Author Archives: Central

በኦሮሚያ እና በጎንደር የተቀጣጠለው ህዝባዊ ተቃውሞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምሁራን ጠየቁ

ኢሳት (ሃምሌ 13 ፥ 2008) በኦሮሚያ እና በጎንደር የተቀጣጠለው ህዝባዊ ተቃውሞ ተጠናክሮ እና ተቀናጅቶ እንዲቀጥል ሁለት ታዋቂ ምሁራን ገለጡ። ከኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮና ቴሌቪዥን (ኢሳት) ጋር ቆይታ ያደረጉት ሁለት ምሁራን ለወራት የዘለቀው የኦሮሞ ህዝብ እንቅስቃሴና የጎንደር ህዝብ መብቱን ለማስመለስ የሚያደርገውን ትግል ተቀናጅቶ ከቀጠለ የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነቱ የሚያደርገው ጉዞ ሩቅ እንደማይሆነ አስታውቀዋል። በቺካጎ ኤሊኖይ ግዛት ሃርፐር ኮሌጅ የኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ጌታቸው ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት ዝግ ሆነው የቆዩ የፋይናንስ ህጎችንና መመሪያዎችን በማሻሻል ላይ መሆኑ ተነገረ

ኢሳት (ሃምሌ 13 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ያጋጠመውን የውጭ ምንዛሪና የፋይናንስ እጥረት ተከትሎ ለአመታት ዝግ ሆነው የቆዩ የፋይናንስ ህጎችንና መመሪያዎችን በማሻሻል ላይ መሆኑን አለም አቀፍ የፋይናንስ አካላት አስታወቁ። ሃገሪቱ መውሰድ የጀመረችውን እርምጃ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰድ ኬኒያና የተለያዩ ሃገራት የፋይናንስ ተቋማትና ባንኮች በፋይናንስ አቅርቦት ላይ ለመሰማራት ድርድር እያካሄዱ መሆኑን ዘ ስታንዳርድ የተሰኘ የኬንያ ጋዜጣ ማክሰኞ ዘግቧል። በኬንያ ብድርን በማቅረብ የሚታወቀው ...

Read More »

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ትብብር በጎንደር ህዝብ ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እንዲቆም ጥሪ አቀረበ

ኢሳት (ሃምሌ 13 ፥ 2008) የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ታንድ) በጎንደር ህዝብ ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እንዲቆም ጥሪ አቀረበ። የህዝብ መብት ጥያቄን ወደብሄር ቅራኔ ለመውሰድ የሚደረገው ሃላፊነት የጎደለው ተግባር እንዲታገድም አሳስቧል። በዶ/ር አረጋዊ በርሄ የሚመራው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ታንድ) “ጎንደር የህዝብ ትግል ሲግል፣ የኢህአዴግ ውድቀት ሊቀላጠፍ” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በጎንደር ሰላማዊ ህዝብ ላይ ባጠቃላይ ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ ...

Read More »

የግብጽ ምሁራን ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር በምታደርገው ድርድር ጊዜዋን እያጠፋች ነው አሉ

ኢሳት (ሃምሌ 13 ፥ 2008) የታላቁ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ በኢትዮጵያና በግብፅ መካክል እየተደረገ ያለው ድርድር ወደተሳሳተ አቅጣጫ እየሄደ ሲሉ የግብጽ የውሃ ሃብት ምሁራን ስጋታቸውን ገለጹ። በካይሮ ዩኒቨርስቲ የውሃን ሃብት ፕሮፈሰር የሆኑት ናደር ኖር ኤልዲን /ዴይሊ ኒውስ ለተባለ ጋዜጣ ሲናገሩ፣ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የተስማሙበት የአማካሪዎች ጥናት ለግብጽ የሚሰጠው ምንም ጥቅም የለም በማለት ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር በምታደርገው ድርድር ጊዜዋን እያጠፋች እንደሆነ መናገራቸው ...

Read More »

በእነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ መዝገብ በሽበርተኝነት የተከሰሱት የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈባቸው

ኢሳት (ሃምሌ 13 ፥ 2008) በእነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የክስ መዝገብ በጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ተከሳሽ የነበሩት ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካሳይ ላይ አቃቤ ህግ የመሰረተባቸውን ክስ በሰውና በማስረጃ ማስረዳት በመቻሉ የ14ኛው ወንጀል ችሎት የጥፋተኝነት ውሳኔ መተላለፉን የደረሰን ዜና ያመለክታል። አቃቤ ህግ በጸረ-ሽብርተኝነቱ አዋጅ የከሰሳቸው እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ 141 መከላከያ ምስክሮችን አስመዝገው እንደነበር የታወቀ ሲሆን፣ በተከሳሾች በኩል የተመዘገበው ጭብጥ ...

Read More »

በያቤሎ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄደ

ሐምሌ  ፲፫ ( አሥራ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ክልል በቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ  ሃምሌ 13 ቀን 2008 ዓም የከተማው ህዝብ በነቂስ በመውጣት ተቃውሞ ሲያካሂድ ውሎአል። ተቃውሞውን የጀመሩት ተማሪዎች ሲሆኑ፣ የከተማውም ህዝብ ተቀላቆሎአቸዋል። ከጥንት ጀምሮ የሞያሌ ወረዳ በቦረና ዞን ይተዳደር እንደነበር እየታወቀ፣ በየትኛውም ቦታ ባልታዬ ሁኔታ ወረዳው በሁለት ክልላዊ መንግስት ሲተዳደር መቆየቱ አግባብ ባለመሆኑ ወደ ቦረና ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ፍተሻው ተጠናክሯል

ሐምሌ  ፲፫ ( አሥራ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት በአማራ ክልል በተለያዩ ቦታዎች በተለይም በሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ በደቡብና ሰሜን ወሎ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ አውቶቡሶችና ሚኒባሶች በየቦታው እንዲቆሙ እየተደረገ ፣ ፖሊሶች መንገደኞችን እያስወረዱ መታወቂያ እየተቀበሉ ፍተሻ በማካሄድ ላይ ናቸው። ተሳፋሪዎች በተደጋጋሚ እንዲፈተሹ በመደረጋቸው ምሬታቸውን እየገለጹ ነው። የጎንደሩ ህዝባዊ አመጽ ወደ ሌሎች የክልሉ ከተሞች ይሸጋገራል የሚል ፍርሃት ...

Read More »

እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ተከላከሉ ተባሉ

ሐምሌ  ፲፫ ( አሥራ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርበኞች ግንቦት 7ትን ሊቀላቀሉ ሲሉ መንገድ ላይ ተይዘዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው ብርሃኑ ተክለያሬድ ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እንዲሁም የግንባሩ አባል ነው የተባለው ደሴ ካሳይ ፍርድ ቤት ቀርበው ጥፋተኞች ተብለዋል፡፡ 14ኛው ወንጀል ችሎት ውሳኔውን ያስተላለፈው ተከሳሾች የመከላከያ ምስክሮችን ባላቀረቡበት ሁኔታ ነው። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ የተለያዩ ታዋቂ ሰዎችንና ...

Read More »

ደቡብ ሱዳናውያን የአፍሪካ ሕብረት ተጨማሪ ሰላም አስከባሪ ጦር ወደ አገራቸው እንዳይገባ ጠየቁ

ሐምሌ  ፲፫ ( አሥራ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጁባ በተካሄደው ተቃውሞ ዜጎች ተጨማሪ ጦር ወደ አገራችን እንዲገባ አንፈልግም ብለዋል። በድጋሜ እንደ አዲስ ያገረሸውን የደቡብ ሱዳን የእርስ በርስ ጦርነትን ተከትሎ  ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬኒያ፣ ሩዋንዳ፣ ኡጋንዳና ሱዳን ሰራዊታቸውን ለመላክ ተዘጋጅተዋል። ውሳኔውን የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አውግዘውታል። ”እኛ አንድም ተጨማሪ ሰላም አስከባሪ ጦር ወደ አገራችን እንዲገባ ...

Read More »

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ኢትዮጵያውያን ከአፋኝ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት  እንዲተባበሩ ጥሪ አቀረበ

ኢሳት ((ሃምሌ 12 ፥ 2008) የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኦዴግ/ ከጎንደር ህዝብ ጎን እንደሚሰለፉ አስታወቁ። የጎንደር ህዝባዊ እንቅስቃሴ መሪዎች ትግላቸውን ከኦሮሞ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ጋር እንዲያቀናጁና ሌሎች ኢትዮጵያውያን  ከአፋኝ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል። በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (አዴግ) ሰኞ ሃምሌ 11 ፥ 2008 ባወጣው መግለጫ ህዝብ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለመብት ትግል የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ዕመቃ እንደማያቆመው፣ በኦሮሚያ ...

Read More »