Author Archives: Central

ከኦሮሚያ ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የታሰሩት ዜጎች ቁጥር 50ሺህ እንደሚደርስ ዶ/ር መረራ አስታወቁ

ኢሳት (ሰኔ 27 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል ከመንፈቅ በላይ የዘለቀው ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ወደ እስር ቤት የተጋዙ ዜጎች ቁጥር ከ40ሺህ እስከ 50ሺህ እንደሚገመት የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ገለጹ። ወጣቶቹ በስርዓቱ ላይ ተቃውሟቸውን ከሚገልጹባቸው መንገዶች አንዱ ባለስልጣናት ስርዓቱን እንዲያወግዙና መንገድ በድንጋይ እንዲዘጉ ማስገደድ እንደነበርም አመልክተዋል። ኦህዴድ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ብሎ መስከረም ወር ላይ ስራ ጀምሮ፣ በህዳር ...

Read More »

በጣሊያን ኢትዮጵያውያንንና ኤርትራውያን ህገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢሳት (ሰኔ 27 ፥ 2008) የጣሊያን ፖሊስ በህገወጥ ሰው አዘዋዋሪነት የተጠረጠሩ 12 ኢትዮጵያውየንና 25 ኤርትራውያንን በፖሊስ ቁጥጥር ስር ማዋሉን ሮይተርስ ሰኞ ባወጣው ዘገባ አስታወቀ። ተጠርጣሪዎቹ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ በሚያዘዋውር ድርጅት ውስጥ ሲሰሩ የነበሩ ናቸው ተብሏል። ህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ የተከሰሱት ክስ ስደተኞችን በማስገባት፣ ዕፅ በማዘዋወር፣ እና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር በማካሄድ እንደሆነ ተገልጿል፣ መረጃውም በ2014 ዓም በዚያው በጣሊያን አገር የታሰረው ...

Read More »

የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ (ESFNA) 33ኛ አመት በካናዳ በድምቀት ተከፈተ

ኢሳት (ሰኔ 27 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን አሜሪካ 33ኛ ዓመት በዓል በካናዳ ቶሮንቶ በድምቀት ተከፈተ። ከተለያዩ የካናዳ ግዛቶች እንዲሁም ከዩኤስ አሜሪካ የተጓዙ ኢትዮጵያውያን ጭምር እንደታደሙበት በተገለጸው በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያውያን በዓል፣ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከኢትዮጵያ ጭምር የተጓዙ ኢትዮጵያውያን በዝግጅቱ መሳተፋቸውን መረዳት ተችሏል። የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ፕሬዚደንት አቶ ጌታቸው ተስፋዬ ይህ ታላቅ የኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ መድረክ፣ “የኢትዮጵያውያን ሰንደቅ አላማ በባዕድ ...

Read More »

ኢትዮጵያዊ አርሶአደሮች 5 የሱዳን ወታደሮችን ገደሉ

በሰሜን ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ በሲናር በረሃ የኢትዮጵያን የእርሻ መሬት ለመውሰድ በተንቀሳቀሱ የሱዳን ወታደሮች ላይ ተኩስ የከፈቱት ኢትዮጵያዊ አርሶአደሮች 5 የሱዳን ወታደሮችን ገድለዋል። ሰኔ 25 ቀን 2008 ዓም የሱዳን ወታደሮች የጓንግን ወንዝ ተሻግረውና አንድ የእርሻ ካም አቃጥለው ጦርነት ሲከፍቱ ፣ በተለይ  ጎዳና አምዴ  የተባለው ወ   ጣት አርሶአደር እና አብረውት የነበሩት 5 የሱዳን ወታደሮችን ገድለው 3 ክላሽንኮቭ እና አንድ መትረጊስ ...

Read More »

የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት ሰፍኗል

የደቡብ ክልል የብሄረሰቦች ምክር ቤት ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓም የኮንሶ ህዝብ የራስ አስተዳደር ጥያቄ ውድቅ መደረጉን የሚግልጽ ደብዳቤ መጻፉን ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት መንገሱን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ምክር ቤቱ በደብዳቤው “ የክልሉ ህገመንግስት አንቀጽ 59 ንኡስ አንቀጽ 3 እና የብሄረሰቦች ምክር ቤትን ለማጠናከር ስልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር የወጣው አዋጅ ቁጥር 60/95 መሰረት አጠቃላይ የጥያቄው ይዘትና ምክንያቶችን መርምሮ በማየት የኮንሶ ህዝብ መሰረታዊና ...

Read More »

በአዲስ አበባ ቤታቸው የፈረሰባቸውን ሰዎች አሳዛኝ ህይወት የሚያሳዩ ፎቶግራፎች እየወጡ ነው

በወረዳ አንድ የሁለት ፖሊሶችንና የአንድ ወረዳ አስተዳዳሪን ህይወት ጨምሮ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ዜጎች የተገደሉትን የቤት ማፍረስ ዘመቻ ለመደበቅ መንግስት ጥረት ቢያደርግም ቤታቸው የፈረሰባቸውን ዜጎች ህይወት የሚያሳዩ ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተለቀቁ ነው። የፌደራል ፖሊሶች አካባቢውን አጥረው ምንም ሰው ወደ ውስጥ እንዳይገባ ጥረት ሲያደርጉ ሰንብተዋል። ይህን ተከትሎም አሽከርካሪዎች በመንገድ መጨናነቅ ሲቸገሩ ሰንብቷል። ነዋሪዎች እንደሚሉት መስተዳድሩ ድርጊቱ እንዳይታወቅበት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሆኖም የመስተዳድሩ ...

Read More »

በገላና ወረዳ አንድ የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ ተደበደበ

በሁሌ ቦራ ዞን በገላና ወረዳ ሜጄ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑትና ሰማያዊ ፓርቲን በመወከል ባለፈው ግንቦት ወር ምርጫ እጩ ተወዳዳሪ የነበሩት  አቶ ደስታ ቁጤ ከምሽቱ አንድ ሰአት ላይ በተፈጸመባቸው ድብደባ በእግሮቻቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶአቸው በህክምና እየተረዱ ነው። ማንነታቸው ያልታወቁት ግለሰቦች ጨለማን ተገን አድርገው ግለሰቡን መደብዳበቸውንና ከዚህ ቀደም ከደህንነቶች ማስፈራሪያ ሲደርሰው እንደነበር እንደነገሯቸው የዞኑ የሰማያዊ ፓርቲ ተወካይ አቶ ጌታቸው በቀለ ለኢሳት ተናግረዋል

Read More »

በአዲስ አበባ ከተማና አካባቢው ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው የማፈናቀል ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) ጠየቀ

ኢሳት (ሰኔ 24 ፥ 2008) በአዲስ አበባ ከተማና አካባቢው ዜጎችን ከቤት ንብረታቸው የማፈናቀል ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) ጠየቀ። ዜጎች ለረጅም ዓመታት በይዞታነት ግብር ሲከፍሉበት ከቆዩበት ቦታ “ህገወጥ ናችሁ” ብሎ ማፈናቀል በምንም መልኩ ተቀባይነት ያለው ድርጊት አለመሆኑን ድርጅቱ ባወጣው አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል። በቦሌ ክ/ከተማ ወረገኑ የሚባል አካባቢን ጨምሮ በተለያዩ ክፍለከተሞችና በአዲስ አበባ ከተማ ዳርቻ ለረጅም ጊዜ ከኖሩበት ...

Read More »

በአቶ ሃብታሙ አያሌው ላይ በፍርድ ቤት የተጣለበት እገዳ እንዲነሳ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቀረበ

ኢሳት (ሰኔ 24 ፥ 2008) በፍርድ ቤት ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ እገዳ ተጥሎበት የሚገኘውና በጽኑ ህመም ላይ የሚገኘው የአንድነት ፓርት አመራር አቶ ሃብታሙ አያሌው የተጣለበት እገዳ እንዲነሳለት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪውን አቅረበ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ለጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በላከው የጽሁፍ መልዕክት አቶ ሃብታሙ ከሰብዓዊ መብት አንጻር እገዳው በአስቸኳይ ሊነሳለት የሚገባ እንደሆነ አመልክቷል። በእስር ቤት ቆያታው የተለያዩ ስቃዮች በአቶ ሃብታሙ አያሌው ...

Read More »

በአወዳይ በተነሳው ተቃውሞ  ህጻናትን ጨምሮ  በትንሹ 4  ሰዎች ተገደሉ

ሰኔ ፳፬ ( ሃያ አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምስራቅ ሃረርጌ በአወዳይ ከተማ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የወረዳው አስተዳዳሪ በከፈተው ተኩስ  ሁለት ህጻናት እና  አንድ ጎልማሳ ተገድለዋል። ነዋሪዎች ማምሻውን ለኢሳት እንደገለጹት ከሆነ የሟቾች ቁጥር 7 ድርሷል። ኢብራሂም ሙሜ የሚባል ባለ ጸጉር ቤት እና አህመድ አልዬ የሚባል ባለሞባይል ቤት አሊ መሰራ ህንጻ እና አዋሽ ባንክ መሃል የሚገኘው ቤታቸው  ...

Read More »