Author Archives: Central

ምርጫ ቦርድ የዶ/ር በየነ ጴጥሮስን ኢዴሃህን ጨምሮ 14 ፓርቲዎችን ከግንቦት 5 ቀን ጀምሮ መሰረዙን አስታወቀ

ግንቦት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከቦርዱ የተሰጠው መግለጫ እንደሚያመለክተው ፓርቲዎቹ በመተዳደሪያ ደንባቸዉ መሠረት ጠቅላላ ጉባኤ የሚያካሂዱበት ጊዜ ያለፈ በመሆኑና የሥራ ጊዜያቸው በተጠናቀቀው አመራሮች ምትክ አዲስ የአመራር አባላትን መርጦ ወዲያውኑ ለቦርዱ ባለማሳወቃቸው፣ በኦዲተር የተረጋገጠና በግንባሩ መሪ የተፈረመ የሃብትና እዳ ሰነድ የጽሑፍ ሪፖርት ባለማቅረባቸው፣ ፓርቲው ያለውን ዋና ጽሕፈት ቤት እና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች አድራሻ፣ የጽሕፈት ቤቶቹን ኃላፊዎች ወይም ተወካዮች ...

Read More »

አልሻባብ በኢትዮጵያ ጦር ላይ ጥቃት ሰነዘረ

ኢሳት (ግንቦት 8 ፥ 2008) በአለም አቀፍ ደረጃ በአሸባሪነት የተፈረጀውና፣ በሶማሊያ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አለው የሚባለው አልሻባብ፣ በሶማሊያ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ወታደሮችንና የሶማሊያን ሰራዊት ላይ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ጥቃት መሰንዘሩ ተነገረ። አልሻባብ የወሰደው የጥቃት እርምጃ የተፈጸመው ዛሬ ሰኞ የሂራን የአስተዳደር ማዕከል በሆነችው ባልደዋይን ከተማ አቅራቢያ መሆኑን የሶማሊያ ድረ-ገጾች ከስፍራው እማኞችን በመጥቀስ ዘግበዋል። በሶማሊያና አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ለሚዘግብ “ማረግ” ለተሰኘው ድረ-ገፅ ...

Read More »

የውጭ ምንዛሪ ያመጣሉ ተብለው ድጋፍ ሲደረግላቸው የነበሩ 19 ኩባንያዎች በዚህ አመት ምንም አለማምረታቸው ታወቀ

ኢሳት (ግንቦት 8 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የጨርቃጨርቅ ምርትን ለውጭ ገበያ እንዲያቀርቡ የተለያዩ ድጋፎች ሲደረጉላቸው ከቆዩ 60 ኩባንያዎች መካከል 19ኙ በተያዘው በጀት አመት ምንም ምርት ሳይልኩ መቅረታቸው ተገለጠ። ኩባንያዎቹ ሲጠበቅባቸው የነበረን ምርት ከውጭ ገበያ ባለማቅረባቸው ምክንያትም መንግስት በበጀት አመቱ ሊያገኝ ካሰበው የውጭ ምንዛሪ ውስጥ የ45 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ መመዝገቡን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ይሁንና 19 የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች የተለያዩ ድጋፎች ...

Read More »

የዶ/ር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ቀብር ነገ ማክሰኞ ይፈጸማል

ኢሳት (ግንቦት 8 ፥ 2008) በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ለረጅም አመታት በአሰልጣኝነት ሲያገለግሉ የነበሩት ዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬ ባደረባቸው ህመም እሁድ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። የእኝሁ አንጋፋ አሰልጣኝ የቀብር ስነስርዓት ማክሰኞ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኝው የቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን እንደሚፈጸምም ታውቋል። በ1942 ዓም በሰሜን ሸዋ ተጉለትና ቡልጋ የተወለዱትና ለኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ስፖርት አባት የሚል መጠሪያ ያላቸው አንጋፋው አሰልጣኝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጤና ...

Read More »

የተዛቡ ምስሎችን በድረገጾቸው ላይ የለጠፉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴርና ኢቢሲ አንባቢዎችን ይቅርታ ጠየቁ

ኢሳት (ግንቦት 8 ፥ 2008) የመንግስት ኮሚውኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን  ከአርበኞች ግንቦት ሰባት የተማረኩ ጦር መሳሪያዎችና የመንገድ ግንባታ ናቸው በሚል በድረገጾች ላይ የተለጠፉ ምስሎች የኢትዮጵያ ያልሆኑ መሆናቸውን በማስመልከት በማህበራዊ ድረ-ገጽ ተጠቃሚዎች በደረሰባቸው ጫና ምስሎቹን ማንሳታቸው ታወቀ። የመንግስት ኮሚውኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትና በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮሮፖሬሽን በድረገጾቻቸው ላይ ያሰራጯቸው ሁለት ምስሎች በኢትዮጵያ ውስጥ ያልተነሱ መሆናቸውን ማህበራዊ ድረገጽ ተጠቃሚዎች ስለደረሱባቸው መስሪያ ቤቶቹ ...

Read More »

በደንቢያ የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ መምህራን አድማ እንደቀጠለ ነው

ግንቦት ፰(ሥምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደንቢያ ወረዳ በቆላድባ ከተማ የሚገኘው የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጅ መምህራን ባለፈው አርብ የጀመሩትን አድማ በመቀጠላቸው ተማሪዎች ወደ ቤታቸው መመለሳቸው ታውቋል። የወረዳው ባለስልጣናት አድማውን ከሚያደርጉ መምህራን ጋር ለመነጋገር ያደረጉት ሙከራ ፣ መምህራኑ ባሳዩት ጠንካራ አቋም ምክንያት አልተሳካም። የአድማው መነሻ ኮሌጁን ሲያስተዳድሩ የነበሩት መምህር ሙሉ አበበ እና ምክትላቸው ሰይድ ካሴ ከሃላፊነታቸው በመነሳታቸው ነው። መምህራኑ “የመብት ...

Read More »

አሸዋ ሜዳ በሚባለው አካባቢ የተገነቡት የኮንዶሚኒዬም ቤቶች ሙሉ በሙሉ ለኢህአዴግ ካድሬዎች ተሰጡ

ግንቦት ፰(ሥምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እሁድ ግንቦት7፣ 2008 ዓም በኦሮምያ ልዩ ዞን ወደ አምቦ መስመር መውጫ አሻዋ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተገነቡት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ሙሉ በሙሉ ለኢህአዴግ ባለስልጣናትና ካድሬዎች መሰጠቱን ወኪላችን ገልጿል። ቤቶቹ ከተገነቡ ብዙ አመታትን ማስቆጠራቸውን የገለጸው ወኪላችን፣ በቅርቡ በተካሄደው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ቆጠራ ይህ አካባቢ መተላለፉን ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። እነዚሁ የመንግስት ባለስልጣናትና ካድሬዎች የተሰጣቸውን ቤት ...

Read More »

በርካታ ወታደሮች የኢህአዴግን መንግስትን በመክዳት ወደ ትጥቅ ትግሉ መቀላቀላቸውን የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ይፋ አደረገ።

ግንቦት ፰(ሥምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትህዴን ባወጣው መግለጫ ከድተው ወደ ድርጅቱ ከተቀላቀሉት መካከል የ14ቱን የትውልድ ቦታ፣ ስም፣ የነበሩበትን ክፍለ ጦር፣ ሬጅመንትና ሻምበል በዝርዝር አመልክቷል። ከከዱት መካከል አንዳንዶቹ ማዕረግ ያላቸው ሲሆኑ፤ ማዕረግ የሌላቸው በርካታ ወታደሮችም ይገኙበታል። ሥርዓቱን ከድተው ወደ ት ህዴን መቀላቀላቸውን ያስታወቁት ወታደሮች በሰጡት አስተያዬት፦” እኛ ወታደሮች የገዢው ሰርአት እድሜ ማራዘሚያ ከምንሆን፤ በዚህ ወቅት በሀገራችን እየተከሰተ ያለው የእርስ ...

Read More »

በአማራ ክልል የሳንቲም እጥረት ተፈጠረ

ግንቦት ፰(ሥምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ዘጋቢያችን እንደገለጸው በተለይ በክልሉ ዋና ከተማ ባህርዳር የአንድ ብር ሳንቲም እጥረት በመከሰቱ ታክሲዎች ፣ ደንበኞቻቸውን ከማሳፈራቸው በፊት ጥያቄያቸው “ ዝርዝር ሳንቲም ይዘሃል ?” የሚል ሆኗል። ለተፈጠረው የሳንቲም እጥረት ትክክለኛ ምክንያቱን ለማወቅ ባይቻልም፣ ባለፈው አመት መጋቢት ወር ድምጻችን ይሰማ የጠራው የሳንቲም መሰብሰብ ሰላማዊ የተቃውሞ ማእቀብ ውጤት ሊሆን እንደሚችል አንዳንድ ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።

Read More »

አሜሪካ ተጨማሪ 128 ሚሊዮን ዶላር የሰብዓዊ ዕርዳታ አደረገች

ግንቦት ፰(ሥምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (USAID) እንዳስታወቀው የሰብዓዊ ድጋፉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በ50 ዓመታት ውስጥ አስከፊ የተባለውን ድርቅ እንዲቋቋም ለማገዝ ነው። በአሁኑ ወቅት አብዛኛው ሕዝብ ረሃቡን መቋቋም ከሚችለው በላይ እንደሆነበት የገለጸው ተራድኦ ድርጅቱ፣ የዛሬው ተጨማሪ ድጋፍ የሰብዓዊ ምግብ ዕርዳታ፣ የንጹህ መጠጥ ውኃ፣ የተመጣጠነ ምግብ አገልግሎትና ተንቀሳቃሽ የጤና ቡድንን ያካተተ ወሳኝ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ ...

Read More »