ግንቦት ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሚሆኑ የአማራ ብሔር ተወላጆች ከነባር ይዞታቸው መፈናቀላቸውን አስመልክቶ ለአማራ ክልል ብሶታቸውን አሰምተዋል። ለአሶሣ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ተብሎ ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት 163 ሺህ ሄክታር መሬታቸው ላይ ካለምንም ካሳ ተነስተው ጎዳና ላይ መጣላቸውን ገልጸዋል። እስከ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ድረስ አቤት ቢሉም ሰሚ አካል ማጣቸውንና የፍትሕ ያለህ ...
Read More »Author Archives: Central
የሃገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊ የነበሩት አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካዔል 10 አመት ተፈረደባቸው
ኢሳት (ግንቦት 9 ፥ 2008) ከአንድ አመት በፊት ለእስር የተዳረጉትና በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል ክስ በቅርቡ ጥፋተኛ የተባሉት የቀድሞ የሃገር ውስጥ የደህንነት ሃላፊ የአስር አመት ፅኑ እስራት ተላለፈባቸው። የደህንነት ሃላፊ የነበሩት አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካዔል ከተላለፈባቸው የእስር ቅጣት በተጨማሪም የ50 ሺ ብር ቅጣት የተወሰነባቸው ሲሆን፣ ወንድማቸውና እህታቸውም በአራትና በሶስት አመት እስራት መቀጣታቸውንም ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የደህንነት ሃላፊ የነበሩት አቶ ወልደ ...
Read More »በሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በጸጥታ ሃይሎች እየታፈኑ ነው ተባለ
ኢሳት (ግንቦት 9 ፥ 2008) በሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ታፍነው እየተወሰዱ እንደሆነ ታወቀ። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎችም ሰሞኑን የተመታውን የምግብ ማቆም አድማ ተከትሎ 5 የሚሆኑ ስማቸው ያልተገለጹ ተማሪዎችን ከግቢ አፍነው በመውሰድ የት እንዳደረሷቸው እንዳልታወቀ ኢሳት ያነጋገራቸው ተማሪዎች ከሃረማያ ዩኒቨርስቲ ተናግረዋል። እነዚህ ተማሪዎች ታፍነው የተወሰዱበት ምክንያት ፖለቲካዊ ሊሆን እንደሚችልና ከዚህ በፊት በተደረጉ ተቃውሞ እንቃስቃሴዎች ጋር ግንኙነት ሊኖራቸው ይችላል ተብለው ተጠርጥረው ...
Read More »በሙርሌ ታጣቂዎች ታፍነው ከተወሰዱት ህጻናት መካከል 44 የሚሆኑ መመለሳቸው ተነገረ
ኢሳት (ግንቦት 9 ፥ 2008) ከአንድ ወር በፊት በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን ድንበር ተሻግረው በመጡ በሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከተጠለፉት 125 ከሚሆኑት ህጻናት ውስጥ 44 ያህሉ ትናንት ሰኞ ወደ ጋምቤላ ክልል መመለሳቸው ተገልጸ። ህጻናቱ የተመለሱት ከጠላፊዎች ጋር በተካሄደው ረጅም ጊዜ በፈጀ ድርድር እንደሆነ ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል። ከ1 እስከ 5 ዓመት እድሜ ውስጥ የሚገኙት እነዚህ ህጻናት እንዲመለሱ የተደረጉት ወደ ጋምቤላ ክልል ሲሆን፣ ...
Read More »በህገወጥ መንገድ ወደ ተባበሩት አረብ ኤመሬትስ የሚጓዙ ኢትዮጵያውይን ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ
ኢሳት (ግንቦት 9 ፥ 2008) መንግስት ወደተባበሩት አረብ ኤመሬት የሚደረግ የሰራተኞች ጉዞ እንዲቋረጥ ቢያደርግም በየዕለቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ተለያዩ የአረብ ሃገራት በህገ-ወጥ መንገድ በመጓዝ ላይ መሆናቸው ተገለጠ። ባለፈው አንድ አመት ብቻ በተመሳሳይ ሁኔታ የተጓዙና የተለያዩ ችግሮች ያጋጠሟቸው 5ሺ ኢትዮጵያውያን በቅርቡ ወደሃገራቸው እንዲመለሱ መደረጉንም ባለስልጣናት አስታውቀዋል። የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ከሃገር በመውጣት ላይ ያሉ ሰዎችን መቆጣጠር እንዳልተቻለና በርካታቹ ህጋዊ ...
Read More »የኔዘርላንድስ እና የአሜሪካ መንግስታት በድርቅ ለተጠቁ ኢትዮጵያውያን ዕርዳታ ለገሱ
ኢሳት (ግንቦት 9 ፥ 2008) የኔዘርላንድ መንግስት በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ በምግብ እጦት ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን የሚሆን የሶስት ሚሊዮን ልዩ የእርዳታ ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ። የኔዘርላንድስ ውጭ ንግድ እና የእድገት ትብብር ሚኒስትር የሆኑት ሊላን ፕሉሜን ኔዘርላንድ ታይምስ ለሚባለው ድረ-ገጽ እንደተናገሩት ተጨማሪ እርዳታው ለህጻናት ምግብ አገልግሎት እንዲውል የተመደበ መሆኑን ተናግረዋል። ሚኒስትሯ የተጨማሪ 3 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታን አስፈላጊነት ሰኞ ለመገናኛ ብዙሃን ሲናገሩ፣ “ከጥቂት ወራት ...
Read More »በቃፍቲያ ወረዳ የሚኖሩ የወልቃይት ተወላጆች በትግራይ ክልል ስር አንተዳደርም አሉ
ኢሳት (ግንቦት 9 ፥ 2008) በትግራይ ክልል የሚገኙ ከአራት ሺ በላይ የቃፍቲያ ሁመራ አካባቢ የወልቃይት ተወላጆች በትግራይ ክልል ስር አንተዳደርም በማለት ሰኞ አዲስ የቃለ መሃላ ውሳኔ አስተለለፉ። በተወላጆቹ ሲነሳ የቆየው አስተዳደራዊ ጥያቄ ፍትሃዊ ምላሽን ባለማግኘቱ ምክንያትም አካባቢው አሁንም ድረስ በውጥረት ውስጥ መሆኑን የአካባቢው ተወላጆች ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አስተድተዋል። ከትግራይ ክልል ሃላፊዎች እየደረሰባቸው ያለው ጫናና ግፊት እየተጠናከረ መምጣቱን የሚናገሩት ...
Read More »በማጀቴ ከተማ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
ግንቦት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ሸዋ ዞን በአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ የሚገኙ የማጀቴ ንኡስ ወረዳ ነዋሪዎች የገምዛ ወረዳ ይመለስልን በሚል የጀመሩት ተቃውሞ እየሰፋ መሄዱን ተከትሎ የመንግስት አመራሮችና ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወደ ዋናው ከተማ ሄደዋል። ግንቦት3 ቀን 2008 ዓም የክልሉ የፍትህ ሃላፊና የክልሉ የህዝብ ግንኑነት ተጠሪ ወደ አካባቢው ከተንቀሳቀሱና ህዝቡን ካነጋገሩ በሁዋላ፣ የህዝቡ ጥያቄ ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጻቸው፣ በእለቱ ...
Read More »ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ያልተወራረደ ሂሳብና ከ540 ሚሊዮን ብር በላይ ህገወጥ ግዢ መፈጸሙን ጄኔራል ኦዲተር አስታወቀ
ግንቦት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል ዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ የ2007 በጀት አመት ኦዲት ካደረጋቸው 145 የመንግስት መ/ቤቶች መካከል 94 ያህሉ ከ 2 ቢሊየን ብር በላይ ሂሳባቸውን በወቅቱ ሳያወራርዱ የተገኙ ሲሆን ፣ 77 መ/ቤቶች ደግሞ ከ546 ሚሊየን ብር በላይ ከህግ ውጪ ግዥ ፈጽመው መገኘታቸውን ይፋ አድርገዋል። ዋና ኦዲተሩ በዛሬው እለት ለፖርላማ ባቀረቡት የ2007 በጀት አመት ሪፖርት 2 ...
Read More »በሃረር እና ደሴ ከተሞች ከሚፈርሱ ቤቶች ጋር በተያያዘ በርካታ ቤተሰቦች ለችግር ተዳርገዋል
ግንቦት ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ በላይነህ ተስፋዬ የተባሉ የሃረሪ ክልል ምክር ቤት አባል እና ባለሃብት፣ ህዳር 29፣ 2009 ዓም ለሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች በአል በአምስት ወራት ውስጥ 75 ሆቴሎችን እገነባለሁ በሚል ከ30 በላይ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ድርጅቶችን እንደፈርሱ በማስደረጋቸው ከ300 ያላነሱ ዜጎች ችግር ላይ መውደቃቸውን ወኪላችን ከስፍራው ዘግቧል። የአንዳንድ ነጋዴዎች የንግድ ድርጅቶች ከ 30 እና 40 አመታትን ...
Read More »