ኢሳት (ጳጉሜ 2 ፥ 2008) የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ መንግስት ይፈጸማል ያለውን ግድያና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወም ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እንዲቋረጥ መወሰኑን ረቡዕ ይፋ አደረገ። ህብረቱ ባለፈው አመት ያቋቋመው ልዩ የአስቸኳይ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሃገራት በሚሊዮን የሚቆጠር ዩሮ ገንዝብ ድጋፍ ለማድረግ ያለመ እንደነበር ህብረቱ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። ይሁንና፣ በኢትዮጵያ መንግስት እየተፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ...
Read More »Author Archives: Central
በቂሊንጦ እስር ቤት ከእሳት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ የቤተሰቦቻቸውን ሁኔታ ለማወቅ የጠየቁ ቤተሰቦች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረጋቸው ታሰሩ
ጳጉሜ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የእስረኞች ቤተሰቦች ላለፉት አምስት ቀናት የቤተሰቦቻቸውን ሁኔታ ለማወቅ ወደ ቅሊንጦ እስር ቤት ተመላልሰዋል። በገዢው ፓርቲ በኩል 23 ሰዎች እንደሞቱ ከመገለጹ በስተቀር የሟቾቹን ቁጥር በዝርዝር ይፋ ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆነም። አብዛኞቹ ሟቾች በጥይት መሞታቸው ብቻ ሳይሆን፣ ቁጥሩ ገዢው ፓርቲ ከጠቀሰው በእጥፍ ከፍ እንደሚል መረጃዎች ያመለክታሉ። ኢትዮጵያውያን በድርጊቱ በመበሳጨት ሃዘናቸውን እየገለጹ ባለበት ወቅት፣ በገዢው ፓርቲ ...
Read More »በኦሮምያ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ ተጠናክሮ ቀጥሎአል
ጳጉሜ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የኦሮምያ ከተሞች የንግድ እንቅስቃሴዎች ቆመዋል። የንግድ መደብሮች ተዘግተዋል፤ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ አቁመዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች የስራ ማቆም አድማውን በጣሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ሻሸመኔ፣ አሰላ፣ ነቀምት፣ ባሌ ሮቤ ፣ ጊምቢ፣ ዶዶላ፣ ቆቦ፣ ዳዳር እና ሌሎችም በርካታ ከተሞች አድማውን ተግባራዊ እያደረጉ ሲሆን፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ነጋዴዎች ስራቸውን እንዲጀምሩ የተለያዩ እርምጃዎችን ቢወስዱም አልተሰካላቸውም። የስራ ማቆም ...
Read More »በባህርዳርና ፍኖተሰላም በርካታ ወጣቶች ወደ ብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ተወሰዱ
ጳጉሜ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር ከተናሳው ህዝባዊ እምቢተኝነት ጋር በተያያዘ ከታሰሩት ከ1 ሺ 500 ያላነሱ ወጣቶች መካከል 600 የሚሆኑት ዛሬ ወደ ብር ሸለቆ ወታደራዊ ካምፕ የተወሰዱ ሲሆን እስረኞቹ በቆይታቸው ከፍተኛ ስቃይ እንደደረሰባቸው የአይን እማኞች ገልጸዋል። አብዛኞቹ ወጣት እስረኞች በደረሰባቸው ድብደባ የተነሳ ተጎሳቁለዋል፣ የጤና እክል ያጋጠማቸውም ቁጥራቸው በርካታ ነው። ድብደባውን መቋቋም የተሳናቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ወጣቶች ...
Read More »በኦሮሚያ የስራ ማቆም አድማ ተጀመረ
ኢሳት (ጳጉሜ 1 ፥ 2008) ከአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው የአምቦ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ማክሰኞ የስራ ማቆም አድማ መጀመሩን ነዋሪዎች ለኢሳት አስታወቁ። በአምቦና ጉደር አካባቢ የንግድ ተቋማትን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶች መስጫ ተቋማት የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ መሆናቸውን በጉዳዩ ዙሪያ ከኢሳት ጋር ቃለምልልስን ያደረጉ ነዋሪዎች አስረድተዋል። መንግስት በክልሉ እንዲሁም በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች እየወሰደ ያለውን ግድያና ...
Read More »በነቀምቴ ከተማ ሁለት የአጋዚ ወታደሮች ሲገደሉ ሌላ አንድ መቁሰሉ ተነገረ
ኢሳት (ጳጉሜ 1 ፥ 2008) በምዕራብ ኦሮሚያ ክልል ስር በምትገኘው የነቀምቴ ከተማ ማክሰኞ ምሽት ማንነታቸው ያልታወቁ አካላት በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ በፈጸሙት የቦንብ ጥቃት ሁለት የአጋዚ ወታደሮች መገደላቸውንና ሌላ አንድ ወታደር መጎዳቱን እማኞች ለኢሳት ገለጹ። ወተደሮቹ ትቃቱ የተፈጸመባቸው በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ወከባ ማድረሳቸው አስመርሯቸው እንደሆነ ተመልክቷል። ወታደሮቹ ላይ የተፈጸመው ጥቃት በከተማዋ ቀበሌ 07 ውስጥ በሚገኝ አንድ የመንግስት ድርጅት ውስጥ መከሰቱን ...
Read More »የብሪታኒያ መንግስት ዜጎቹ ወደ አማራና ጋምቤላ ክልሎች ሲጓዙ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ አሳሰበ
ኢሳት (ጳጉሜ 1 ፥ 2008) በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች በመካሄድ ላይ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ እልባት አለማግኘቱን ተከትሎ የብሪታኒያ መንግስት ዜጎቹ ወደ ክልሉ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ ማክሰኞ በድጋሚ አሳሰበ። ከሶስት ቀን በፊት ለዜጎቹ ተመሳሳይ ማሳሰቢያን አሰራጭቶ የነበረው የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዜጎቹ አሁንም ድረስ ወደክልሉ በሚያደርጉት ማንኛውም እንቅስቃሴ ላይ የጥንቃቄ እርምጃን እንዲያደርጉ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። የሃገሪቱ ዜጎች በአማራ ...
Read More »ቁጥራቸው የማይታወቅ እስረኞች በሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው ነው
ኢሳት (ጳጉሜ 1 ፥ 2008) ሰሞኑን በቂሊንጦ እስር ቤት የደረሰውን የእሳት አደጋ ተከትሎ የገቡበት ካልታወቀው ወደ ሶስት ሺ አካባቢ እስረኞች መካከል በርካቶች በተለያዩ የአዲስ አበባ ሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ተገለጸ። የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በበኩሉ ለ8 ሰዓታት ያህል የቆየው የእሳት አደጋ የእስረኞቹን ንብረቶችና መጠለያ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ማውደሙን ማክሰኞ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ አመልክቷል። ደርሷል የተባለው የእሳት አደጋ ...
Read More »በቂሊንጦ የጸጥታ ሃይሎች በእስረኞች ላይ የጅምላ የተኩስ እርምጃን ሲወስዱ እንደነበር ተገለጸ
ኢሳት (ጳጉሜ 1 ፥ 2008) በሳምንቱ መገባደጃ ቅዳሜ በቂሊንጦ እስር ቤት የደረሰውን የእሳት አደጋ ተከትሎ የእስር ቤቱ የጸጥታ ሃይሎች በእስረኞች ላይ የጅምላ የተኩስ እርምጃን ሲወስዱ እንደነበር በእለቱ በእስር ቤቱ ጥበቃ ስራ ላይ ተሰማርቶ የነበረ የጸጥታ ባልደርባ ገለጸ። ለደህንነቱ ሲል ስሙን ያልገለጸው ይኸው የቂሊንጦ እስር ቤት ጠባቂ በ20 ደቂቃ አምስት እስረኞች በኢላማ ተኩስ ተገድለው መመልከቱን አዲስ አበባ ውስጥ ለሚታተመው አዲስ ስታንዳርድ ...
Read More »የአሸንዳ በዓልን በጭፈራ ሊያሳልፉ የነበሩ የህወሃት ደጋፊዎች ተቃውሞ ገጠማቸው፥ በመንግስት ሃይሎች ጉዳት ለደረሰባቸው ገንዘብ ተሰበሰበ
ኢሳት (ጳጉሜ 1 ፥ 2008) በካናዳ ካልጋሪ የአሸንዳ በዓልን በደስታና በጭፈራ ለማሳለፍ የሞከሩ የህወሃት ደጋፊዎች በአካባቢ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ገጠማቸው። ኢትዮጵውያኑ ባለፈው ቅዳሜ ተቃውሟቸውን ያሰሙት በአሁኑ ወቅት በአገራችን በርካታ ሰዎች በአጋዚ ወታደሮች እየተገደሉና እየተጨፈጨፉ በደስታ መጨፈር ሰብዓዊነት የጎደለው ተግባር መሆኑን በቁጭት በመግለጽ ነው። በአሰቃቂ ሁኔታ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በአጋዚ ታጣቂዎች የተገደሉ ሰዎችን ፎቶ በመያዝ ኢትዮጵያውያኑ የህወሃትን ደጋፊዎች ድርጊት አውግዘዋል። ተቃውሞ ...
Read More »