ነሃሴ ፳፭ ( ሃያ አምስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦህዴድ ክልሉን ያረጋጉልኛል ያላቸውን በርካታ ቁጥር ያላቸውን የኦሮሞ አባቶች በመጥራት በሶደሬ የመዝናኛ ማእከል ስብሰባ እያደረገ ሲሆን፣ ከሆቴሉ ምንጮች በተገኘው መረጃ ለአንድ አልጋ በቀን ከ700 እስከ 1 ሺ ብር ይከፈላል። ነሃሴ 23 ቀን ከምሽቱ 2 ሰአት ላይ በመቱ ዩኒቨርስቲ አውቶቡሶች ተጭነው የመጡት አባቶች፣ ለ4 ቀናት የሚቆዩ ሲሆን፣ 6 በሬዎች ...
Read More »Author Archives: Central
ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 816 ስደተኞች በሱዳን ቁጥጥር ስር ዋሉ
ኢሳት (ነሃሴ 25 ፥ 2008) በሱዳንና ሊቢያ ድንበር ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት በህገወጥ መንገድ ሲጓዙ ነበሩ የተባሉ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ80 በላይ የተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት ስደተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሱዳን የጸጥታ ሃይል ባለስልጣናት አስታወቁ። እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከሰኔ 27 እስከ ነሃሴ 16 2016 ድረስ 816 የአፍሪካ ስደተኞች በሊቢያ አድርገው ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ መታሰራቸውን የሱዳን ፖሊስ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዥ ለመገናኛ ብዙሃን ...
Read More »በአማራ ክልል ህዝባዊ ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል፣ ገበሬዎች የአጋዚ ወታደሮች ጋር እየተጋፈጡ ነው
ኢሳት ( ነሃሴ 25 ፥ 2008) በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ እና ምስራቅ ጎጃም የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ አድማሱን እያሰፋ ወደሌሎች ዞኖች እየገሰገሰ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት መደበኛ ጦር በማንቀሳቀስ ተቃውሞን ለማፈን እየሞከረ መሆኑ ተነገረ። በአማራ ክልል የሚገኘው ህዝብ ተቃውሞውን በቤት ውስጥ አድማ በማድረግ የትግል ስልቱን መቀየሩና ሌሎች አካባቢዎችም እንደሁኔታው የትግል ስልታቸው እየቀያየሩ እንዲታገሉ ጥሪ ቀርቧል። ...
Read More »በኦሮሚያና አማራ ክልልሎች ከተፈጠረው ህዝባዊ እምቢተኝነት ጀርባ የውጭ ሃይል አለበት ሲሉ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ገለጹ
ኢሳት (ነሃሴ 24 ፥ 2008) የኢህአዴግ ም/ቤት ያደረገውን የ15 አመት ግምገማ ተከትሎ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ “በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ከተነሱት ግጭቶች ጀርባ የውጭ ሃይል አለበት” በማለት ውንጀላ አሰሙ። በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ፣ በአገሪቱ የሚስተዋሉትን ግጭቶች በማባባስ ጀርባ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብቷን እንዳትጠቀም የሚፈልጉ አገራት አሉ በማለት ተናግረዋል። አያይዘውም፣ “ሁከቶችን በገንዘብ እየደገፉ የሚገኙት ...
Read More »የቀድሞ ከፍተኛ የአጋዚ ክ/ጦር አዛዥ ጦሩ አፈሙዙን ወደ አዛዦቹ እንዲያዞር ጠየቁ
ኢሳት (ነሃሴ 24 ፥ 2008) በአማራና በኦሮሚያ ክልል በተቀጣጠለው ህዝባዊ እምቢተኝነት በመንግስት የግድያ ትዕዛዝ የተሰጠው የአጋዚ ጦር ወደ ህዝቡ እንዳይተኩስ እና መሳሪያውን ወደ አዛዦቹ እንዲያዞር አንድ የቀድሞ ከፍተኛ የአጋዚ ክ/ጦር አዛዥ ጠየቁ። በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የተነሳውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ መንግስት ያሰማራቸው የጸጥታ ሃይሎች ህዝቡን በመግደል ላይ መሆናቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳዘናቸው ለኢሳት የገለጹት የቀድሞ አጋዚ ክ/ጦር መስራችና አመራር ኮሎኔል አለበል አማረ፣ ...
Read More »በርካታ ኢትዮጵያውያን በህወሃት/ኢህአዴግ ሃይሎች ለተሰው ዜጎች አጋርነታቸውን ለማሳየት ጸጉራቸውን እንደተላጩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ
ኢሳት (ነሃሴ 24 ፥ 2008) በአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች ህዝባዊ እምቢተኝነት ተጋግሎ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን በመንግስት ሃይሎች ጥቃት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን አጋርነታቸው ለማሳየት ጸጉራቸውን መላጨታቸውን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። ኢትዮጵያውያን ጸጉራቸውን ሲላጩ የሚያሳይ ቪዲዮ በማህበራዊ ደረገጾች መለቀቃቸውን ያወሳው የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የእንግሊዝኛው አገልግሎት፣ የጸጉር መላጨት ድርጊት የታሰሩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጥሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ የተፈጸመ መሆኑን አስረድቷል። በኢትዮጵያ ...
Read More »በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ህዝባዊ እምቢተኝነት ወደሌሎች ቦታዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው ተባለ
ኢሳት (ነሃሴ 24 ፥ 2008) በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ህዝባዊ እምቢተኝነት አድማሱን አስፍቶ በሰላማዊ ሰልፍና በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ተጠናክሮ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት፣ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ዛሬ ማክሰኞች ብዛት ባላቸው የአማራ ክልል ከተሞች እየተካሄደ እንደሆነ ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። በምዕራብ አማጭሆ አብርሃ ጅራ የተጀመረው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ወደ አብደራፊና አጎራባች አካባቢዎች ተዛምቶ ህዝቡ ከአገዛዙ ወታደሮች ጋር ከፍተኛ ፍጥጫ ውስጥ እንደሚገኝ ለመረዳት ተችሏል። በጋይንት፣ ...
Read More »በኢትዮጵያ መንግስት እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ወንጀል ገለልተኛ አለም አቀፍ ቡድን እንዲመረምረው ተጠየቀ
ኢሳት (ነሃሴ 24 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም ክልሎች በመንግስት ጸጥታ ሃይሎች እየተደረገ ያለውን ግድያና፣ ሰቆቃ፣ እና እስራትን የሚመረምር አለም አቀፍ ገለልተኛ ቡድን እንዲቋቋም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሲቪክ ማህበራት ባወጡት መግለጫ ጠየቁ። የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ተከላካይ ድርጅት (ዲፌንድ ዲፌንደርስ)፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ፕሮጄክት፣ Front Line Defenders, እና የሰብዓዊ መብት አለም አቀፍ ፌዴሬሽን (FIDH) በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ በኢትዮጵያ ...
Read More »በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ተከትሎ አብዛኞቹ አካባቢዎች ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ነጻ እየወጡ ነው ተባለ
ኢሳት (ነሃሴ 23 ፥ 2008) በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ አድማሱ አስፍቶ መላው ሰሜን ጎንደርን፣ ደቡብ ጎንደርን፣ ምዕራብ ጎጃምን፣ አዊን እና ምስራቅ ጎጃምን ከህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ነጻ እያወጣ መሆኑ ተገለጸ። በጎንደር፣ ደባርቅ፣ ዳባት፣ ገብደብየ፣ አምባጊወርጊስ፣ ጎንደር፣ ደምቢያ፣ አዲስ ዘመን፣ በለሳ፣ ወረታ፣ ዓለም በር፣ ደብረ ታቦር፣ ጋሳይ- ክምር ድንጋይ፣ ነፋስ መውጫ፣ ሳሊ፣ ጨጭሆ፣ ጎብጎብ፣ ፍላቂት፣ ደራ ሐሙሲት፣ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ የአገዛዙ መዋቅር ...
Read More »ከፍተኛ ቁጥር ያለው መደበኛ ሰራዊት ወደ አማራ ክልል እየተንቀሳቀሰ ነው
ኢሳት (ነሃሴ 23 ፥ 2008) ህወሃት በአማራ ክልል እየተካሄደው ባለው ህዝባዊ ንቅናቄ በድንጋጤ ላይ የሚገኘው የህወሃት አገዛዝ፣ በጎንደር፣ ጎጃም፣ አዊ ዞኖች የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ለማስቆም እንዲያግዙ ከ2ሺ በላይ የአጋዚ ጦር አባላትን ከአዲስ አበባ ትናንት ዕሁድ ወደ አማራ ክልል ማንቀሳቀሱ ተገለጸ። በአማራ ክልል በጎጃምና ጎንደር የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ፣ የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ መጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደደረሰ የተረዳው የህወሃት አገዛዝ፣ ተቃውሞን በሃይል ...
Read More »