Author Archives: Central

በሱዳን አብዬ ግዛት የሞቱ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ቁጥር 16 ደረሰ

ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2008) ሁለቱ ሱዳኖች የይገባኛል ጥያቄን አንስተው በሚገኙባት የአብዬ ግዛት በሰላም ማስከበር ስራ ላይ ተሰማርተው ከሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች መካከል በተለያዩ ጊዜያት የሞቱ ወታደሮች ቁጥር 16 መድረሱን የተባበሩት መንግስታት የልዑካን ቡድን ገለጠ። የሰላም አስከባሪ ቡድኑ ሰላም ማስከበር ስራ ላይ ተሰማርተው ህይወታቸው ላጡ ወታደሮች ቤተሰቦች የክብር የሜዳሊያ ስጦታን ሰሞኑን በአብዬ ግዛት ማበርከቱን የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ሁለቱ ሱዳኖች በነዳጅ ...

Read More »

ግብፅ ከሃያ በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በግዳጅ ወደ ኢትዮጵያ መለሰች

ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2008) የግብፅ መንግስት በሃገሪቱ በኩል ወደ ሌላ ሃገር በህገወጥ መንገድ ለመጓዝ ሙከራን አድርገዋል ያላቸውን ከ20 በላይ ኢትዮጵያውያን፣ የሱዳን እንዲሁም የናይጀሪያን ተወላጆችን በግዳጅ ወደ ሃገራቸው መመለሱ ታውቋል። መቀመጫቸውን በካይሮ ያደረጉ የየሃገራቱ የኤምባሲ ተወካዮች ስደተኞቹን ወደሃገራቸው ለመመለስ ትብብር ያደረጉ ሲሆን፣ 24 የሚሆኑት ስደተኞች በአራት እስር ቤቶች መቆየታቸውን ካይሮ ፖስት ጋዜጣ ማክሰኞ ዘግቧል። የግብፅ መከላከያ ሰራዊት በበኩሉ ባለፉት 10 ...

Read More »

በደቡብ  አብዛኛው አርሶአደር የታጠቀው መሳሪያ ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ ሲሆን በአማራ ክልል የእዝ ቁጥጥሩ የጠበቀ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ

ግንቦት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ወይም ሜቴክ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የጸጥታ ሃይሎችን ለመለየት እንዲያስችል በሚል በደቡብ እና በአማራ ክልሎች በ2006 ዓ.ም ያደረገው ጥናት ዝርዝር ለኢሳት የደረሰ ሲሆን ፣ ጥናቱ እንደሚያሳዬው በደቡብ ክልል አብዛኛው አርሶአደር የታጠቀው  ዘመናዊ መሳሪያ ክላሽ ሲሆን፣ ይህ የጦር መሳሪያ ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ውጭ ነው። “የፖሊስና የሚሊሻ ሃይል ከታጠቅው በህብረተሰቡ ...

Read More »

ህዝቡ  “ለቀብራችን ደርሳችሁዋል” በማለት ለኢህአዴግ  “ምስጋናውን” አቀረበ

ግንቦት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 25ኛ አመቱን በማክበር ላይ ያለው ኢህአዴግ ፣ ህዝቡን ለማወያየት በባህርዳር በጠራው ስብሰባ ላይ አባሎቹ “ ኢህአዴግ ለቀብራችን ደርሰህልናልና እና እናመሰግንሃለን” ሲሉ ተሳልቀውበታል። አንድ  አስተያየት ሰጪ “ይህ ህዝብ ያለቀና የሞተ ህዝብ ነው፤  አሁን ነው እንዴ የምትመጡት? ፣ ለህዝቡ ቀብር መጥታችሁዋል ጥሩ ነው ያሉ ሲሆን መንግስት በዲሞክራሲ ረገድ አገኘሁት በማለት ያቀረበውን የድል ዜና ...

Read More »

ከአስር ዓመት በላይ የመስሪያ ቦታ ጠይቀው ምላሽ ያላገኙ ወጣቶች ቅሬታቸውን አቀረቡ፡፡

ግንቦት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአስር ዓመት በፊት በህጋዊነት ተደራጅተው ሎጂ ( የመዝነኛ ቦታ)  በመገንባት በቱሪስቱ ዘርፍ ለመስራት ጠይቀው የተሰጣቸውን ቦታ ያለ አግባብ በባለሃብት ሲነጠቁ የከተማ አስተዳደሩ ምላሽ አለመስጠቱ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው የላሊበላ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ፡፡ የገዥው መንግስት አመራሮች አርባአራት ስራአጦችን በ 1996 ዓም.እንዲደራጁ ካደረገ በኋላ በ1997 ዓም.በተካሄደው ሃገራዊ ምርጫ “ተቃዋሚን ትደግፋላችሁ!” በማለት ለወጣቶች የተዘጋጀውን አራት ነጥብ ...

Read More »

ወጣት አቤል በመከላከያ ሰራዊት አባላት ታፍኖ ከተወሰደ ከ4 አመታት በሁዋላ ያላበት አለመታወቁን ዘመዶቹ ተናገሩ

ግንቦት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪነቱ በሃረር ከተማ ሸንኮር ሰፈር የሆነው ወጣት አቤል ሆሶ ሁቤር በመከላከያ ሰራዊት ከእስር ቤት ተወስዶ እስካሁን ድረስ የደረሰበት አልታወቀም። ከአራት አመታት በፊት በታክሲ ሹፌርነትና በመካኒክነት ሙያ ይተዳደር የነበረው ከኢትዮጵያዊ እናትና ከኩባዊ አባት የተወለደው በቅጽል ስሙ አቤል ኩባ መሰናዶ በሚባለው በሸንኮር ወረዳ በሚገኘው የሰራዊቱ መኖሪያ ውስጥ ይኖር ከነበረ አንድ የመከላከያ ሰራዊት ጋር ...

Read More »

መንግስት በአንድ ወር ውስጥ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና እንደሚያዘጋጅ አስታወቀ

ግንቦት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና  አስቀድሞ መውጣቱን ተከትሎ የፈተናውን መሰረዝ በተምታታ መግለጫ ያወጀው መንግስት፣ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አፋጣኝ የሆነ ፈተና እንደሚሰጥ አስታውቋል። ፈተናው ከሰኔ 27-30 እንደሚሰጥ የተገለጸ ቢሆንም፣ ሰኔ 28 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የኢድ አል ፈጥር በአልን የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ በተማሪዎች ላይ የሚያመጣው ተጽእኖ ቀላል አይሆንም በማለት ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ነው። ...

Read More »

ሶስት የኢትዮጵያ ወታደሮችና ሁለት የሶማሊያ ጸጥታ ሃይል አባላት በሶማሊያ መገደላቸው ተነገረ

ኢሳት (ግንቦት 22 ፥ 2008) በሶማሊያ ሞቃዲሾና ጌዶ በተባሉት አካባቢዎች ሁለት የሶማሊያ ዜጎችና ሌሎች ሶስት ኢትዮጵያውያን በመንገድ ዳር በተጠመደ የተሽከርካሪ ፈንጅ መገደላቸው ተነገረ። ኢትዮጵያውያኑ ወታደሮች የተገደሉት የርቀት መቆጣጠሪያ መሳሪያ በተገጠመለት የመንገድ ዳር ፈንጅ ጌዶ በሚባል አካባቢ ሲሆን፣ በሶማሊያ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው አልሻባብ የተባለው ቡድን ሃላፊነት መውሰዱን ማሪግ የተባለው በሶማሊያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሚዘግበው ድረገጽ ዘግቧል። አልሻባብ የተገደሉት ኢትዮጵያውያን ወታደሮች በሶማሊያ ...

Read More »

በምግብ አቅርቦት ላይ እስከ 27 በመቶ የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ ተከሰተ

ኢሳት (ግንቦት 22 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች በመሰረታዊ የምግብ አቅርቦቶች ላይ እስከ 27 በመቶ የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ መከሰቱን የአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ሰኞ አስታወቀ። በሃገሪቱ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ 10.2 ሚሊዮን ሰዎች የሚያስፈልገው የምግብ ድጋፍ በወቅቱ ባለመድረሱና የተረጂዎች ቁጥም እየጨመረ በመሄድ በምግብ ሸቀጣሸቀጦች ላይ ከመቼው ጊዜ በላይ የዋጋ ንረት መከሰቱ አሳሳቢ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል። አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ ...

Read More »

የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሃመንድ በኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለጸ

  ኢሳት (ግንቦት 22 ፥ 2008) በእስር ላይ የሚገኙ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በቂ ህጋዊ ድጋፍን አላገኙም በማለት ለኢትዮጵያ መንግስት ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎችን ሲሰጡ የቆዩት የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሃመንድ ነገ በስቲያ ረቡዕ በኢትዮጵያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለጸ። ሚኒስትሩ ሃመንድ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ብሪታኒያ ለምታነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ የማትሰጥ ከሆነ የሁለቱ ሃገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙንት ሊሻክር ይችላል ሲሉ በቅርቡ መግለጻቸው ይታወሳል። የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ...

Read More »