ኢሳት (ሃምሌ 11 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ከተለያዩ የልማት ድርጅቶች ሲወስድ የቆየው አለም አቀፍና የሃገር ውስጥ ብድር ዕዳ የአገሪቱን እዳ የመክፈል አቅም እንደሚጎዳ አንድ አለም አቀፍ ተቋም አሳሰበ። ይኸው የመንግስት የውጭ ዕዳ የመሸከም አቅም እንዲገመገም በመንግስት ተቀጥሮ የነበረውና ፈች የሚል ስያሜ ያለው ኩባንያ የመንግስት የልማት ድርጅቶች እዳ እያሻቀበ መሆኑንና በድርጊቱ በብሄራዊ ደረጃ ስጋት እየሆነ መምጣቱን ይፋ አድርጓል። ኢትዮ-ቴሌኮምን ጨምሮ የኢትዮጵያ ...
Read More »Author Archives: Central
በጎንደር የተቀሰቀሰው ግጭት ወደሌሎች አካባቢዎች እየተዛመተ እንደሆነ ተነገረ
ኢሳት (ሃምሌ 11 ፥ 2008) የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በጎንደር በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ የተገደሉት የመንግስት ታጣቂዎች 11 መሆናቸውን የብሄራዊ መረጃና ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ። የተገደሉ ሰላማዊ ሰዎች ደግሞ 5 መሆናቸውንም አስታውቋል። ግጭቱ ከጎንደር ባሻገር በሌሎች አካባቢዎች መዛመቱንና ግጭት መከተሉንም አረጋግጧል። የብሄራዊ መረጃና ፌዴራል ፖሊስ የጸረ-ሽብር ግብረ ሃይል እሁድ ዕለት ባወጣው መግለጫ ተጠርጣሪ የተባሉ ግለሰቦችን ለመያዝ የመንግስት ሃይሎች በተንቀሳቀሱበት ወቅት በተከፈተባቸው ...
Read More »በጎንደር የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ በመንግስት በሽብርተኝነት መፈረጁ ተቃውሞ አስነሳ
ኢሳት (ሃምሌ 11 ፥ 2008) በቅርቡ በጎንደር ከተማና አካባቢው ከማንነት ጥያቄ ጋር የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ መንግስት በሽብርተኛ ድርጊት መፈረጁ በነዋሪው ዘንድ ተቃውሞ ማስነሳቱን የአርማጭሆ ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጡ። በአካባቢው አሁንም ድረስ ውጥረት መኖሩን የተናገሩት ነዋሪዎች ህዝቡ ዘርን ሳይለይ በአንድነት በመሆን መብቱን ለማስከበር ጥረት እያደረገ መሆኑን ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስረድተዋል። የመንግስት ባለስልጣናት ተቀስቅሶ የነበረውን ግጭት ከሽብርተኛ ድርጊት ጋር ማገናኘታቸው ህዝቡ ...
Read More »ህወሃት የጎንደርን ህዝብ የመብት ትግል በሽብርተኝነት እና በዘር ለመፈረጅ የሄደበት መንገድ እጅግ አበሳጭቶናል ሲሉ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት የኮሚቴ አባላት ተናገሩ
ሃምሌ 10 ቀን 2008 ዓም ብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ የጋራ ጸረ ሽብር ግብረሃይል የተባለ ተቋም በሰሜን ጎንደር በመካሄድ ላይ ያለውን ህዝባዊ የመብት ትግል በሽብርተኝነት እና በዘር በመፈረጅ በህዝቡ ውስጥ ጥርጣሬ እንዲፈጠር ያደረገው ሙከራ አሳፋሪ ነው ሲሉ የኮሚቴ አባላቱ ለኢሳት ገልጸዋል። ለጊዜው ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁት የኮሚቴው ከፍተኛ አመራር፣ አንድ አገርን እመራለሁ የሚል ፓርቲ ከሜዳ ተነስቶ የህወሃትን አመለካከቱ ማንጸባረቁ የወልቃይት ...
Read More »በጡረታ የተገለሉ የህወሃት የጦር መኮንኖች በአዲስ አበባ ሚስጢራዊ ስብሰባ እያደረጉ ነው
አንድ ሺ ያክል ቁጥር ያላቸው በጡረታ የተገለሉ የህወሃት አባላት የሆኑ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በአዲስ አበባ ከትናንት ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሚስጢራዊ ስብሰባ በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል። ጥሪው የተላለፈው ለትግራይ ተወላጅ የጦር መኮንኖች ብቻ መሆኑ በሰራዊቱ ውስጥ ያለው አለመተማመን እየሰፋ መምጣቱን ያሳያል በማለት የመረጃው ምንጮች አስተያየታቸውን ገልጸዋል። የስብሰባው አላማ ግልጽ ባይሆንም በጎንደር በመካሄድ ላይ ካለው ህዝባዊ አመጽ፣ በመላ አገሪቱ ከሚታዬው አለመረጋጋት ...
Read More »በሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደሮች 13 ንጹሃን ዜጎችን ገደሉ
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ሰላም አስከባሪነት ጦር አሚሶም ስር ሶማሊያ ውስጥ የተሰማራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ምንም ዓይነት የጦር መሳሪያ ያልታጠቁ 13 ሰላማዊ የሶማሊያ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ መፈጸሙ ተዘግቧል። ከባይደዋ ከተማ በስተምእራብ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው አውዲኒያ አቅራቢያ የግፍ ግድያው መፈጸሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸው፣ ከሞቱት13 ዜጎች በተጨማሪ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ዜጎች ላይ ከፍተኛና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። የኢትዮጵያ ወታደሮች ...
Read More »በጎንደር ከተማ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ጸረ-ሰላም በሆኑ የውጭ ሃይሎች የተቀነባበረ ነው ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ
ኢሳት (ሃምሌ 8 ፥ 2008) የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ከቀናት በፊት በጎንደር ከተማ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ጸረ-ሰላም በሆኑ የውጭ ሃይሎች የተቀነባበረ ነው ሲሉ አርብ ለመገኛኛ ብዙሃን አስታውቀዋል። ከግጭቱ ጋር በተገናኘ ስለደረሰው ጉዳት መረጃን ከመስጠት የተቆጠቡት ሚኒስትሩ የውጭ ሃይሎች ያሏቸውን አካላት በስም ያልጠቀሱ ሲሆን፣ ድርጊቱ ኢትዮጵያን የማተራመስ ተልዕኮ ነበረው ሲሉ አክለው ገልጸዋል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተጠርጣሪ የተባሉ አካላትን ለመያዝ ...
Read More »ለኤርትራ መንግስት መረጃን ሲያቀብሉ ነበሩ የተባሉ ዘጠኝ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
ኢሳት (ሃምሌ 8 ፥ 2008) በኢትዮጵያና የኤርትራ ድንበር አካባቢ ስላሉ በኢትዮጵያ ወታደሮች እንቅስቃሴ ለኤርትራ መንግስት መረጃን ሲያቀብሉ ነበሩ የተባሉ ዘጠኝ ግለሰቦች ከ3 ወር እስከ 4 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ ። ቅጣቱ ከተላለፈባቸዉ መካከል አምስቱ ኤርትራውያን መሆናቸዉንና ከ2004 ዓም እስከ 2006 ዓም ባሉት ጊዚያት ዉስጥ ከኤርትራ የመረጃ ሰራተኞች ጋር ሚስጢራዊ ግንጙነት በመፍጠር የስለላ ድርጊት ሲፈፅሙ መቆየታቸዉን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን አርብ ዘግበዋል። ...
Read More »በጎንደር የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ
ኢሳት (ሃምሌ 8 ፥ 2008) ከቀናት በፊት በጎንደር ከተማ ተቀስቅሶ ከነበረው ህዝባዊ አመጽ ጋር በተገናኘ በትንሹ 10 ሰዎች መገደላቸውና ድርጊቱ በከተማ ውጥረት ማንገሱን አለም-አቀፍ መገናኛ ብዙሃን አርብ ዘገቡ። በተለያዩ ጊዜያት ተመሳሳይ ድርጊቶች በበርካታ የሃገሪቱ አካባቢዎች ሲካሄዱ መሰንበቱን ያወሳው አልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ የቱሪስቶች መስሕብ የሆነችው ጎንደር ከተማ ያልተለመደ የስጋት ድባብ እንደሚታይበት በግጭቱ ዙሪያ ባቀረበው ሪፖርት አመልክቷል። በጎንደር በተቀሰቀሰው ግጭት ፖሊሶችን ጨምሮ ...
Read More »በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች የተወለዱ ህጻናት በአስከፊ የምግብ እጥረት ውስጥ መሆናቸው ተነገረ
ኢሳት (ሃምሌ 8 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ባለፉት ስድስት ወራት የተወለዱ ከ300 ሺ በላይ ህፃናት በአስከፊ የምግብ እጥረት ውስጥ መሆናቸዉን የካናዳ የክርስቲያን ችልድረንስ ፈንድ ገለጠ ። ድርቁ በህፃናትና በነፍሰ ጡር እናቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳትን እያደረሰ እንደሚገኝ ያስታወቀዉ ድርጅቱ፣ አዲስ የተወለዱት ህፃናት አፋጣኝ እርዳታን ካላገኙ ህይወታቸዉ አደጋ ውስጥ እንደሚሆን አሳስቧል። ድርቅ ጉዳት እየደረሰባቸዉ ባሉት አካባቢዎች ባሉበት ስድስት ወራቶች ውስጥ ...
Read More »