያ ገበሬዎች እርሻቸውን ቢያዘጋጁም፣ የሚዘሩት ዘር አጥተው ተቸግረው እንደሚገኙና የዘር እህል ባስቸኳይ እንደሚፈልጉ የተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ ድርጅት FAO አስታወቀ። እህል የሚዘራበት ወቅት ስድስት ሳምንት ብቻ ስለቀረው፣ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ለገበሬዎች ለዘር መግዣ የሚሆን የእርዳታ ገንዘብ ለመሰብሰብ እንደሚሞክር ይኸው ድርጅት ገልጿል። የተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ ድርጅት የአደጋ ጊዜ የቡድን መሪ የሆኑት ሮሳኔ ማርሼሲ ለጋዜጠኞች ...
Read More »አባት አርበኞች የፋሽስት ጣሊያን ዳግም ወረራ በተባበረ ክንዳቸው ያሸነፉበት 75ኛ ዓመት የድል በዓል በመላው ኢትዮጵያ ተከብሮ ውሏል።
ሚያዚያ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፋሽስት ጣልያን ጥሏት የነበረችው አርንጓዴ፣ቢጫና ቀይ ቀለማት ያላት ስንደቅ አላማችን፤ በአርበኞች ደም ታጥባ ዳግም በሰንደቁ ጫፍ ላይ ከፍ ብላ ከተውብለበለች ዛሬ 75ኛ ዓመት ሆኗታል። የድል በዓል 75ኛው አመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በልዩ ሁኔታ መከበር ሲኖርበት ከወትሮው በተለየ መልኩ አለመዘከሩ አግባብ አለመሆኑን አስተያየት ሰጭዎች ተችተዋል። እለቱን በማስመልከት የጥንታዊነት ኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ...
Read More »ሙስናን እንዋጋለን ቢባልም የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት መኖሪያ ቤቶችንና ድርጅቶችን ከመገንባት አልታቀቡም
ሚያዚያ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ ሙስናን እዋጋለሁ በሚል በጀመረው ዘመቻ፣በዝቅተኛ እርከን ላይ ያሉ አንዳንድ አመራሮችን ከስራቸው ላይ አንስቶ ወደ ሌሎች ቦታዎች በመመደብ፣ በተወሰኑት ላይ ደግሞ ክስ በመመስረት ከህዝብ የሚደርስበትን ነቀፋ ለማብረድ እየሞከረ ቢሆንም፣ በከፍተኛ አመራሮቹ ላይ የወሰደው እርምጃ ባለመኖሩ ፣ በህዝቡ ዘንድ ያለው ቅሬታ አሁንም ከፍተኛ ነው። በመጀመሪያዎቹ የስልጣናት ወራት፣ ሙስናን ለመዋጋት ቁርጠኛ መሆናቸውን ሲናገሩ ...
Read More »የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በኦነግነት ተከሰሰ
ሚያዚያ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኃላፊው አቶ ዮናታን ተስፋዬ በጸረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ቁጥር 652 አንቀጽ 4 ስር የተመለከተውን ተላልፈሀል ተብሎ ነው የሽብር ክስ የተመሰረተበት፡፡ የአቶ ዮናታን ክስ፤ ትናንት ሚያዝያ 26/2008 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በዳኞች ቢሮ በንባብ ተሰምቷል። በንባብ በተሰማው የአቃቤ ህግ ክስ ላይ አቶ ዮናታን የአዲስ አበባ ከተማ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ሽፋን ...
Read More »