ኢሳት (ጳጉሜ 3 ፥ 2008) በአለም በሰብዓዊ መብት መከበር ዙሪያ የሚሰሩ 14 የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ እርምጃን እንዲወስድ የጋራ ጥያቄን ሃሙስ አቀረቡ። ለምክር ቤቱ ጥያቄያቸውን ያቀረቡት እነዚሁ ድርጅቶች ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈጸሙ ግድያና አፈና በአስቸኳይ እንዲቆምና ድርጊቱ በገለልተኛ አለም አቀፍ ተቋማት/ቡድን ማጣራት እንዲካሄድበት አሳስበዋል። ከፊታችን ማክሰኞ ጀምሮ 33ኛ ልዩ ...
Read More »Author Archives: Central
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ኮንሶ በሚገኙ ዘጠኝ ቀበሌዎች ላይ የእሳት ቃጠሎ ማድረሳቸው ተነገረ
ኢሳት (ጳጉሜ 3 ፥ 2008) በደቡብ ክልል በሚገኘው የሰገን ህዝቦች ስር የሚገኙ የኮንሶ ብሄረሰብ አባላት በቅርቡ ያቀረቡትን አስተዳደራዊ ጥያቄ ተከትሎ ከቀናት በፊት በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በዘጠኝ ቀበሌዎች የእሳት ቃጠሎ አደጋ መድረሱን ለኢሳት አስታወቁ። በዘጠኙ ቀበሌዎች የደረሰውን ይህንኑ የእሳት አደጋ ተከትሎም ከ1ሺ በላይ ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው እንደሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ከዜና ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ አስረድተዋል። የኮንሶ ብሄረሰብ አባላት በልዩ ወረዳ ወይም ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች አድማው ለሶስተኛ ቀን ቀጥሎአል
ጳጉሜ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጳጉሜ አንድ ቀን የጀመረው የኦሮሚያ ክልል ሕዝባዊ እንቢተኝነት አሁንም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ በአዳ በርጋ፣ ጊኒር ፣ ሙገር፣ ዶዶላ፣ አምቦ፣ ነቀምቴ፣ ጉደር፣ ደደር፣ ቡራዩ፣ ሱሉልታ እንዲሁም በምስራቅ ሃረርጌ የንግድ እንቅስቃሴዎች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል። የፀጥታ አስከባሪዎች በግዳጅ የንግድ ድርጅቶችን ለማስከፈት የሃይል እርምጃዎችን ቢወስዱም በህብረተሰቡ ተቀባይነት ሊያገኙ ግን አልቻሉም። በወለጋ ለቀምት ከተማ አድማውን ተከትሎ ...
Read More »በአማራ ክልል ወጣቶችን የማሰር ዘመቻ እንደቀጠለ ነው
ጳጉሜ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ገዢው ፓርቲ በአንድ በኩል የአገር ሽማግሌዎችን እየሰበሰበ ከእንግዲህ ወጣቶችን እንደማያስርና ያሰራቸውን እንደሚፈታ ቃል ቢገባም በሌላ በኩል አሁንም ወጣቶችን በብዛት እየያዘ ወደ ብርሸለቆ እያጋዘ ነው። በብርሸለቆ ወታቶች በርሃብና ውሃ ጥም እየተሰቃዩ ሲሆን፣ በባዶ እግራቸው በጠርሙስና እሾህ ላይ እንዲራመዱ እንደሚደረጉ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ይሁን እንጅ ወጣቶች የሚደርስባቸውን እንግልት ...
Read More »በአማራ እና ኦሮምያ ለተሰማሩት ወታደሮች የሶማሊ ክልል ህዝብ የቀንድ ከብት እንዲለግስ ተገደደ
ጳጉሜ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት (ኦብነግ) እንደገለጸው የክልሉ ፕሬዚዳንት ከአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች ተፈናቀሉ ለተባሉ የትግራይ ተወላጆች ከውጭ ለልማት በሚል ከሚለገሰው ገንዘብ በማንሳት 10 ሚሊዮን ብር መስጠቱ አስገራሚ ሆኖ እያለ፣ አሁን ደግሞ በደጋሃቡርና ቀብሪደሃር ወረዳዎች በመዘዋወር በአማራ፣ በኦሮምያና ጋምቤላ ለተሰማሩ ወታደሮች የእርድ ከብቶችን ህዝቡ እንዲያዋጣ እያስገደደ ነው ። ፕሬዚዳንቱ ለዚህ ፕሮጀክት ከብት ...
Read More »የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ምርመራ እንዲካሄድ ጠየቁ
ጳጉሜ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዓለም አቀፍና አገርበቀል የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ድርጅት በኢትዮጵያን እየተፈጸሙ ያሉትን የመብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካል እንዲመረመሩ በጋራ በደብዳቤ ጠይቀዋል። በኢትዮጵያ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እየተባበሰ የመጣው ግድያ፣ እስራትና አካል ማጉደል መቀጠሉና የዜጎች ሰላማዊ ሕይወት አስጊ ሁኔታ ላይ መወደቁን ድርጅቶቹ በጋራ አስታውቀዋል። የተመድ የሰብዓዊ መብት ጠቅላላ ጉባኤ በቀጣይ ...
Read More »ኢሳት በሶስተኛ ሳተላይት ስርጭት ጀመረ
ኢሳት (ጳጉሜ 3 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ሳተላይትና ቴሌቪዥንና ሬዲዮ (ኢሳት) አሁን ካሉት ሁለት የሳተላይት ስርጭት ፍሪኩዌንሲዎች (Satellite Frequencies) በተጨማሪ ሶስተኛ ፍሪኩዌንሲ በመከራየት የስርጭት አድማሱን ማስፋቱን ገለጸ። “ኢሳት ባለፉት 6 እልህ አስጨራሽ አመታት የህወሃትን ቀቢጸ-ተስፋ የአፈና እንቅስቃሴ ተቋቁሞ የስርጭት አድማሱን በማስፋትና በማጠናከር ላይ ይገኛል” ያለው የኢሳት ማኔጅመንት መግለጫ፣ የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ኢሳትን ከአየር ላይ ለማውረድ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠር ዶላር መድቦ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም አልተሳካለትም ...
Read More »የልጃቸውን ሁኔታ ለማወቅ ጥያቄ ያቀረቡ እናት በፖሊስ ድብደባ ተፈጸመባቸው
ኢሳት (ጳጉሜ 2 ፥ 2008) አንድ ልጃቸው በቂሊንጦ እስር ቤት የታሰረባቸው እናት ረቡዕ የልጃቸውን ሁኔታ ለማወቅ ጥያቄ ባቀረቡ ጊዜ በፖሊስ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለሰዓታት ታስረው መቆየታቸው ለኢሳት ገልጸዋል። “ልጄም ከሞተ አስከሬን ይሰጠኝ ብዬ በመጠየቄ በፖሊስ ድብደባ ተፈጽሞብኛል” ሲሉ የገለጹት እናት ለአምስተኛ ቀን የልጃቸውን ሁኔታ ባለማወቃቸው ምክንያት ለከፋ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ አስረድተዋል። ሌላ አንዲት ሴት ልጅ በቃሊቲ እስር ቤት በእስር ላይ እንዳለች ...
Read More »በቂሊንጦ የእስረኞችን ሁኔታ ለመጠየቅ የሄዱ የእስረኛ ቤተሰቦች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እስርና ድብደባ ተፈጸመባቸው
ኢሳት (ጳጉሜ 2 ፥ 2008) በቂሊንጦ እስር ቤት የሞቱትና የገቡበት ያልታወቀ እስረኞችን ሁኔታ ለማወቅ ረቡዕ ረፋድ ላይ ወደ ስፍራው በማቅናት ላይ የነበሩ የእስረኛ ቤተሰቦች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ። የመንግስት ባለስልጣናት ስለሞቱና ወደሌላ እስር ቤት ተላልፈዋል ስለተባሉ እስረኞች ረቡዕ መረጃን እንደሚሰጡ ቃል ቢገቡም በእለቱ መረጃው ለእስረኛ ቤተሰቦች አለመገልጹ ታውቋል። ምላሽ ባለማግኘታቸው ስጋት ያደረባቸው የእስረኛ ቤተሰቦች ወደ ስፍራው ቢያመሩም ...
Read More »በአበባ እርሻ የተሰማራ የኔዘርላንድ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ጠቅልሎ መውጣቱን አስታወቀ
ኢሳት (ጳጉሜ 2 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በግዙፍ የአበባ እርሻ ምርት ላይ ተሰማርቶ የነበረ አንድ አለም አቀፍ የኔዘርላንድ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ጠቅልሎ መውጣቱን ይፋ አደረገ። ኢስመራልዳ ፋርም የተሰኘው ኩባንያ በአማራ ክልል በመንግስት ላይ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ በአበባ ማምረቻ የእርሻ ድርጅቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጿል። ከሳምንት በፊት በተፈጸመበት በዚሁ ጥቃት ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት እንደወደመበት የኔዘርላንዱ ኩባንያ አውስቷል። በክልሉ ...
Read More »