ሰኔ ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እስካሁን ድረስ በገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ማጣራት መሰረት ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሚሆኑ ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውንና ከ10 ሽህ በላይ የሚሆኑ ሰላማዊ ዜጎች በእስርቤት ሰቆቃ ዘግናኝ ግፍ እየተፈጸመባቸው እንደሚገኙ ሂውማን ራይትስ ወች ለተ መ ድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት በሪፓርቱ ገልጿል። የጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ትኩረት በመስጠት ካለምንም ቅድመ ሁኔታዎች ...
Read More »Author Archives: Central
በደቡብ ሱዳን የተሰማራው የሰላም አስከባሪ ጦር ትችት ቀረበበት
ሰኔ ፲፭ (አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሥር የደቡብ ሱዳን የሰላም አስከባሪ ጦር ሰላማዊ ዜጎችን ከለላ መስጠት አልቻለም ተባለ። በእርስበርስ ጦርነት የምትታመሰው አዲሲቷ አገር ደቡብ ሱዳን በማላካል ከተማ ውስጥ እልቂት ሲፈፀም በስፍራው የነበሩት የሰላም አስከባሪ ጦር አባላት የሰላማዊ ዜጎችን ሕይወት ለመታደግ እንዳልቻሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምርመራ ቡድን ጥናት ሪፓርት አስታውቋል። ቁጥራቸው 48 ሽህ በላይ ...
Read More »የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራዝ ኪሳራ እንዳጋጠመው ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 14 ፥ 2008) በቅርቡ የገቡበት ባልታወቀው ከ5 ሺ በላይ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቆጠር ኪሳራ እንዳጋጠመው ተገለጸ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከእነዚሁ ተቋማት መሬት እና ከፍተኛ ብድር በማቅረብ የስራ እድል ፈጠራን ለማስፋፋት ጥረት ቢያደርግም እቅዱ በተቃራኒው ኪሳራ መስመዝገቡ ተውቋል። የአዲስ አበባ ከተማ ከአስር አመት በፊት ማቋቋም ለጀመረው ለዚሁ ፕሮግራም በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ መድቦ የነበረ ሲሆን ሰሞኑን የከተማዋ አስተዳደር ...
Read More »አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የተያዙበትን 2ኛ አመት ለማስታወስ ትዕይንት ተካሄደ
ኢሳት (ሰኔ 14 ፥ 2008) የግንቦት 7 መስራችና ዋና ጸሃፊ የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን በጸጥታ ሃይሎች ታፍነው ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው የተሰጡበትን 2ኛ ዓመት ለማስታወስ በዋሽንግተን ዲሲ ህዝባዊ ትዕይት ተካሄደ። የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች በተገኙበት ሰኞ በዋሽንግተን ዲሲ ብሪታኒያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በተካሄደው ህዝባዊ ትዕይንት የብሪታኒያ መንግስት ሃላፊነቱን በአግባቡ አልተውጣም የሚል ተቃውሞ ቀርቧል። የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ታናሽ እህት እስከዳር ጽጌ እንዲሁም ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት ያለበት እዳ 36.6 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 14 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት እስከ ፈረንጆች አቆጣጠር 2015 ዓም ማጠናቀቂያ ድረስ ያለበት አጠቃላይ እዳ 36.6 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገለጠ። ይኸው የሃገሪቱ የእዳ መጠን ከአጠቃላይ ሃገራዊ ምርት ጋር ሲነጻጸር ወደ 55 በመቶ የሚደርስ ሲሆን፣ መንግስት ከሚያጸድቀው በጀት ውስጥ ለእዳ ክፍያ የሚመደበው ገንዘብ እየጨመረ መምጣቱ ታውቋል። ለ2009 ዓም ከተያዘው 274 ቢሊዮን ብር በጀት መካከል መንግስት ወደ 14 ቢሊዮን ለእዳ ...
Read More »የአቶ አባይ ወልዱ ባለቤት በአውስትራሊያና ኒውዚላንድ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ፥ ሌሎች የህወሃት አባላት ቁልፍ ቦታዎች ላይ እየተሾሙ ናቸው
ኢሳት (ሰኔ 14 ፥ 2008) የትግራይ ክልል ፕሬዚደንትና የህወሃት ሊቀመንበር የአቶ አባይ ወልዱ ባለቤት በአውስትራሊያና ኒውዚላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ። ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ የህወሃት አባላትና አመራሮች በአምባሳደርነት በብዛት መሾም ያስፈለገበት ምክንያት ያልታወቀ ሲሆን፣ የዋሽንግተኑንም የአምባሳደርነት ስፍራ ወደ ህወሃት ታጋይ እንደሚተላለፍ ተሰምቷል። ስፍራው ለህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ለአቶ ብርሃነ ኪዳነማሪያ እንደሚሰጥ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በቅርቡ በብሪታኒያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አቶ ብርሃኑ ...
Read More »በጨለንቆ አንዲት ወጣት መገደሏን ተከትሎ ተቃውሞ በመቀስቀሱ መንገድ ተዘጋ
ኢሳት (ሰኔ 14 ፥ 2008) በምስራቅ ሃረርጌ ጨለንቆ ውስጥ የአንዲት ወጣት መገደልን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ በዛሬው ዕለት መንገድ መዘጋቱን የአይን ምስክሮች ከስፍራው ገለጹ። የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሳብሪና አብደላ የተባለች ወጣት ከመስጊድ ወጥታ ስትሄድ በፖሊሶች መገደሏን በመቃወም በተነሳው ተቃውሞ ፖሊሶች ቀብሩን ለመከፋፈል የሞከሩ ቢሆንም፣ በመጨረሻ የቀብሩ ስርዓት መፈጸሙን መረዳት ተችሏል። ፖሊሶች የግለሰቦችን ጸብ ለማብረድ በሚል ተኩሱን እንደከፈቱ ለኢሳት ከስፍራው የተናገሩት ...
Read More »አየር ሃይል የበረራ ስልጠናውን ሙሉ በሙሉ ወደ ድሬዳዋ አዛወረ
ሰኔ ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት አየር ሃይል በዚህ ሳምንት አዳዲስ በገዛቸው የጦር አውሮፕላኖቹ ድሬዳዋ ላይ ወታደራዊ ልምምድ የሚጀምር ሲሆን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፓይለት ስልጠና ( pilot Training base) መቀመጫውን እስከሳምንቱ መጨረሻ ድረስ ከድሬዳዋ ወደ መቀሌ እንዲያዛውር ትእዛዝ ተላልፎለታል። አየር ሃይል “ለአገራዊ ጉዳይ ቅድሚያ መስጠት አለባችሁ” በሚል ትእዛዝ አየር መንገዱ የድሬዳዋ የበረራ ማሰልጠኛውን ...
Read More »በጨለንቆ በተነሳው ተቃውሞ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ ዋለ
ሰኔ ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ሃረርጌ ከትናንት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው ተቃውሞ ምክንያት ከአዲስ አበባ ወደ ሃረር ከሃረር ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ በድንጋይ በመዘጋቱ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ አርፍዷል። አድማ በታኝ ፖሊሶች ከሃረር ወደ ጨለቆ በማምራት እና በህዝቡ ላይ በመተኮስ መንገዱን ቢያስከፍቱትም፣ ተቃውሞው ግን ይህን ዜና እስካጠናከርንበት በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር እስከ 9 ሰአት ቀጥሎአል። ...
Read More »በአርባምንጭ የ76 አመቱ አዛውንት ተፈረደባቸው
ሰኔ ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብር ወንጀል ተከሶ 7 አመት የተፈረደበት የሰማያዊ ፓርቲ የአርባምንጭ ተጠሪ የአቶ በፈቃዱ አበበ አባት የሆኑት አቶ አበበ አስፋው ትናንት ፍርድ ቤት ቀርበው 1 አመት ከስድስት ወር የተፈረደባቸው ሲሆን፣ ውሳኔው እንደተላለፈ አዛውንቱ ወደ አርባምንጭ እስር ቤት ተልከዋል። በፈቃዱ የአርባ ምንጭ ወጣቶችን እየመለመልክ ለአርበኖች ግንቦት7 ትልካለህ በሚል መታሰሩን ኢሳት በወቅቱ ዘግቦ ነበር። ...
Read More »