ሐምሌ ፲፭ ( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰኔ 7 ቀን 2008 ዓም በኢትዮጵያ አየር ሃይል የድሬዳዋ ምድብ ውስጥ ሄሊኮፕተርን በመሬት ላይ የማሮጥ ስራ ወይንም ኢንጅን ቴስት ረንአፕ (Engine Test Runup) ሲያደርጉ የነበሩት ሌ/ኮሎኔል ፀጋዘዓብ ካሳ ሌሎች ሁለት የቆሙ ሄሊኮፕተሮችን በመግጨታቸው ሶስቱም ሄሊኮፕተሮች ከጥቅም ውጭ ሆነው የቆዩ ሲሆን፣ ሄሊኮፕተሮቹ በከባድ መኪና ተጭነው ወደ ደብረዘይት አየር ሃይል ...
Read More »Author Archives: Central
የጤንነቱ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኘው አቶ ሃብታሙ አያሌው ከአቃቤ ሕግ ጋር የቃል ክርክር ለማድረግ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠው
ሐምሌ ፲፭ ( አሥራ አምስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ ሃብታሙ አያሌው ከአገር ወጥቶ እንዲታከም በሕክምና ቦርድ የተፈረመበት ማረጋገጫ ቢሰጠውም ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በመዝገብ ቤት በኩል ከአቃቤ ሕግ ጋር የቃል ክርክር ለማድረግ ለማክሰኞ ሀምሌ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል። አቃቤ ሕግ ቅሬታ ባላቀረበበት ጉዳይ ላይ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ከሕግ አግባብ ውጪ ውሳኔ ማሳለፉን ...
Read More »የአማራ ክልል ቴሌቪዥን ስርጭት ተቋረጠ
ኢሳት (ሃምሌ 15 ፥ 2008) የአማራ ክልል ቴለቪዥን የሳተላይት ስርጭት መቋረጡን የአማራ ክልል መገናኛ ብዙሃን ያረጋገጠ ሲሆን፣ ጉዳዩ ከክፍያ ጋር የተያያዘ መሆኑን አመልክቷል። ሆኖም አንዳንድ ምንጮች የስርጭቱን መቋረጥ ከጎንደር ህዝባዊ እንቅስቃሴ ጋር አያይዘውታል። የአማራ ክልል ቴሌቪዥን ከጎንደር ህዝባዊ እንቅስቃሴና ከወልቃይት የመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና የመንግስት ባለስልጣናት የመብት ጠያቂዎቹን በሚወነጅሉበት መጠን አለመስራቱንና ህዝብን ከሚያስቆጡ ድርጊቶች መቆጠቡ ለስርጭቱ መቋረጥ እንደምክንያት ...
Read More »በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች የምግብ እጥረት ተከሰተ
ኢሳት (ሃምሌ 14 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ወደ ረሃብ ሊሸጋገሩ አንድ ደረጃ ብቻ የቀራቸው ወረዳዎች ቁጥር 206 መሆኑንና በአለም አቀፍ የምግብ ፕሮግራም ሲሰራጭ የነበረው የምግብ አቅርቦት እጥረት ማጋጠሙን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ። ያጋጠመውን የምግብ አቅርቦት ለመቅረፍ 426 ሚሊዮን ዶላር በአስቸኳይ የሚያስፈልግ ሲሆን፣ በስደት ክልሎች ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ አሁንም ድረስ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል። የአለም አቀፍ ምግብ ...
Read More »መንገድ ፕሮጄክት ለመስራት የተዋዋለ የህንድ ኩባንያ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ይዞ መጥፋቱ ተነገረ
ኢሳት (ሃምሌ 14 ፥ 2008) በቅርቡ አንድ ቢሊዮን ብር አካባቢ የሚደርስ የመንገድ ፕሮጄክት ተሰጥቶት የነበረ አንድ የህንድ ስራ ተቋራጭ ኩባንያ የተረከበውን ስራ ሳያጠናቅቅ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ይዞ ከሃገር ኮበለለ። በዚሁ ፕሮጄክት ስር ይሰሩ የነበሩ ከ200 በላይ ሰራተኞች ሊከፈላቸው የሚገባ የአንድ ወር ከግማሽ ደሞዝ ሳይከፈላቸው መቅረቱን በመግለጽ ላይ መሆናቸው ታውቋል። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በበኩሉ የ958 ሚሊዮን ብር የመንገድ ፕሮጄክት ተሰጥቶት ...
Read More »ሁለት ኢትዮጵያውያን በካይሮ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ጽ/ቤት በራፍ ላይ ራሳቸውን አቃጠሉ
ኢሳት (ሃምሌ 14 ፥ 2008) ሁለት ኢትዮጵያውያን ካይሮ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን በራፍ ራሳቸውን አቃጠሉ። በቅርቡ ኦሮሚያ ከተካሄደው መጠነ ሰፊ ግድያና እስራት ሸሽተው ግብጽ መድረሳቸው የተገለጸው እነዚህ ሁለት የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ ራሳቸውን ያቃጠሉት በተቃውሞ መሆኑን ተመልክቷል። ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን በማቃጠል ተቃውሟቸውን የገለጹት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን የካይሮ ቢሮ የስደተኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ በማድረጉ እንደሆነም መረዳት ተችሏል። በግብፅ ካይሮ የሚገኘው ...
Read More »የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ ዜጎች ላይ የወሰዱትን እርምጃ እንደሚያጣራ አስታወቀ
ኢሳት (ሃምሌ 14 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ወታደሮች በቅርቡ 14 ሰላማዊ ሰዎችን በሶማሊያ ገድለዋል የተባለውን መረጃ ምርመራ ሊያካሄድበት መሆኑን በሃገሪቱ በሰላም ማስከበር ስራ ላይ ተሰማርቶ የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ልዑክ ይፋ አደረገ። የኢትዮጵያ ወታደሮች ባለፈው ሳምንት በቤይ ግዛት በምትገኘው የዋርዲንግ ከተማ አካባቢ ከአልሸባብ ታጣቂ ሃይል ጋር ውጊያን ባካሄዱ ጊዜ በንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያ ፈጽመዋል የሚል መረጃ እንደደረሰው ልዑኩ መገልጹን አዣንስ ...
Read More »ህወሃት በሰሜን ጎንደር የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ለማውገዝ የሚያደርገው እንቅስቃሴ አደገኛ ነው ሲሉ የኮሚቴ አባላት ተናገሩ
ሐምሌ ፲፬ ( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጋር በተያያዘ በሰሜን ጎንደር የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ በአካባቢው የሚታዬው ውጥረት እንደቀጠለ ባለበት ወቅት፣ ህወሃት መራሹ የትግራይ መስተዳድር፣ የኮሚቴ አባላቱን እንዲሁም አጠቃላዩን የህዝብ ንቅናቄውን የሚያወግዙ ሰልፎችን በማዘጋጀት ዋናውን የማንነት ጥያቄ ለማደፋፈን የሚያደርገው ሙከራ አደገኛ ውጤት ይኖረዋል ሲሉ የኮሚቴ አባላቱ አስጠንቅቀዋል። በአዲ ረመጥ የተካሄደው የተቃውሞ ...
Read More »አንድም ሰራዊት ለመንግስት እጅ አልሰጠም ሲሉ የአፋር ህዝብ ፓርቲ መሪ አስታወቁ
ሐምሌ ፲፬ ( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ 400 የሚሆኑ የአፋር ህዝብ ፓርቲ ወታደሮችና አመራሮች በድርድር እጃቸውን ሰጡ በማለት በመገናኛ ብዙሃን ያሰራጨው ዘገባ ሃሰት መሆኑን የድርጅቱ መሪ ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ ተናግረዋል። ዶ/ር ኮንቴ እንዳሉት ከአመት በፊት የድርጀቱ ሊ/መንበር የነበረው አቶ አሎ አልዳየስ ከኮሎኔል ሙሃመድ አህመድ ጋር በመሆን ድርድር መጀመራቸው እንደታወቀ በመጋቢት 2007 ዓም ከሃላፊነት ...
Read More »ታላቁ የኢትዮጵያ የቲያትር ባለሙያ አቶ አባተ መኩሪያ አረፈ
ሐምሌ ፲፬ ( አሥራ አራት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ቴያትር ሲነሳ ስማቸው ከቀዳሚዎቹ ተርታ የሚጠራው አንጋፋው የቴያትር ባለሙያ አባተ መኩሪያ ፣ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ72 ዓመታቸው አረፈ። የቀብሩ ስነስርዓት ሃሙስ በአዲስ አበባ ከተማ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን እንደተፈጸመ መረዳት ተችሏል። በቲያትር አዘጋጅነት በቲያትርና ስነጥበብ መምህርነት እንዲሁም ቲያትር ቤቶችን በሃላፊነት በመምራት በኪነጥበቡ መስክ ጉልህ አስተዋጽዖ ...
Read More »